አዲስ ሪፖርተር ዜና – ነባር መንግስት ይመለስ የሚለው የህወሓት ውሳኔ አደገኛ፣ ተጨማሪ ግጭትና ጥፋት የሚጋብዝ ውሳኔ ነው። ውሳኔው ከተተገበረ ውድቀት እንጂ ድል አይገኝም” ሲሉ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ አስታወቁ። ስልጣናቸውን በደቦና በጩኸት እንደማይለቁም አስገነዘቡ። ውሳኔውን የወሰነው ወገን አርሚ ሃያ ሁለት አፈጻጸሙን እንዲመራ መመሪያ ሲሰጥ፣ አቶ ልደቱ አያሌው በእነ ዶክተር ደብረጽዮን የሚመራው ቡድን “ጥፋት የለበትም” ሲሉ ሞገቱ።
ታደሰ ወረደን ጠቅሶ ይህን ያሰራጨው የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ነው። አርሚ 22 ከክልሉ ፖሊስ ጋር በመሆን እሳቸውን ለማስወገድና የእሳቸውን መመሪያ በሚቀበሉ ላይ እርምጃ እንዲወስድ መመሪያ መሰጠቱ እንደተሰማ ነበር “አታስቡት፣ አታድርጉት” ሲሉ የተናገሩት።
ህወሃት በውስጡ በተፈጠረ የሃሳብ ልዩነት ከተከፈለ በኋላ አብላጫውን ታጣቂ ኃይል የተቆጣጠረ ነው የሚባለው ወገን ጫና ማሳደሩ በተለያዩ መድረኮች ሲገለጹ ቆይተዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ በኃይል ከኃላፊነታቸው ከተነሱ በኋላ፣ አሁንም ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደን ከኃላፊነታቸው ለማንሳት የተጀመረውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ “የተለየ ሃሳብ ያላቸውን ወገኖች ማግለልና ማጥቃት የትም አያደርስም። የሚበጀው የትግራይን አንድነትና የጋራ አቅም በአስቸኳይ መልሶ ማጠናከር ነው” ብለዋል።
የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ፕሬዝዳንቱ እንደገለጹት፤ ይህ አካሄደ “የስትራቴጂካዊ አመራር ውድቀት” አቅምንና ሀብትን ወደ ማባከን የሚያመራ ነው። ቀደም ሲል በተደረገ የጋራ ግምገማ የስትራቴጂክ አመራር ውድቀት ገጥሞናል” በማለት በፓርቲ ደረጃ ቢወሰነም ይህ “ወድቀናል” የሚለው አካል አሁንም ለስልጣን ግብግብ ቅድሚያ መስጠቱ የትግራይ ተወላጆችን አሳዝኗል።
ህወሓት ከዚህ ቀደም የተለያዩ ሃሳቦችን በማሰባሰብና በማቀናጀት እንደሚታወቅ አስታውሰው፤ በአሁኑ ወቅት ግን በፓርቲው ውስጥ ያለው ሁኔታ መቀየሩን ገልጸዋል። አሁን ላይ ከድርጅቱ ውስጥ እንኳ የተለየ ሃሳብ ማቅረብ ስም ማጥፋትንና በግለሰቦች ገጸ ባህርይ ላይ ግድያ እንደሚያስከትል የደረሰ መሆኑን ጠቁመዋል።
“የሃሳብ አማራጮችን ከመቀበል ይልቅ በአሁኑ ወቅት የሚታየው የተለየ አሳብን የማግለል አዝማሚያ ለትግራይ የሚፈይደው ነገር የለም ብለዋል” ይህ አካሄድ ጦርነትን ለማካሄድም ሆነ ትግራይን በሰላምን ለመምራት እንደማይበጅም አስጠንቅቀዋል።
የክልሉ መንግስት የተለያዩ ቡድኖችንና ውሳኔዎቻቸውን እንደሚያከብር የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ ይሁን እንጂ ክልሉ ልዩ ልዩ አመለካከቶችና ሃሳቦች ላላቸውም ተመሳሳይ ምልከታ እንዳለው አስታውቀዋል። በዚህም መነሻ ትግራይን በአንድ ፓርቲ እይታ ብቻ መምራትም ሆነ መወሰን እንደማይቻል ማስገንዘባቸውን የትግራይ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በእንግሊዝኛ ባሰራጨው ዜና አስታውቋል።
ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደንና በእሳቸው ጎን የቆሙትን ለማስወገድ ኃላፊነት የወሰዱት የአርሚ 22 አዛዥ ኮሎኔል ገብረ ስላሴ የፖሊስ አመራሮችን ሰብሰበው ማነጋገራቸውና ለጊዜው ይፋ ያልሆነ መመሪያ መስጠታቸው ተሰምቷል። ታደሰ ወረደ በበኩላቸው ይህ መረጃ እንደተሰማ “አታስቡት” ብለዋል።
ቀደም ባለው ቀን የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር መሪ ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ በትግርኛ ለሚሰራጭ ዩቲዩብ በሰጡት ማብራሪያ “የተለያዩ አመለካከቶችን ማግለልና ማጥቃት ትግራይን አይጠቅምም” ብለዋል።
ህወሓት ባለፈው ሳምንት ” ነባሩ መንግስት ይመለስ ” ሲል የወሰነው ውሳኔ እሳቸውን ጨምሮ ዘጠኝ አባላት ላሉት ካውንስል እስከ አሁን እንዳልቀርበም። ቢቀርብም ቀርቦም ካውንስሉ ውሳኔውን እንዲያውቀው ከማስቻል በዘለለ ውሳኔውን መቀልበስ እንደማይችል ገልጸዋል።
ከአክሱም ከተማ ስብሰባ በኋል “ነባሩ መንግስት ይመለስ” የሚል ውሳኔ በኋላ የውሳኔው አስፈፃሚ ከሆነ የህወሓት አካል እንዳልተገናኙ ፤ በተናጠል ሳይሆን ውሳኔውን ከሚያስፈፅም አካል ተገናኝተው መወያየት እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል።
የህወሃት ነባር መንግስት ይመለስ ሲል የያዘው አቋም አደገኛ፣ ተጨማሪ ግጭትና ጥፋት የሚጋብዝ ፤ ውሳኔው ከተተገበረ ውድቀት እንጂ ድል እንደያያስገኝ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ደጋግመው አስጠንቅቀዋል።
ፕሬዜዳንቱ የተፈጠረውን የፓለቲካ ቀውስ ለማረጋጋት የሚያስችል አማራጭ የመፍትሄ ሀሳብ እንዳላቸው፣ ይህም አማራጭ ጉዳዩን ዶክተር ደብረጽዮን ለሚመሩትና እሳቸው ጨምሮ ዘጠኝ አባላት ላሉት ካውንስል ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸው ነው።
ጄኔራሉ የክልሉ መንግስት ሚድያዎች በህወሓት በመጠለፋቸው ምክንያት ሚያዝያ 13 ቀን የሰጡት ቃለ መጠይቅ ተዛብቶ መቅረቡን አመልክተዋል። ለአብነት “ስልጣኔን እለቃለሁ” ብለዋል ተብሎ በክልሉ የሚዲያዎች የተሰራጨ መረጃ እንዳለና ይህም የተሳሳተ መሆኑ አስገንዝበዋል።
“ነባሩ መንግስት ይመለስ” የሚል የህወሓት ውሳኔ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ስር ያሉ ዞኖች ለምሳሌ፣ የክልሉ ደቡባዊ ዞን ” ውሳኔውን ተቀብያለሁ” ብሎ በካቢኔ ደረጃ በሚድያ መስተጋባቱን የተሳሳተ መሆኑን ፤ ይህ ስህተት ምንጩ የቆየው የፓርቲ እና የመንግስት መዋቅር መደበላለቅ እንደሆነ አንስተዋል።
በጊዚያዊ መንግስት ላይ መፈንቅለ መንግስት (ኩዴታ) ለማድረግ ማሰብና መተግበር ለትግራይ ህዝብ የማይመጥን የቅርቡም የሩቅም የማይቀበለው ዘመኑ የማይዋጅ እንደሆነ ገልጸው፣ እንዲህ ያለ አደገኛ ድርጊት እንዳይታሰብ እንዳይተገበር በፅኑ አስጠንቅቀዋል።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ መዋቅር አሁንም በስራ ላይ እንደሆነና የዕለት ተዕለት መንግስታዊ ስራዎች በአግባቡ መከናወን እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ፕሬዜዳንቱ ስልጣናቸው በጩኸትና በደቦ ውሳኔ እንደማይለቁ በመግለፅ ማንኛው ትግራዋይ፣ የማህበረሰብ አንቂ፣ የክልሉ ፓለቲካ ከድጡ ወደ ማጡ ከሚያሸጋግር ሃላፊነት የጎደለው ተግባር እንዲቆጠብ አስጠንቅቀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ ልደቱ የፕሪቶሪያው ስምምነት ፈርሷል። 2012 የተመረጠው መንግስት ወደ ስልታን ይመለስ የሚለው ውሳኔ ትክክል ነው አሉ። አቶ ልደቱ በሃሳብ ገበታ ላይ ከአቶ አሉላ ጋር ሲሟገቱ ነው ይህን ያሉት።
አቶ አሉላ ቀደም ሲል “አቶ ልደቱ የሚመሩት የአመጽ አደራጅ ግብረኃይል የህወሃትን ወኪሎች ብቻ አሳትፏል። ግብርኃይሉም ከሽፏል፣ ህወሃትን የሚፈልጉት ጦርነት ስለሚያነሳላቸው ነው” ማለታቸው አቶ ልደቱን እስኪሳደቡ ድረስ አበሳጭቷል።
አቶ አሉላ ህወሃት 2012 የተመረጠው መንግስት እንዲመለስ መጠየቁ ጦርነት እንደማወጅ እንደሚቆጠር የቀድሞው ጦርነትም ዋና ምክንያት እንደሆነ ገልጸው አስታውቀው ነበር። ታደሰ ወረደ፣ የተለያዩ የህወሃት አባላትና በሃሳብ የተለዩ አመራሮች፣ ራሳቸው አቶ ጌታቸው “መቶኛ እብደት” ያሉትን ጉዳይ አቶ ልደቱ “ህወሃት ትክክል ነው” በማለት ሞግተዋል።
አቶ ልደቱ የፕሪቶሪያውን ስምምነት ያፈረሰው የፌደራሉ መንግስት እንደሆነ ደጋግመው ተናግረዋል። ይህን ሲሉ ወልቃይት አለመመለሱን ይሁን ሌላ የጎደሉ ጉዳዮች አላብራሩም። ሚዲያውም አልጠየቃቸውም። አቶ ልደቱ አያሌው አክለውም ህወሃት ጦርነት ሲያውጅ አይተውም ሰምተውም እንደማያውቁ ተናግረዋል። በመግለጫው ሁሉ “ቅድሚያ ለውይይት፣ ለሰላም ሲል ነው የማውቀው” ብለዋል።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






