መንግሥት በሕገ ወጦች፣ በሌብነት እና የኢኮኖሚ አሻጥር በፈጸሙ ላይ የወሰደውን እርምጃ ይፋ አደረገ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የሀገር በቀል ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ለማደናቀፍ፣ የሀገር ሀብት በማመዝበር እና በኢኮኖሚ አሻጥር ላይ በተሰማሩ አካላት ላይ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ መውሰዱን አስታውቀዋል።

ምርት በማከማቸት ሰው ሠራሽ እጥረት የፈጠሩ 13 አቅራቢ ድርጅቶች ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሲሆን፣ ከ7 ሺህ በላይ ሕገ-ወጥ የንግድ ድርጅቶችና መጋዘኖች ታሽገዋል ብለዋል። በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርና በጥቁር ገበያ የተሳተፉ 169 ግለሰቦች፣ እንዲሁም ከባንክ ደንበኞች አካውንት ገንዘብ ያጭበረበሩ 36 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

7 የክሪፕቶ ካረንሲ መተግበሪያዎች የታገዱ ሲሆን፣ የውጭ ምንዛሬ ያላስገቡ 29 ላኪዎች ላይ ሕጋዊ ተጠያቂነት ሰፍኗል። ግብር ያጨበረበሩና ሕገ-ወጥ ገንዘብ ያዛወሩ 38 የቤቲንግ ድርጅቶች ታሽገው ባለቤቶቻቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል፤ የባንክ ሒሳባቸውም ታግዷል።

በወርቅ ኮንትሮባንድ የተሳተፉ የመንግሥትና የፀጥታ አመራሮችን ጨምሮ 183 ግለሰቦች በሕግ ተጠያቂ ሆነዋል፤ ሕገ-ወጥ የውጭ ዜጎች ከሀገር እንዲወጡ ተደርገዋል። በሕገ-ወጥ የነዳጅ ንግድና አየር በአየር ሽያጭ የተሳተፉ 38 የመንግሥት አመራሮች እንዲሁም ከ650 በላይ ግለሰቦችና ማደያዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል። ጥራት የጎደለውና ጊዜው ያለፈበት አፈር ማዳበሪያ እንዲገዛ ባደረጉ የግብርና ሚኒስቴር አመራሮች ላይ የወንጀል ተጠያቂነት ሰፍኗል።

ከ36 የዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች ጋር ሕገ-ወጥ የኃይል ሽያጭ ውል የፈጸሙ 4 ከፍተኛ አመራሮች እና ኤሌክትሪክ የሰረቁ አካላት በሕግ እንዲጠየቁ ተደርጓል። በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና ጉቦ መቀበል ወንጀል የተሳተፉ 8 ከፍተኛ አመራሮችና 44 ደላሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የግብር መረጃ በማጥፋትና ሐሰተኛ ደረሰኝ በማወራረድ የተጠረጠሩ 109 አካላት ተለይተው 91 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ሚኒስትሯ አክለውም ኅብረተሰቡ ሙስናን በማጋለጥና ከሕገ-ወጦች ጋር ባለመተባበር ከመንግሥት ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

አሜሪካ “ከኤርትራ ጋር አላሴርንም” የማሳድ ቡሎስ ተደጋጋሚ ማስተባበያ ለምን?

አዲስ ሪፖርተር | የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአረብና የአፍሪካ...

የሰኔ 15 ግድያ የዛሬ የአማራ ክልል ትርምስ መነሻ

 “ዓብይ አህመድን ገዳይ አድርጎ ገዳይንና ሟቸን እኩል ማጀገን በሚል...

የትግራይ የፖለቲካ አቅጣጫና የቀጠናው ጂኦፖለቲካ፤ የግብጽ፣ ሱዳንና ሻዕቢያ የ”ጽምዶ” ቃል ኪዳን ይፈጸማል?

ለአዲስ አበባ የሚወረወሩ ወጥመዶች፡ ድርጅቱ ባለው የዲጂታል ሰራዊት እና...