“ፋኖንና ከኢሳያስ ጋር ያሸማገሉት ሻለቃ ዳዊት ናቸው፤ ዓላማው አገረ መንግስቱን በማፍረስ ኢትዮጵያን የጎበዝ አለቆች እንዲቀራመቷት ማድረግ ነው”

Date:

ኢትዮጵያ መከላከያዋ እንዲፈርስ በሚወጠኑ ውጥኖች ቀዳሚ ውስጥ መሪ ተዋናይ ናቸው። ከረሃብተኞች ዘርፈው በመኮብለል የቆሸሸ ታሪክ አላቸው። በቅርብ ዓመታት የፋኖ መሪና የውጭ ግንኙነት ኃላፊ በመሆን ለሌላ ዙር ሴራ ሲንቀሳቀሱ ነበር። የቀድሞ የአፋብን አመራር የነበሩት ጌራ ወርቅ ይፋ እንዳደረጉት የሻዕቢያውን መሪ ኢሳያስ አፉወርቂንና ፋኖን ያደራደሩት እኚሁ ጉደኛው የሰማኒያ ዓመቱ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ ናቸው።

የኢትዮጵያ አገር መከላከያን ማፍረስ ወይም ለማፍረስ የሚደረጉ ሙከራዎች ሁሉ ኢትዮጵያን መንግስት አልባ የማድረግ የቆየና የማይቀየር ዕቅድ ነው። ይህ ዕቅድ የኢትዮጵያ ቋሚ ጠላቶች ሲሆን አስፈጻሚዎቹ ደግሞ ራሳቸውን የሸጡ ባንዳዎች እንደሆኑ በርካታ የጽሁፍና የምስክርነት ማስረጃዎች አሉ። ይህን ያጣቀሱት አቶ ጌራ ወርቅ “ሻለቃ ዳዊት ፋኖንና ኢሳያስን አደራድረው፣ አብረው እንዲሰሩ አድረገዋል” ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

የግንቦት 8 ቀን 1980 ዓ.ም የተሞከረው መፈንቅለ መንግስት በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቁስል ጥሎ ያለፈ ክስተት ነው። ብዙዎች “እንዲከሽፍ ታስቦ የተቀነባበረ” ወይም “የታወቀ የሞት ወጥመድ” ብለው የሚጠሩት ሴራ አባቱ ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ናቸው። ከዚህ በደም የጨቀየ ታሪካቸው ወደኋላ በመሄድ ሻለቃ ዳዊት ከንጉሱ መወገድ ጀምሮ ተሳታፊ እንደሆኑ ያብራራሉ። በተለይም እንዲከሽፍ ተደርጎ በተቀነባበረው የ1980 ዓ.ም መፈንቅለ መንግስት የነበራቸውን ሚና በማጉላት “ኢትዮጵያ እንድትፈርስ የሚሰሩ” ሲሉ ሴራቸውን አጋልጠዋል።

ከሱዳን፣ ከኤርትራ፣ ከግብጽና ከወያኔ ጋር የተጀመረው ግንኙነት እና ይህንኑ ተከትሎ ትግሉ በመጠለፉ ስንጥቅ በመፈጠሩ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ከገቡት ኮሎኔል ማንነገረው መለሰ፣ኢንጂነር አየነው አስፋው፣ ሃምሳ አለቃ ፍቅሩ ሙልዬ ጋር በመሆን ከኢቢሲ በጋር በተደረገ ቃለ ምልልስ አቶ ጌራ ወርቅ “ሻለቃ ዳዊት አሸማጋይ ሆነው መጡ” በማለት የሚያውቁትን መስክረዋል።

በግንቦት ወር 1980ዓም ወታደራዊ መኮንኖች መፈንቅለ መንግሥት ሲያቅዱ የውጭውን ሤራ ሲመሩ የነበረው ዳዊት ራሳቸው እንደነበር በተደጋጋሚ ሲናገር የነበረው ሃቅ ቢሆንም በአንድ ወቅት ከኢሳት ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ ላይ “ሱዳን እመላለስ ነበር” በማለት የዕምነት ቃላቸውን ሳያስቡት ሰጥተዋል። ። 

ደርግ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ በ1971 ዓ.ም “የመለዮ ለባሾች ንቅናቄ” የሚል እንቅስቃሴ ተጀምሮ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ጌራ ወርቅ፣ ሻለቃ ዳዊት በከፍተኛ ጉትጎታና አማላጅ ንቅናቄውን እንደተቀላለቀሉ ያስታውሳሉ። ከረሃብተኞች ጉሮሮ ዘርፈው ከኮበለሉ በኋላ ይህንኑ እንቅስቃሴ በመከታተል መጨረሻ ላይ የኢትዮጵያን ምርጥ ጄኔራሎች እንዳስጨረሱ አቶ ጌራ ወርቅ አስታውቀዋል። እሳቸው ከአዲሱ ይፋ ያልሆነው ታሪክ ጋር እንደ አዲስ አነሱት እንጂ፣ ሻለቃ ዳዊት ከሻዕቢያ ይሰሩ የነበሩ መንታ ሰው መሆናቸው በተለያዩ ባልደረቦቻቸውና በሚያውቋቸው በተደጋጋሚ ተመስክሯል።

እንዲከሽፍ ተደርጎ ከተቀነባበረ በኋላ የኢትዮጵያን ውድ ጄኔራሎች የበላው መፈንቅለ መንግስት ውስጥ ተባባሪ መስለው የገቡት ሻለቃ ዳዊት እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ለኮሎኔል መንግስቱ ያሳልፉ እንደነበር አቶ ጌራ ወርቅ አመልክተዋል። ይህን ያደረጉት መፍለንቅለ መንግስቱ ቢሳካ በኢትዮጵያ ሰላማዊ ሽግግርና ጠንካራ አገረ መንግስት እንደሚገነባ ስለሚታወቅ ሻለቃ ዳዊት ከሻዕቢያ፣ ከወያኔና ሻዕቢያን ካዋለዱት አካላት ተልዕኮ በመውሰድ ሂደቱን የለውጥ አራማጅ መስለው በደም እንዲቋጭ አስደረጉ።

በዚሁ የክህደት ተግባራቸው መረጃ አሳልፎ በመስጠት መኮንኖች መፈንቅለ መንግስቱ በጀመሩ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በመከላከያ ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ እያሉ በደህንነት ኃይሎች ተረሸኑ። በድምሩ ሃያ ስምንት የሚሆኑ እውቅ የኢትዮጵያ መኮንኖች የተገደሉ ሲሆን፣ ይህ እርምጃ የኢትዮጵያን ጦር ያለ መሪ በማስቀረት ለደርግ ውድቀት ትልቅ ምክንያት ሆኗል። እነዚህ መኮንኖች በአብዛኛው በምዕራባውያንና በሶቪየት ህብረት ወታደራዊ አካዳሚዎች የሰለጠኑ፣ ከፍተኛ ልምድ የነበራቸው “የኢትዮጵያ ወታደራዊ ምሁራን” ተብለው የሚታወቁ ነበሩ። ሻለቃ ዳዊት ይህን ካመቻቹና በስኬት ካጠናቀቁ በኋላ የኢትዮጵያ መከላከያ በዓመቱ “የደርግ” ተብሎ ፈረሰ፣ ባህር ኃይልና አየር ኃይል ተበተነ።

በውቀቱ ብጋዴር ጄኔራል ሰለሞን ከደዳ የመከላከያ ሚኒስቴር የሰው ኃይል አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ፣ ሜጀር ጄኔራል መርዕድ ንጉሴ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም፣ ሜጀር ጄኔራል አመሓ ደስታ የኢትዮጵያ አየር ኃይል አዛዥ፣ ሜጀር ጄኔራል ደምሴ ቡልቶ የሁለተኛ አብዮታዊ ጦር አዛዥ (በአስመራ የተገደሉ) ብጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ብርሃኑ – የባህር ኃይል ጠቅላይ አዛዥ ወዲያው ከተረሸኑት መካከል ነበሩ።

እነ ሻለቃ ዳዊት እንዲከሽፍ አድርገው የሰሩት መፈንቅለ መንግስት ከከሸፈ በኋላ በቁጥጥር ስር ውለው፣ ለአንድ ዓመት ያህል በእስር ላይ የቆዩት ጄኔራሎች በመንግስቱ ትዕዛዝ ተረሸኑ። ሜጀር ጄኔራል ፋንታ በላይ ቀድሞ የአየር ኃይል አዛዥና በወቅቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር የነበሩ ፣ ሜጀር ጄኔራል አበራ አበበ የመከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ መኮንን፣ ሜጀር ጄኔራል ከበደ ጋሻው ፣ሜጀር ጄኔራል ስዩም መኮንን ፣ብጋዴር ጄኔራል ታዬ ባልቻ ፣ብጋዴር ጄኔራል አፈወርቅ ወልደሚካኤል ፣ብጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ትርፌ ፣ብጋዴር ጄኔራል ንጉሴ በቀለ ፣ብጋዴር ጄኔራል ደሳለኝ አበበ ፣ ብጋዴር ጄኔራል እንግዳ ወልደአምላክ ፣ ብጋዴር ጄኔራል ወርቁ ዘውዴ የሚታወሱ ናቸው። የጎጃሙ ጄኔራል ቁምላቸው ሸሽተው ሱዳን በመግባት ከሻለቃ ዳዊት ጋር መገናኘታቸውን ራሳቸው በኢሳት በኩል አስታወቁ፣ ቁምላቸው መፈንቅለ መንግስቱን ወታደር በማሰማራትና ከለላ በመስተት ውጭ ሆነው የማሳለጥ ሚና ወስደው ነበር። ይሁን እንጂ ኃይል ሲጠየቁ ባለማቅረብ ይከሰሳሉ። ሜጀር ጄኔራል ታሪኩ አይኔ ከመፈንቅለ መንግስቱ ጥቂት ቀደም ብሎ የተረሸኑ ሲሆን፣ እንደ ታሪኩ ቀደም ብለው የተረሸኑ ሌላው ሜጀር ጄኔራል ሃይሉ ገብረአማኑኤል የመከላከያ ሚኒስቴር የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ የነበሩ ናቸው።

በዚህ የክህደት አሻራ የሚታወቁት ሻለቃ ዳዊት ለውጡን ተከትሎ አዲስ አበባ እንደ “ጀግና” በመምጣት “ህገ መንግስቱ” እንዲቀደድ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጥያቄ አቅርበው አልሆን ሲላቸው፣ አሜሪካ ሄደው “ኢትዮጵያ የምትፈርስ አገር ናት” በማለት ሰፊ ዘገባ አሰራጩ።

አዲስ አበባ በመጡበት ወቅት እስክንድር ነጋንና መስከረም አበራን እንዲሁም ሌሎች ሴሎችን ተክለው እንደሄዱ ብዙም ሳይቆይ ተሰማ። ትንሽ ቆይተው የአማራ ነጻ አውጪ መሆናቸውን በእነ መሳይ መኮንን ዩቲዩብ አበሰሩ። እስከንድር “የፋኖ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ናቸው” ሲል አስታወቀ። በዚሁ ስም በርካታ ዶላር ሰበሰቡ፣ በተደጋጋሚ ኤርትራ በመመላለስ የሚወርድላቸውን መመሪያ በመያዝ ወደ ኢትዮጵያ ይደፉ ጀመር። አቶ ጌራ ወርቅ አሁን ይፋ ያደረጉት ጉዳይ ፋኖ ሻዕቢያ እጅ የገባው አሁን ሳይሆን ቀደም ሲል ነው።

በኢትዮጵያ ውስጥ ተሞክረው ከከሸፉ በርካታ መልካም አጋጣሚዎች ጀርባ ስማቸው የሚነሳው ሰላዩ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ደጋፊ ለማሰባሰብ ሲሉ እሳቸውና አቶ ታምራት ላይኔ፣ እንዲሁም በመረጃ ቲቪ ባለቤቶች ስፖንሰር አድራጊነት የሽግግር ሰነድም አዘጋጅተው ነበር። ፋኖን ለሻዕቢያ ካስረከቡ በኋላ ትግሉ የአሜሪካ መንግሥት ዕውቅና እንዳለው በማስመሰል የሚዲያ ማስታወቂያ ሲያሰሩ ነበር። ይሁን እንጂ ሰነዱ ለአሜሪካ መንግሥት ከመድረሱ በፊት ሙሉ ዶሴው መንግሥት እጅ መግባቱን ጎልጉል በወቅቱ ዘግቦ ነበር።

ከፍተኛ ገንዘብ ከተሰበሰበ በኋላ “በቃኝ” ያሉት ሻለቃ ዳዊት፣ አሁን ላይ አታላንታ ከከተመው የፋኖ ባለቤት ነኝ የሚል ስብሰብ ጋር አልፎ አልፎ ከጅም መልስ ስብሰባ እንደሚያደርጉ በቅርብ የሚከታተሏቸው ይናገራሉ። አቶ ጌራ ወርቅና በላደረቦቻቸው በጋራ እንዳሉት፣ በፋኖ ውስጥ መሰንጠቅ የተፈጠረው ከዚህ ጊዜ በኋላ ነው። እንደ እነሱ ገለጻ የአማራ ሕዝብ ከኤርትራ፣ ከሱዳን፣ ከግብጽና ከወያኔ የሚያገኘው አንድም ዓይነት ምላሽ የለም። ይልቁኑም አገረ መንግስቱን ለማፍረስ የአገር መከላከያን ለመበተን ያላቸውን የማይቀየር ዕቅድ ተግባራዊ አድርጎ አገሪቱን የጎበዝ አለቆች መፈንጫ ማድረግ ነው።

ለዚህም እንደ ማስረጃ ሲያነሱ ትህነግ ትግራይ ከገባ በኋላ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት አስቀድሞ ያደረገው የአገሪቱን የመከላከያ እንምብርት የሆነውን የሰሜን ዕዝን ማጥቃቱን ነው። ይህ ታስቦበት የአገሪቱን መከላከያ በማፍረስ እንድትበታተን የተያዘውን ዕቅድ ለማስፈጸም ነው።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ቴድሮስ ካሳሁን ለሰዋሰው መልቲሚዲያ 33 ሚሊዮን ብር ከፍሎ በሰላም ፍቺ ማደረጉ ይፋ ሆነ

"ቴድሮስ በማህበራዊ ገጹ እውነቱን ለምን አይናገርም? በስማ በለው በማህበራዊ...

በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል በፓኪስታን ሲካሄድ የነበረው ድርድር ያለ ስምምነት ተበተነ

አዲስ ሪፓርተር— በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል በፓኪስታን አስተናጋጅነት...

ሻዕቢያ ያደራጀው የአመጽ ቀስቃሽ ኮሚቴ ዲያስፖራው ስለፈራ አገር ቤት አመጽ ማስነሳት ቅድሚያው አደረገ

ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ ተጠራ፤ ኢህአፓን ማገዝና ብረት ያንሱ ድርጅቶችን...