ስምንት አባላት የተካተቱበት አዲስ የትርምስ ቡድን ተቋቋመ፤ ቡድኑ የተቋቋመው በብረት የታገዘው እንቅስቃሴ እንደተጠበቀው ባለመሆኑ በኃይማኖትን በጎሳ ግጭቶች ለማገዝ ነው

Date:

አዲስ ሪፖርተር | አዲስ አበባ | በተለያዩ አግባቦች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች፣ ድርጅቶች፣ ማህበሮች ወዘተ “ጽምዶ” ብለው በይፋ ከመውጣታቸው በፊት አቶ ነዓምን ዘለቀ ሻዕቢያን፣ አቶ ልደቱ አያሌው ህወሃትን ወክለው የመሰረቷቸውን ስብስብቦች “የጋራ መድረክ” በማለት አጣምደዋቸው ነበር። በ”ሰላማዊ” ትግል ስም የተሸፈነው ጥምረቱ ምርጫ እንዳይደረግ፣ ከዚያም የምክክር ኮሚሽኑ ስራውን እንዳያከናውን አጀንዳ እየቀያየረ ቢሞክርም ሁለቱንም ዓላማዎቹን ሳያሳካ እየተመናመነና እየከሸፈ መሄዱን ከአባላቱ መካከል ለአዲስ ሪፖርተር በተደጋጋሚ መረጃ ሲያደርሱና ሲዘገብ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

እነዚሁ ወገኖች እንዳሉት “የህልውና ትግል” በማለት የተለያዩ ታጣቂዎችን በማሰባሰብ በሻዕቢያ የተደራጀ ኃይል መመስረቱን ተከትሎ አቶ ነዓምን እና አቶ ልደቱ ተጣምረው በመሰረቱት የጋራ መድረክ አክቲቭ የሆኑ አባላቱ ከሶስት ሊበልጡ ባለመቻሉ መደረኩ እያደር ሟምቷል። ከሶስት የማይበልጡ አባላቱ ብቻ ስብሰባ የሚገኙበት ህብረት “ቀንዲል” እና “አንከር” የተባሉት ሚዲያዎች ላይ እየወጡ ያቋቋማቸውን ሻዕቢያን አጀንዳ ቢናገሩም ህብረታቸው በመፍረሱ አዲስ ስምንት አባላት ያሉት የትርምስ ቡድን ማቋቋማቸው በሳምንቱ መጀመሪያ ታውቋል። አዲሱ ቡድን ዋና መሰረቱን ኃይማኖት ውስጥ የሚተክል ሲሆን መምህር ፋንታሁን ዋቄ ተካተውበታል።

“ቡድኑ ውስጥ ውስጡን በኃይማኖት፣ በዘርና በጎሳ ህዝብ እንዲጫረስ የኃይማኖት ሽፋን ከለበሱ አካላት ጋር ሲሰሩ ቢሰነባብቱም በሳምንቱ መጀመሪያ ይፋ ሆኖልናል” ያሉ የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪዎች እንዳሉት፣ ይህንኑ ያረጋገጡላቸው አቶ ያሬድ ኃይለማሪያም እንደሆኑ አስታውቀዋል። ራሳቸውን የሰብአዊ መብት ተሟጋች፣ ተንታኝ እና የሲቪል ማህበረሰብ መሪ አድርገው የሚያቀርቡት አቶ ያሬድ “ነጮቹ ጋር ለመጮህ ትግላችንን የሰላማዊ እያልን እንጥራው። በአገር ቤት ደጋፊዎቻችን ሲታሰሩ ተቃውሞ ለማሰማትም ያመቸኛል” በማለት በፈረሰው የጋራ መድረክ መደበኛ ስብሰባዎች ላይ ሲናገሩ እንደነበር በአዲስ ሪፖርተር የኦዲዮ መረጃ በማስደገፍ መዘገቡ አይዘነጋም።

አቶ ያሬድ እሳቸው፣ አቶ ልደቱ አያሌውና አቶ ነዓምን ያሉበት ስምንት ቡድን ያለው የህቡዕ ቡድን መቋቋሙን ሲያስታውቁ የተቀሩትን አባላት ስም ዝርዝር ይፋ አላደረጉም። በአብሮነት ውስጥ አብሯቸው ሲሰበሰብ ለነበረ ባልደረባቸው “የጋራ መድረኩ ስለፈረሰ ተስፋ አትቁረጥ” በማለት ይህ አዲስ [የትርምስ ቡድን] ተቋቁሞ ስራውን ከጀመረ አንድ ወር እንዳለፈውና በአገር ቤት ስራውን በስፋት እየሰራ መሆኑን አስታወቀዋል።

ሌላ የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪ እንዳሉት ይህ አዲሱ ቡድን መመህር ፋንታሁን ዋቄን በአባልነት ያካተተ መሆኑን አምልክተዋል። ትልቅ ተግዳሮት የሆነባቸው ከሙስሊም ወገኖች ቡድኑ የተቋቋመለትን ዓላማ የሚያራምድ መሪም ሆነ ተባባሪ ማግኘት አለመቻላቸው ነው።

በኢትዮጵያ “ኦርቶዶክሳዊያን ተጎዱ” በሚል የዕምነቱን ተከታዮች ለማነቃነቅ ቀደም ሲል በዋናነት ሲሳተፉ ከነበሩ ታዋቂ አርቲስቶችና “ጥቁር ልበሱ” የሚለውን ዘመቻ ሲመሩ ከነበሩት መካከል አብዛኞቹ በቀጥታ ተሳታፊ ለመሆን ፈቃደኛ ባለመሆናቸው፣ በውጭ አገር ያሉ የኃይማኖት አባቶች እንዲካተቱ ተደርጓል። አካሄዱ ለገባቸውና ድርጊቱን ለማይቀበሉት መመህር ፋንታሁን የሚያዘጋጁት የማስፈራሪያና የማስጠንቀቂያ መልዕክት በግል እንዲደርሳቸው ለማድረግ እቅድ መያዙን መረጃውን ያጋሩን አመልክተዋል።

መመህር ፋንታሁን “ፋኖ የእኛ ነው” በማለት በተደጋጋሚ አደረጃጀቱ እሳቸው ከሚመሩት “ሞዐ ተዋህዶ” ከተሰኘው የዕምነት ክንፍ የተፈጠረና አደረጃጀቱም በቤተ ዕምነት ውስጥ ብህቡዕ የተዘረጋ መሆኑ መዐዛ መሐመድ በምትመራው የድርጅቱ ሚዲያ መናገራቸው አይዘነጋም።

“በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እምነትን መሰረት ያደረጉ ግጭቶችን ማስነሳትና ህዝብን ከዕምነቱ ጋር በማያያዝ ሆድ እንዲብሰው በማድረግ ለአመጽ፣ ለቅዱስ ምስዋዕት ለማዘጋጀት በመናበብ ዘመቻ በማካሄድ የታስበለትን ያህል ውጤት ማምጣት ያልቻለውን የህልውና የተባለ ጦርነት ለማገዝ እየተሰራ ነው” ያሉት የመረጃው ባለቤቶች ከወራት በፊት በኤርትራ ኤምባሲ በሞዐ ተዋህዶ ሰዎች አማካይነት በአሜሪካ ኤርትራ ኤምባሲ የተከናወነውን የትርምስ ስብሰባ አስታውሰዋል። አዲስ ሪፖርተር በኤርትራ ኤምባሲ ከአዲስ አበባ በሄዱ የሞዐ ተዋህዶ ምልምሎች አማካይነት በተለምዶ ሸዋ የሚባለውን የኢትዮጵያ ክፍል ለማነሳሳትና ለማሳመጽ ይበጃል ያሉትን ዕቅድ ማቅረባቸውን ዘግበን እንደነበር ይታወሳል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የአውሮፓ ህብረት ተወካዩ ኤርትራና ህወሓት የአፍሪቃ ቀንድ ሰላም እየፈተኑ መሆኑን አስታወቁ፤

አዲስ ሪፖርተር | አዲስ አበባ | በአፍሪቃ ቀንድ የፖለቲካና...

የሶማሊያ ጠ.ፍ.ቤት የፕሬዝዳንቱን የሥልጣን ዘመን ማራዘም ሕገ መንግሥታዊ አይደለም አለ

አዲስ ሪፖርተር | አዲስ አበባ |በሶማሊያ የፖለቲካ ውጥረት ከፍተኛ...