የጃዋር እና የፋንታሁን ዋቄ ጽምዶ! የአቶ ጌትነት ወርቁ “ግልጽ ደብዳቤ” የአርሲን የ”ሽብር” ወንጀል ተንተርሶ ይፋ የሆነው አዲሱ የግብጽ የድህረ ምርጫ ማኒፌስቶ፤

Date:

አዲ ሪፖርተር -“አገር ሰላም ብለን ተኝተናል። ሌሊት መጡና ተኩስ ከፈቱ። ሚሊሻና ፖሊስ ገጥመው ነበር። ፍሬ አለቀባቸውና የቻሉት ሸሹ፣ ያልቻሉት ሞቱ” ይላል የጠለታ ነዋሪ። ጠለታ ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ሌሊት ጥቃት ያስተናገደችው የአርሲ አንድ አነስተኛ ከተማ ናት።

ከፍያለው /ስሙ የተቀየረ/ ጠለታ ተወልዶ ያደገ፣ አሁን ተፈናቅሎ ኢሬቻ በምትባለዋ ሌላ አነስተኛ ከተማ ዘመድ ጋር የተጠለለ ጎረምሳ ነው። “ማን ነው ጥቃቱን የሰነዘረው?” በሚል አዲስ ሪፖርተር ሲጠይቀው አብረው የነበሩ ተፈናቃዮች “ሸኔ፣ ኦነግ ሸኔ” በማለት በጋራ መለሱ። “ሸኔዎች መሆናቸውን እንዴት አወቃችኋቸው?” ለተባሉት “ከገደሉህ፣ ከዘረፉህ፣ ንብረትህን ካቃጠሉ እነሱ ናቸው። ይህ መለያቸው ነው። በደንብ እናውቃቸዋለን። የሚመጡት ከበረሃው ቢዮ አቅጣጫ ነው” አሉ ቁልቁል ወደታች እያመለከቱ።

ቢዩ ከጠለታ በታች ወደ መርቲ ለማቆራረጥ የምትመች መንደር ናት። ብዙ ጊዜ የሸኔ ኃይሎች ይህችን መንደር እንደሚመርጧት፣ በጣም የሚሞቅ ጫካ እንደሆነ ተፈናቃዮቹ ይናገራሉ።

ኢሬቻ የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሚገኝበት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የአማራ ተወላጆች የሚኖሩበት አካባቢ በመሆኑ ሸኔ ደፍሮ እንደማይመጣ እነ ከፍያለው ይናገራሉ። በላይ /ስሙ የተቀየረ/ “ኢሬቻ፣ ነዋሪው መሣሪያ አለው። ቤተ ክርስቲያኑም ራሱን መጠበቂያ ስላለው ማንም አይደፍርም” ይላል። የመሣሪያ ዓይነቱንም ዘርዝሮ ይናገራል።

በአሰኮ ወረዳ ሥር የምትገኘው ጠለታ ሊነጋጋ ሲል በድንገት የተወረረችው ከዚህ ቀደም ባልታየ መልኩ ነው። የአሰኮ ከተማ ነዋሪ የሆነና ከጠለታ ተፈናቅለው የመጡ ዘመዶቹን የሚያስተናግደው ስንታየሁ /ስሙ የተቀየረ/ ስልኩን አቀብሎት ምስክርነቱን የሰጠው ተፈናቃይ፣ በግምት ከወር በፊት የሸኔ ታጣቂዎች ለተመሳሳይ ጥቃት መጥተው ሕዝቡ፣ ፖሊስና ሚሊሻው አንድ ላይ ሆኖ አሳዷቸው ነበር። ሰባት ያህል ታጣቂዎችም ተገድለውባቸው ነበር። “በዚህ ቂም ተነሳስተው ተሰባስበው መጡና ያደረጉትን አደረጉ” ሲል የሚያውቀውን ይናገራል።

“ዋርድያውም፣ ሚሊሻውም፣ ሕዝቡም በተኛበት ሌሊት መጥተው ተኩስ ከፈቱ። ሕዝቡም፣ ሚሊሻውም፣ ፖሊሱም ገጠሙ። ፍሬ አለቀባቸው /ጥይት ማለቱ ነው/ ከዚህም የሞተው ሞተ፣ የቻለው ሸሸ። የቻሉትን ቀልብ፣ ከብትና ንብረት ዘረፉ። በጅምላ መኖሪያ ቤት አቃጠሉ” በማለት ወደ ኢሬቻ የሸሸው ከፍያለው ያስረዳል።

ጠለታ ያሉ ሱቆች በሙሉ መዘረፋቸውን የጠቆመው ከፍያለው፣ የጸጥታ ኃይሉ ከወረዳው የሚሊሻ ዘርፍ በቂ ጥይት እንደማይሰጠው፣ በቂ ጥይት ቢኖር ኖሮ በዚህ ደረጃ ጉዳት ሊደርስ እንደማይችል መስማቱን መስክሯል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ይሆን ተጨማሪ ሌሎች ጥርጣሬዎች፣ የአሰኮ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ፣ የሚሊሻ ዘርፍ ኃላፊ፣ አስተዳዳሪና ምክትል መከላከያ ከገባ በኋላ በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

ሁለት ፖሊሶችና ስምንት ሚሊሻዎች መገደላቸውን እንደሚያውቅ ያስረዳው ከፍያለው፣ ሁለት የቆሰሉ የፖሊስ አባላት እንዳሉም አመልክቷል። ሚሊሻዎቹ ክርስቲያንና ሙስሊሞች መሆናቸውን አመልክቶ፣ ቀደም ባሉት ጊዜያት ሙስሊሞችም መገደላቸውን አስታውሷል። አሁንም ከተገደሉት ውስጥ ሙስሊሞች እንዳሉበት አስታውቋል። ከነዋሪዎች በእሱ መረጃ ማምለጥ ያልቻሉ ስምንት ሰዎች ተገድለዋል።

በተደጋጋሚ በአካባቢው የሚደርሱ ጥቃቶችን አስመልክቶ የተሳሳተ መረጃ ወደ ማዕከል እንደሚላክ መረጃ እንዳላቸው ያመለከተው ከፍያለው፣ የአሁኑ ጥቃት ሊሸሸግ ያልቻለው ቤተ ክርስቲያን በመቃጠሉ እንደሆነ አመልክቷል። እሱ ተፈናቅሎ ካረፈበት ኢሬቻ በግምት ሰላሳ ደቂቃ የእግር መንገድ ርቀት ላይ በምትገኘዋ ጨፌ በተባለች ትንሽ ከተማ የተወለዱት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ስለ ደረሰው ግድያ ከቤተሰቦቻቸው ተደውሎ እንደተነገራቸው፣ ከዛም ወዲያ እሳቸው ባደረጉት ሪፖርትና ዜናው በስፋት በመሰራጨቱ መከላከያ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም አሰኮ ገባ።

መከላከያ አሰኮ እንደገባ ወዲያውኑ ወደ ጠለታ እንዳያመራ ከታሰሩት መካከል ከብት አርደው መከላከያው እረፍት እንዲያደርግ፣ ችግሩ መብረዱን ጠቅሰው ምግብ ይጋብዛሉ። እንደ ከፍያለው መረጃ ይህ የተደረገው የሸኔ ኃይሎች የዘረፉትን ሀብት ይዘው፣ ከብቶቹን እየነዱ ለመሄድ ጊዜ ስለሚያስፈልጋቸው ይህንኑ ለማመቻቸት ነው።

መከላከያ እረፍት ካደረገ በኋላ ወደ ጠለታ ሲያቀና የኦነግ ሸኔ ኃይሎች ወደ ቢዩ አቅንተው ጫካ ውስጥ ገብተዋል። “ከዚያ መከላከያ ምን አደረገ?” በሚል ለተጠየቀው “አላየሁም፣ አሁን ጠለታ አይደለሁም። እዚያ ካሉ እንደሰማሁት መከላከያ ከቦ እየመታቸው ነው የሚባል ነገር አለ” ሲል ከፍያለው ያስረዳል።

ከአሰኮ በላይ “ደጋ” በሚባለው ቦታና ኢሬቻ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን የማደራጀትና የማስታጠቅ ሥራ እንደተሠራ ያመለከተው ከፍያለው፣ ፋኖ አደረጃጀቱን ወደተጠቀሱት አካባቢዎች ማስፋቱ ውሎ አድሮ ሌላ ችግር እንዳያመጣ ሥጋት አለው።

ዘመነ ካሴ በቲክቶክ ካሰራጨው ጥሪ በተጨማሪ በስልክ እንዲደራጁ ያነጋገራቸው እንዳሉ የጠቀሱት ነዋሪዎች “አብረን ከኖርነው ሕዝብ ጋር ደም እንዳንቃባ ፈርተናል። ምክንያቱም ሕዝቡ ምንም አላደረገም። የሚገድሉን ሸኔዎችና ከነሱ ጋር ግንኙነት ያላቸው ናቸው” ሲሉ ሥጋታቸውን ገልጸዋል።

መከላከያ ጠለታ ላይ መሥፈሩን ካጠናከረና መልሶ ማቋቋም ከተደረገ ሕዝቡ ወዲያው እንደሚያገግም የሚናገረው የጠለታ ነዋሪ፣ እንደ ሥጋት የሚያስቀምጠው አንድ ትልቅ ጉዳይ ቢኖር የአካባቢው አስተዳደር የጸዳ ስለመሆኑ ነው።

“ሙስሊም ወንድሞቻችን ከኛ ጋር ሲገጥሙ ስማቸውንና ማንነታቸውን ሪፖርት የሚያደርጉ ስላሉ፣ በሥጋት የማያናግሩን አሉ” የሚለው ከፍያለው፣ ይህ የሚያሳየው የአስተዳደሩ መዋቅር ከሸኔዎቹ ጋር የተስማማ መሆኑን እንደሆነ ይገልጻል። ስማቸውን ያልገለጹ አንጋፋ አባት “አዝናለሁ። አብሮ የበላ፣ የጠጣ፣ የተጋባ፣ የተዋለደ፣ ክፉና ደጉን አብሮ ያሳለፈ ሕዝብ በዚህ ደረጃ ጥርጣሬ ላይ ጥለውታል። አስተዳደሩ ጤነኛ ከሆነ ሰብስቦን እርስ በርስ ብንነጋገር የድሮውን ፍቅር እንመሰርታለን” ብለዋል። አክለውም “ሩቅ ካለው መንግሥት ይልቅ አጠገባችን ባለው አስተዳደር እጅ ላይ ነው ቁልፉ” ብለዋል።

አዲስ ሪፖርተር ያጣራው እውነት ይህን ይመስላል። የአቶ ጌትነት ወርቁ “ግልጽ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ” ሲሉ በፌስቡክ ገጻቸው ያሰራጩት ደብዳቤ መነሻና መድረሻ እንደ አስተያየት የግላቸው ቢሆንም፤ ቂም፣ ሴራ፣ ከዚያም በላይ የድህረ ምርጫ የትርምስ ዕቅድ ማረገዛቸውን ግልጥ አድርጎ ያሳያል።

የደብዳቤያቸው መነሻ የአርሲ ጠለታ የሽብር ጥቃት ነው። ጥቃቱን ያደረሱት እነማን እንደሆኑ በሰላባዎቹ በይፋ ተገልጿል። ለእሳቸው ይህንን አካል በግልጽ ቋንቋ ማውገዝ ዋነኛውን አጀንዳቸውን ስለሚያስትባቸው “አህያውን ትቶ ዳውላውን” እንዲሉ ሆኗል።

ተበዳዮቹ እንዳሉት በመንግሥት የበታች መዋቅር ላይ ችግር መኖሩን ማመላከትና፣ በደፈናው መንግሥት “የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮችን ሊያጠፋ የጄኖሳይድ ትነትና ሰባተኛው ደረጃ ላይ ደርሷል” ማለት ዝም ብሎ የሚታይ ሳይሆን በሕግም የሚያስጠይቅ፣ ለተበደሉትም የማይጠቅም ነው። ይልቁኑም የግብፅ፣ ኤርትራና እነሱ ያደራጇቸው ቡድኖች ዓላማን ከተማ ተቀምጦ ማራመድ ነው።

ትብብር ለአንድነትን በመወከል በየካ ክፍለ ከተማ ለምርጫ ተወዳድረው የነበሩት የእናት ፓርቲ አባልና የትብብሩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌትነት ወርቁ፣ በአርሲ የተከሰተውን አሳዛኝ የንጹሃን እልቂት መነሻ በማድረግ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፌስቡክ ገጻቸው የላኩት ደብዳቤ፣ የድህረ-ምርጫ የትርምስ ዕቅዶችን (Post-Election Destabilization Plan) ፍንጭ የሚሰጥ ስልታዊ ማኒፌስቶን የማስተዋወቅ የኮድ ቅስቀሳ ነው።

የ“ትብብር” የምርጫ ተሳትፎ ምሥጢር እና የዳያስፖራው ኃይል ሚና

አቶ ጌትነት ወርቁ እና መሰል የትብብር ፓርቲ አባላት ለምርጫ ለመወዳደር የገቡት በዓላማ እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲነገር የቆየ ቢሆንም፣ ምርጫው ከተጠናቀቀ በኋላ ግን የተሸሸጉት የፖለቲካ ሴራዎች ይፋ እየሆኑ መጥተዋል። ምርጫ ገብተው ውጤቱን ከተረዱ በኋላ ማፈግፈጋቸውን የቅንጅቱን አካሄድ በመተቸት ከውስጣቸው ተቃውሞ ያሰሙና አካሄዱ የአገር ብሔራዊ ጥቅምን አሳልፎ የሚሰጥ፣ ተቀባይነት የሌለው አካሄድ መሆኑን ያመለከቱ አሉ።

በምርጫው ክርክር ወቅት አቶ ጌትነትን ጨምሮ የትብብሩ መሪዎች የሚወዳደሩት መንግሥት ለመመሥረት እንዳልሆነ ሲናገሩ መሰንበታቸው ይታወሳል። “የፈለገውን ያህል ወንበር ብናገኝ መንግሥት ለመመሥረት አንችልም” ብለው በሚዲያ መናገራቸው፣ ስብስቡ ለምን ወደ ምርጫ እንደገባ ትልቅ ጥያቄ ሲያስነሳ ቆይቷል። ሽንፈትን በራሳቸው ላይ አውጀው የተነሱት የትብብር ለአንድነት ስብስቦች “ውድቀትን ቀድመው ካወቁ ለምን ወደ ምርጫ ገቡ?” በሚል ለሚነሳባቸው ግራ የመጋባት ጥያቄ ምላሽ የላቸውም።

በውጭ ሀገር የሚገኙ፣ ከግብፅና ከኤርትራ ጋር የሚሠሩ እንዲሁም የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፈው የሰጡ የጥፋት ኃይሎች “ባንዳዎች” አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች ለተካተቱበት የትብብር ጥምረት፣ ለኢሕአፓና ለእናት ፓርቲ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ አድርገውላቸው እንደነበር መረጃዎች አሉ። በተለይ ራሱን ከሃይማኖት ክንፉ ጋር አያይዞ ከሞተበት የተነሳው ኢሕአፓን ጨምሮ በጓሮ ገንዘብ ይደርሳቸው የነበረው፣ ምርጫውን (Delegitimize ማድረግ) በሚል በተያዘው ዕቅድ መሠረት በአገር ውስጥ ሕጋዊነትን ተላብሰው እንዲሠሩ መሆኑን ገንዘቡን ከሚያቀርቡላቸው የሻዕቢያ ወኪል አንደበት በተደጋጋሚ በግብረኃይል ስብሰባ ላይ የተረጋገጠ ስለመሆኑ መዘገቡ አይዘነጋም።

ገንዘቡ የተሰጠበት ዋና ውልና ስምምነት፤ ምርጫው ሲቃረብ “በሀገሪቱ ለመወዳደር የሚያስችል አስቻይ ሁኔታ የለም” በሚል ሰበብ ፓርቲዎቹ ራሳቸውን ከምርጫው እንዲያገለሉ ማድረግ ነበር። ዓላማውም በሻዕቢያና በነሱ ቋንቋ ምርጫውን “ዲሌጂቲማይዝ” (ሕገወጥ) ማስባል ነበር። ይሁን እንጂ የታሰበው ሳይሆን ቀርቶ እነ አቶ ጌትነት፣ አቶ አብርሃም እና እመቤት ሚሥጥረ ሥላሴ በፓርቲያቸው ውስጥ በድምፅ ብልጫ ተበልጠው ወደ ምርጫው ገቡ። ይህንን ተከትሎ የውጭው ኃይል እጅግ በመቆጣት “ካዳችሁን፤ የወሰዳችሁትን ብር ይፋ በማድረግ እናጋልጣለን” በሚል ከፍተኛ የማስፈራሪያና የስድብ ናዳ አውርዶባቸዋል። በተለይ የኢሕአፓ አመራሮች ‘አንከር’ በተባለው የዩትዩብ ቻናል ላይ በመሳይ መኮንን እጅግ የከፋ ውርጅብኝ ወረደባቸው።

“ሕዝባዊ እምቢተኝነትን የማቀጣጠል” እና አገር የማተራመስ ስልት

በደረሰባቸው ከፍተኛ ወቀሳና ማስፈራሪያ የተጨነቁት የፓርቲው አመራሮች፣ የዳያስፖራውን ኃይል ለማረጋጋትና የገቡትን ውል በሌላ መንገድ ለመፈጸም ቃል ገቡ። የብሉይ መጽሐፍ ሊቅ የሆኑት የኢሕአፓ መሪ አቶ አብርሃም ሃይማኖት “ከምርጫው በኋላ የጠራ አቋም ይዘን ሕዝባዊ እምቢተኝነትን እናቀጣጥላለን” ሲሉ ለመሳይ መኮንን ማሉ። አደባባይ አውጥቶ ላበሻቀጣቸው መሳይ፣ የሃይማኖት ክንፉ ባልደረባ የሆኑት አቶ አብርሃም ቃል ገቡ።

መሳይ መኮንን እና የሻዕቢያ ወኪሎች የሚያውቁት የድህረ ምርጫ እንቅስቃሴ፣ ሕዝባዊ አመፅ ለማቀጣጠል የተመረጡትን ዋና መንገዶች የዘረዘረ ነው። በሀገሪቱ ውስጥ ዕልቂትና ፍጅት እንዲኖር ማድረግ፣ ዜጎች መንግሥት አልባ ሀገር ውስጥ እንዳሉ እንዲሰማቸው በፕሮፓጋንዳ ማጣደፍ፣ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ላይ “መንግሥት የጥፋት እርምጃ ጀምሯል” የሚል አደገኛ ቅስቀሳ ማድረግ ናቸው። በአርሲ የተከሰተውን አሳዛኝ ክስተት ለዚህ እኩይ ፖለቲካዊ ዓላማ ዋና ግብዓት አደረጉት።

እዚህ ላይ አቶ ጃዋርና አቶ ፋንታሁን ዋቄ ካለፉት አራት ወራት ጀምሮ የጠበቀ ግንኙነት መጀመራቸውን ማንሳት ግድ ይላል። የሞዐ ተዋሕዶ መሪና በዚሁ የሃይማኖት ክንፍ ውስጥ “ተወለደ” የተባለውን መስቀል የሚያጠልቅ የፋኖ አደረጃጀት “የመሠረትነው እኛ ነን” የሚሉት መምህር ፋንታሁን፣ ለምንና ምን ፈልገው ከአቶ ጃዋር ጋር ገጠሙ? ወይም በዘመኑ ቋንቋ “ጽምዶ” መሠረቱ? የሚለውን ጥያቄ ዜጎች ሊመረምሩት እንደሚገባ ለማመላከት እወዳለሁ።

ከዚሁ ጋር ሊነሳ የሚገባው ቁልፍ ጉዳይ የአርሲውን “የሽብር ወንጀል” በሌሊት ቀድሞ ይፋ ያደረገውና “መንግሥት ኦርቶዶክሳውያንን ጨረሰ” በማለት ያሰራጨው አቶ ጃዋር መሐመድ መሆኑ፣ ምን ሊያስተምረንና ሊነግረን እንደሚችል አብሮ ማሰቡ አግባብ ይሆናል። “ጃዋር ለክርስቲያኖች መቆርቆሩ የክፍለ ዘመኑ ምርጥ ቀልድ ነው” ያሉም አሉ።

የአቶ ጌትነት ወርቁ ደብዳቤ አምስት አደገኛ ነጥቦች ትንተና

አቶ ጌትነት ወርቁ በአርሲ የተከሰተውን ክስተት ተገን በማድረግ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የጻፉት ግልጽ ደብዳቤ፣ በሀገሪቱ ያለውን የፖለቲካ እና የብሔር/ሃይማኖት ሁኔታ መነሻ በማድረግ ስውር አጀንዳን ለማስፈጸም የቀረበ መሆኑን የሚከተሉት 5 ነጥቦች ያረጋግጣሉ፦

  1. የፖለቲካ ሽንፈትን በብሔርና ሃይማኖት ካባ የመሸፈን ስልትደብዳቤው በምሥራቅ አርሲ የተከሰተውን አሳዛኝ የንጹሃን እልቂት ፍጹም ፖለቲካዊ በሆነ መነጽር ብቻ ለመተርጎም ይሞክራል። አራት ፓርቲዎች በጋራ ተሸንፈው፣ በምርጫ ኮሮጆ ማሸነፍ ያቃተው ኃይል የሕዝብን ስሜት የሚኮረኩሩ አጀንዳዎችን በመቅረጽ የከሰረውን የፖለቲካ ካፒታል ለመመለስና የበቀል እርምጃ ለመውሰድ የንጹሃንን ሕመም ተገን ማድረጉን ያሳያል።
  2. ማኅበረሰባዊ እልቂትን የመጋበዝ አደገኛ “የዘር ማጥፋት ደረጃዎች” ትንተናጸሐፊው በደብዳቤያቸው የዘር ማጥፋት (Genocide) ደረጃዎችን በመጥቀስ “አሁን ያለንበት ደረጃ 7 ላይ ነው፣ ወደ ደረጃ 8 (ሙሉ እልቂት) እየተንደረደርን ነው” ማለታቸው፣ ሕዝብን ለማረጋጋት ሳይሆን በሕዝቡ ውስጥ ፍጹም ተስፋ መቁረጥንና የፍርሃት ሥነ-ልቦናን መፍጠር ነው። ይህም ዜጎች “ሊጠፉ ነው” በሚል የህልውና ሥጋት ለግጭትና ለጦርነት እንዲነሳሱ የሰላም አማራጮችን ሙሉ በሙሉ የመዝጋት አደገኛ የፕሮፓጋንዳ ስልት ነው።
  3. የመንግሥትን መዋቅር ሙሉ በሙሉ የመፈረጅ ስውር አጀንዳጸሐፊው “ሰንሰለቱ ከጎጥ እስከ ክልል የተዘረጋ ነው” በማለት ሙሉ የመንግሥትን መዋቅር ከተኳሾችና ከአሸባሪዎች ጋር አንድ አድርገው ፈርጀዋል። የዚህ አካሄድ ዓላማ ሕዝቡ በጸጥታ አካላት ላይ እምነት እንዳይኖረው በማድረግ፣ ሕጋዊውን መዋቅር በማፍረስ ሀገሪቱን ወደለየለት የእርስ በርስ ጦርነትና የመንግሥት አልባነት (Anarchy) ሥርዓት ውስጥ መክተት ነው።
  4. “የጥቃት ተጋላጮችን ማስታጠቅ” የሚለው የመፍትሔ ሐሳብ አደገኝነትጸሐፊው ከመፍትሔዎች አንዱ አድርገው ያቀረቡት “የጥቃት ተጋላጮችን በሕጋዊ መልኩ ማስታጠቅ” የሚለውን ነው። መንግሥታዊ ካልሆነ መዋቅር ውጪ ሕዝብን በብሔርና በሃይማኖት እየለዩ ማስታጠቅ፣ የሲቪል ማኅበረሰቡን ቀጥተኛ የጦርነት ተሳታፊ በማድረግ ሀገሪቱን ወደማያበራ የርስ በርስ እሳት ውስጥ መክተት ማለት ነው።
  5. በሐዘን ስም የተሸፈነ የትርምስ ስትራቴጂ (Post-Election Plan) እና የመረጃ ማዛባትየደብዳቤው ማሳረጊያ ላይ የተጠቀሱት ማስፈራሪያዎች ፍንጭ የሚሰጡት ጽሑፉ የሰላም ጥሪ ሳይሆን የትርምስ ማስጠንቀቂያ መሆኑን ነው። ጉዳዩን ወደ ሃይማኖት ፀብ በመቀየር ሀገርን የማፍረስ ድብቅ ዕቅድ (Post-election destabilization plan) መኖሩን በግልጽ ያሳያል። በተጨማሪም የአቶ ጌትነት ደብዳቤ ዓላማው ፖለቲካዊ የበቀል አመፅ ማነሳሳት በመሆኑ፣ በቦታው የተከሰተውን እውነተኛ መረጃ ሆን ብሎ አዛብቶታል ወይም ደብቆታል። በአርሲ የተፈናቀሉና የሞቱ ዜጎች የቤተሰብ አባላትና ዘመዶች “ኦነግ ሸኔ ገደለን፣ ቤታችንን አቃጠለ፣ ንብረታችንን ዘረፈ” በማለት በግልጽ የተናገሩ ሲሆን፣ በዕለቱ የጥፋት ቡድኑን ለመከላከል ሲሉ የፖሊስና የሚሊሻ አባላት ጭምር ሕይወታቸውን መስዋዕት ማድረጋቸውን በአደባባይ መስክረዋል።

አቶ ጌትነት ግን ይህንን እውነት ወደ ጎን በመተው፣ ጥቃቱን የመንግሥት መዋቅር እንደፈጸመውና የሃይማኖት ማጥፋት ዘመቻ እንደሆነ አድርገው ማቅረባቸው፣ የፖለቲካ አጀንዳቸውን ለማስፈጸም የፈጠሩት የፈጠራ ትረካ መሆኑን ያጋልጣል። ከጠለታ በስተቀር በኢሬቻ፣ አሰኮ፣ ደጋ ወዘተ በሰላም እየኖሩ ያሉትን ዜጎች የዘነጉትም ለዓላማቸው ስለማይሆንላቸው ነው።

የአቶ ጌትነት ወርቁ ግልጽ ደብዳቤ በንጹሃን ደምና ሐዘን ላይ ተመስርቶ የተጻፈ ቢሆንም፣ ዋና ግቡ ግን ከምርጫ ሽንፈትና ከውጭ ኃይሎች መደናገጥ ለመውጣት ሕዝብን ከሕዝብ፣ ሕዝብን ከመንግሥት ጋር በማጋጨት ሀገራዊ መረጋጋትን ለማደፍረስ የታቀደው የድህረ ምርጫ ዕቅድ ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም። እንደውም ስልታዊ ማኒፌስቶ ነው። ደብዳቤው የመፍትሔ አካል ሳይሆን፣ ራሱ ችግሩን ይበልጥ አጋግሎ የሃይማኖትና የብሔር ጦርነት ለመጫር የተነደፈ አደገኛ ዕቅድ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእንዲህ ዓይነት ስውር የድህረ-ምርጫ የትርምስ ሴራዎች ራሱን ሊጠብቅ ይገባል። ሴራው መልኩን እየቀያየረ በሳይበሩ ሠራዊት ሚዲያ በኩል መሰራጨቱ ቀጣይ ነውና ጥንቃቄ ይበጃል።

“የወለጋ አማራ ተደራጅቶና ታጥቆ ጄኔራል እስከመግደል ደርሷል” ሲሉ የሚደመጡት አቶ ጌትነት፣ የአገር መከላከያ ላይ እዚያም እዚህም እያደፈጡ ጥቃት የሚያደርሱትን በማድነቅ፣ አርሲም ይህ መሆን እንደሚገባው መወትወት ከጀመሩ መሰንበታቸውን አብረዋቸው የሚሠሩ እየገለጹ ነው። እናም ይህ አካሄዳቸው አይጠቅማቸውምና ራሳቸውን ቢያርሙ መልካም ነው!

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ2.3 ትሪሊዮን ብር በላይ ረቂቅ በጀት አጸደቀ

አዲስ ሪፖርተር ዜና አዲስ አበባ — የሚኒስትሮች ምክር ቤት...

ካይሮ ያቀኑት ኢሳያስ “ግብፅ በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የምታደርገውን ጥረት አደንቃለሁ”

ኢዲስ ሪፖርተር ካይሮ — የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በትላንትናው...

የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አንደበት የቆለፈው የትራምፕ መመሪያ ተቃዋሚዎች ተስፋ አስቆርጧል፤ አሜሪካ ስለምርጫው ለምን ዝም አለች?

አሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፣ የአገሪቱ ዲፕሎማቶች በሌሎች አገራት...