አዲስ ሪፖርተር ዜና ዋሽንግቶን ዲሲ – ግብፅ የምትመራውና ሱዳን፣ ኤርትራ፣ ሕወሃት እንዲሁም ፋኖ በዋናነት የሚሳተፉበት “ጽምዶ” የተሰኘው ስብስብ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ በማስነሳቱ፣ አዲስ የጋራ መጠሪያ ስም ለማውጣት መወሰኑ ተሰማ። አዲሱ ስም ኢትዮጵያዊ ስም እንደሚላበስ ታውቋል። አብረው ስለተሰባሰቡት ድርጅቶች ዓላማ ማንሳት እንደማያስፈልግም መመሪያ ተሰጥቷል።
“ጽምዶ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ነው” በሚል ሽፋን መሣሪያ ያነሱ ኃይሎች ኢትዮጵያን አብረው ለመውጋት በትግራይ፣ ሱዳንና ኤርትራ ውስጥ ለመሰባሰብ እየሞከሩ እንደሆነ መረጃዎች ይፋ መሆናቸው አጀንዳ ከሆነ ሰነባብቷል።
የተቃውሞውና የስም ለውጡ መንሥኤ
የስም ለውጡ መረጃ የተሰማው “ጽምዶ” በሚል የመሰባሰቢያ ስም የተገለጹት አገራትና ድርጅቶች በመርህ ደረጃ ኢትዮጵያን የማጥፋት አጀንዳ ያላቸውና ራሳቸውን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል በይፋ ማኒፌስቶ አዘጋጅተው በመንቀሳቀስ የሚታወቁ በመሆናቸው ሕዝብ ከየአቅጣጫው ተቃውሞ በማሰማቱ ነው። ከሕዝብ ተቃውሞ ባሻገር “ጽምዶ” ባቀፋቸው ድርጅቶች ውስጥም የእርስ በርስ መለያየት እየተሰማ ይገኛል።
ሰሞኑን ይህንኑ ስብስብ በሕዝብ ግንኙነት እያገለገለ ባለው መሳይ መኮንን በአንከር ሚዲያ የቀረቡት አቶ አንዳርጋቸው፣ “ዋናው ዓላማ የብልጽግናን መንግሥት መጣል ነው” በማለት የስብስቡን የወደፊት የጋራ ዕቅድና የዓላማ መመሳሰል አሁን ላይ ማንሳት እንደማያስፈልግ በግልጽ አስታውቀዋል። ደጋግመውም “አሁን ላይ ይህ ጥያቄ ሊጠየቅ አይገባም” ሲሉ መመሪያ ሰጥተዋል።
በኤርትራ መንግሥት ጥሪ የኤርትራ ኤምባሲ ጋብዟቸው ወደ ሱዳን ማቅናታቸውን ያስታወቁት አቶ አንዳርጋቸው፣ በሱዳን ኤርትራ፣ ትግራይና ፋኖ እንዳልተወከሉ ሲጠቅሱ “አናሳዎች ብቻ ናቸው የተወከሉት” በማለታቸው ከፍተኛ ወቀሳ ደርሶባቸዋል። አቶ አንዳርጋቸው የዚህ ጥምረት ዋና አርክቴክት እንደሆኑ ስለ እንቅስቃሴያቸው የሚያውቁ አካላት በተደጋጋሚ መናገራቸው ይታወሳል።
“አማራ የለም” በማለት የሚታወቁትና ለሻዕቢያ እንደሚያገለግሉ መረጃ የሚወጣባቸው አቶ አንዳርጋቸው “ጽምዶ የሕዝብ ለሕዝብ ስብስብ ነው” ካሉ በኋላ፣ እዚያው ላይ መልሰው “የብልጽግና መንግሥት ተንበቅብቋል፣ ጽምዶ አስፈርቶታል” በማለት በቅርቡ ኦፕሬሽን እንደሚጀመር አስታውቀዋል።
“የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምዝና አንድነት አደጋ ላይ የሚጥለውንና በመገነጣጠል፣ ‘ወደ ሱዳን እና ሶማሊያ እንካተት’ የሚሉትን አግበስብሰው ጦርነት ለመክፈት የተዘጋጁትን በሙሉ የሚነቅፉ የአማራ ማኅበራት ባነሱት ከፍተኛ ተቃውሞ የጽምዶ ስም ተቀይሮ አዲስ ግንባር እንዲመሠረት ተወስኗል” ያሉት የዜናው ምንጮች፣ “በዋናነት ስሙ የሚቀየረው ሕዝብ በስብስቡ ላይ ያለውን የጎሸ ስሜት ለመቀየርና ፋኖ ‘ከሃዲ ሆነ’ በሚል የተነሳበትን ጠንካራ ትችት ለማለዘብ ነው” ብለዋል። አክለውም አዲሱ ስያሜ ኢትዮጵያነትን የተላበሰ እንደሚደረግ መስማታቸውን አስታውቀዋል
የሚዲያና የፕሮፓጋንዳ ዝግጅት
አዲስ የሚፈጠረው ግንባር በጽምዶ ውስጥ የተካተቱትና ከጀርባ ሆነው የሚያደራጁት የውጭ አገራት ስም እንዲረሳ፣ ምስረታውን አስታኮ ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ሥራ ለመሥራት ከወዲሁ ዝግጅት መደረጉ ታውቋል።
የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ዲሲ ተባባሪ እንዳለው፣ “ጽምዶ” የሚለው ስም እንዲቀየርና በውስጡ የውጭ ኃይሎች እንደሌሉበት የሚያስረዳ ፕሮፓጋንዳ ለመሥራት ሚዲያዎች ተለይተዋል።
ኢኤምኤስ (EMS) በተሰኘው የዩቲዩብ ቻናል “ምንም ድብቅብቅ የለም፣ ማንም ይስማ” በማለት የሻዕቢያ ደጋፊዎች በአገር ውስጥ ካሉት በተጨማሪ ቱርክ፣ ሩሲያ፣ ግብፅ፣ ሶማሊያና ኢራን ጽምዶ ውስጥ እንዳሉበት አዲሱ ስም ይፋ በሚሆንበት ማግሥት ይፋ አድርገዋል።
ቀደም ሲል ከባይቶና ፓርቲ የተባረሩትና አሁን ዶክተር ደብረጽዮን የወጣቶች አደረጃጀት ሰብሳቢ አድርገው የሾሟቸው ክብሮም፣ ሕወሃት አብሮ ከሚሠራቸው አገሮች በተጨማሪ ከአልሸባብ፣ ከየመን ሐውቲ (ሁቱ)፣ ከኢራንና ከመሳሰሉት የሽብር ኃይሎች ጋር እንደሚሠራ በድምፅ ወያኔ በይፋ መናገሩ አይዘነጋም።
“ከመንግሥት መፍረስ በኋላስ?” — የሕዝብ ስጋት
በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ዓላማና ምንም የጋራ አጀንዳ የሌላቸው ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በማበር “ቅድሚያ መንግሥትን እናስወግድ፣ መከላከያን እናፍርስ” በሚል አጀንዳ መሰባሰባቸው፣ “ቢሳካላቸውና መንግሥት ቢፈርስ በኋላ ምን ሊሆን ነው?” የሚል ጥያቄ የኢትዮጵያውያን ሁሉ መልስ የሌለው ጥያቄ ነው።
“የጋምቤላ ነፃ አውጪ ‘ወደ ሱዳን ልጠቃለል’ ይላል፤ የኦጋዴን ነፃ አውጪ ወደ ሶማሊያ፣ የቤኒሻንጉል ነፃ አውጪ ወደ ሱዳን ለመጠቃለል፣ ኦነግ ለመገንጠል፣ የቅማንት ነፃ አውጪ ከአማራ ክልል ተለይቶ ራሱን ከሱዳን ወይም ከትግራይ ጋር ለመወላለቅ፣ የአገው የራሱን ክልል መሥርቶ ከትግራይ ጋር ለመሆን፣ የአፋር ነፃ አውጪ ድርጅትም በተመሳሳይ ነፃ ለመውጣት የሚታገሉ ሲሆን፣ የሚያደራጃቸው ሕወሃት ደግሞ የያዘውን ይዞ አገር በመሆን ከሱዳን ጋር መግጠም ዋና አጀንዳቸው ነው” የሚሉ አካላት፣ የአማራ ሕዝብ ወኪል ነን የሚሉ አካላት በዚህ ስብስብ ውስጥ ገብተው ለአማራ ሕዝብ ምን ውጤት እንደሚያስገኙለት በግልጽ ተጠይቀው ምላሽ ሲሰጡ አይሰማም።
ከመንግሥት ወገን ስብስቡ የሚታወቅ አቅምና አደረጃጀት ስላለው ሥጋት ባይሆንም፣ ዓላማውን ወደ መሬት ለማውረድ አሰባሳቢዎቻቸው የሞከሩ ዕለት የከፋ ዕርምጃ እንደሚወስድ “ዓለም ይወቅልኝ” ከማለት የዘለለ ያለው ነገር የለም።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






