15 ሜትር ኩዩብ፣ አንድ መኪና አሸዋ 90 ሺህ ብር ሆነ፤ ምክንያቱ ነዳጅ ነው

Date:

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይበልጥ ፈታኝ ከሆነው የነዳጅ ችግር ጋር በተያያዘ የኮንስትራክሽን ግብዓት ዋጋ ላይ ከ20 እስከ 40 ሺሕ ጭማሪ መታየቱን ህንፃ ገንቢዎች እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ግብዓት አቅራቢዎች እና ማዕድናት ሃብት ሥራ አሰሪ ባለሃብቶች ማህበር አስታውቀዋል።

ከዚህ ቀደም ከ60 እስከ 70 ሺሕ ብር ይሸጥ የነበረው አንድ መኪና አሸዋ አሁን ከ12ዐ ሺሕ እስከ 130 ሺሕ ብር መግባቱን ጠቅሰው ማህበራቱ የተናገሩት ለኢክቫህ ነው። ይህ ጭማሪ የተጋነነና ጊዜን ጠብቆ ዝርፊያ መፈጸም እንደሆነ ዜናውን የሰሙ አመልክተዋል።

ከአሸዋ ባሻገር፣ ከወራት በፊት 60 ሺሕ ብር ሲሸጥ የነበረው አንድ መኪና ጠጠር አሁን ከ85 ሺሕ ብር በላይ እየተሸጠ ነው። የግንባታ ድንጋይም በተመሳሳይ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል። በሺዎች የሚቆጠር ጭማሪ አሳይቷል። የሲሚንቶ ዋጋም ሶስት እጥፍ ተሰቅሏል።

ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ግብዓት አቅራቢዎች እና ማዕድናት ሀብት ሥራ አሰሪ ባለሃብቶች ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኃይለማርያም ገቢሳ፣ ” በትክክል ጭማሪ አለ። የዛሬ ሦስት ዓመት 12 ሺሕ ይጫን የነበረው 15 ሜትርኩዩብ አንድ መኪና አሸዋ ዛሬ ወደ 90 ሺሕ ብር ገብቷል ” በማለት ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

ለዚህ ከፍተኛ የዋጋ ንረት “የነዳጅም እጥረትና የቢሮክራሲ ሰንሰለት” ዋና ተጠቃሽ እንደሆኑ ኃላፊው አስረድተዋል። እንደ ሰንሰለት የተያያዘው ሰው ሰራሽ ችግር ከነዳጅ እጥረርቱ ጋር አንድ ላይ ተዳምሮ፣ አምራች ያልሆኑትም ዋጋ እንዲጨምሩ መንስኤ እንደሆነ አመልክተዋል። የሲሚንቶ ዋጋ ከአምራች ዋጋው ሳይጨምር የገበያው ዋጋ መናሩ በሰንሰለት የሚፈጸም ሌብነት ስለመኖሩ ማሳያ እንደሆነ ለሚናገሩ የኃላፊው መግለጫ ምስክር ሆኗል።

የመንግስት መዋቅሮች ቸግሩን እያሰፉትና በግል ሳይቀር ተቧድነው መጠቀሚያ እንዳደረጉት በስፋት መረጃ እየወጣ ነው። ምርቱን በሚያመላልሱት ተሽከርካሪዎች ላይ በየሚዛን ጣቢያውና በሌሎች አግባቦች ያለው አሰራርና የክፍያ ጫና ተጠቃሚውን ህብረተሰብ ለከፋ ችግር እንደዳረገው ቅሬታ ያላቸው አስታውቀዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm


Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related