ይድረስ ለኢትዮጵያዊያን ሻዕቢያ ኢትዮጵያን ለማውደም ደጋፊዎቹን አሳምኖ ሃብት ማሰባሰብ ጀመረ፤ መረጃው ለኤርትራዊያን ከለላ ለሰጡ አገራት ደርሶ እየተገመገመ ነው

Date:

አዲስ ሪፖርተር | አዲስ አበባ | ሻዕቢያ የኢትዮጵያን ሰላምና ደኅንነት በሁሉም አቅጣጫዎች ለማደፍረስና ዋና የሚባሉ መሰረተ ለማቶችን ለማውደም የነደፈውን ዕቅድ ለማሳካት በውጭ አገር በስደት የሚኖሩ ደጋፊዎቹን አሰባስቦ ከውሳኔ መደረሱ ታወቀ። የፕሬዚዳንት ኢሳያስን አገዛዝ የሚቃወሙ “የኢሳያስ አገዛዝን በመሸሽ ከለላ ያገኙ ኤርትራዊያን ከሻዕቢያ ጋር ያካሄዱትን ስብሰባ መረጃ በማሰባሰብ ለሚመከተው አካላት በማቅረብ ንግግር ጀምረናል” ብለዋል። ለኢትዮጵያ ህዝብም ጥሪ አቅረበዋል።  

ኢትዮጵያን ለማፈራርሰና ለማተራመስ የተፈጠረ መሆኑ የሚነገርለት ሻዕቢያ፣ በቅርቡ “ጽምዶ” በሚል የመሰረተው ሱዳን፣ ግብጽ፣ ህወሃት፣ ኦላ፣ የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር፣ የቤኒሻንጉልና የጋምቤላ ታጣቂዎች የተካተቱበት ህብረት መበተኑ  ይታወቃል።  

ከሳምንታት በፊት “የህልውና ትግል” በሚል ያደገውና በይፋ ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት የከፈተውን ህብረት የሚመራው ሻዕቢያ  ኢትዮጵያን ለማፈራረስና ለማተራመስ ቀንና ሌሊት ሙሉ አቅሙን አሰባስቦ ቢንቀሳቀስም ያሰበው ሳያሳካላት መቅረቱን ከግንባር የሚወጡ መረጃዎች እያረጋገጡ ባለበት በአሁኑ ሰዓት “በየትኛውም የዓለም ክልል የሚገኝ ኤርትራዊ ክተት ይበል” በማለት በዓለም ዙሪያ ስብሰባ ተካሂዷል።  

ስልክም ሆነ ማናቸውም የመቅረጫ መሳሪያ ማስገባት በማይቻልባቸው ስብሰባዎች “የሻዕቢያ ደጋፊዎች የወር ደሞዛቸውን እንዲያዋጡ ተወስኗል። ከዚያም በላይ በድሮን ግዢ እንዲሳተፉ ተስማምተዋል” በማለት ሻዕቢያን የሚቃወሙ የኤርትራ ተወላጆች ለአዲስ ሪፖርተር አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን እንዲያውቅ እና ምን እየሆነ እንደሆነ እንዲመረምር አሳስበዋል።  

እነዝሺሁ ክፍሎች ለአዲስ ሪፖርተር በላጁት ሚስጢራዊ መረጃ መሰረት ሻዕቢያ “ካሚካዜ” (Kamikaze) የተባሉ አጥፊ ድሮኖችን በስፋት መግዛት እንዳለበት ከደጋፊዎቹ ጋር ስምምነት ላይ ደርሷል። ቡድኑ እነዚህን የአጥፊነት ተልዕኮ ያላቸውን ድሮኖች በመጠቀም የኢትዮጵያን ስትራቴጂካዊ መሠረተ ልማቶች ለማውደም አቅዷል።  

በተመረጡ የልማት አውታሮች ላይ እና ድልድዮችን ለይቶ ለማውደም እና ሀገሪቱን ለማሽመድመድ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ ያለው ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በዚህ ደረጃ ለመጉዳት ይመስሉኛል ካላቸው የውጭ ኃይሎች ጋር ሳይቀር ጥምረት መፍጠሩን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቅ ጥሪ ማቅረባቸውን መረጃውን ያካፈሉን ወገኖች አስታውቀዋል።  

በህልውና ትግል የተሸፈነው ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዕቅድ ይሳካ ዘንድ “ኢትዮጵያዊ ነን” የሚሉ ተቃዋሚዎችና አክቲቪስቶች ተባባሪ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ልብ እንዲል ያሳሰቡት የኤርትራው አግወዛዝ ተቃዋሚ ኃይሎች “ኢትዮጵያ በርካታ ስደተኛ የኤርትራ ተወላጆችን ተሸክማ የያዘች ባለውላታችን አገር ናት” ያሉት እነዚሁ ወገኖች ይህ መተሳሰር ሊጠናከርና ሊጠናከር እንደሚገባ እመነታቸው እንደሆነ አመልክተዋል። አያይዘውም አንዳንድ የኢሳያስ አፉወርቂን የቤት ስራ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ የተሸከሙ ካሉ ራሳቸውን እንዲመረምሩ አስጠንቀቀዋል።  

ድሮኖቹን ከኤርትራ ለመላክ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ውስጥ አስርጎ በማስገባት ጥቃት የመሰንዘር እቅድ መያዙን ያመለከቱት ወገኖች፣ ሻዕቢያ ቢሳካለት ኢትዮጵያን ለመጉዳት የሚችለውን ጉድጓድ እየቆፈረ መሆኑን አመልክተዋል። 

በውጭ አገር ከለላ አግኝተው የሚኖሩ የኤርትራ ተወላጆች ራሳቸውን ከዚህ መሰሉ አጥፊ ተግባር ራሳቸውን እንዲያገሉ ያመለከቱት የተቃዋሚ አመራሮች፣ በአውሮፓና አሜሪካ ለሽብር ተገባር የሚውል ገንዘብና ድሮን ለመግዛት ተሰብስበው የተስማሙ የሻዕቢያ ደጋፊዎችን አስመልክቶ ከየአገራቱ መንግስታት የሚመለከታቸው አካላት ጋር ግንኙነት እያደረጉ መሆኑን ለአዲስ ሪፖርተር ገልጸዋል።  

በዲያስፖራ የሚኖሩ የሻዕቢያ ደጋፊዎች በገንዘብ ብቻ ሳይሆን በቴክኖሎጂ እውቀት የሰለጠኑ ልጆቻቸውን ወደ ኤርትራ እና የተመረጡ ቦታዎች ለመላክ መስማማታቸውን፣ በውጭ አገር የተማሩትን ስደተኛ ወጣቶች ኢትዮጵያን ለማፍረስ በሚደረገው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ውስጥ በቴክኖሎጂው አግባብ ሻዕቢያን እንዲረዱ ስምምነት የተደረሰው በኤርትራ በዚህ ደረጃ ትምህርት የሚሰጥ ተቋምም ሆነ ባለሙያ ባለመኖሩ የተፈጠረውን ክፈተት ለመሙላት በሚል እንደሆነ መረጃውን የሰጡን አመልክተዋል።  

ሻዕቢያ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የዘር ፖለቲካ  በመጠቀም፣ የዘር ግጭትን በሁሉም አቅጣጫ ለማስነሳት ልዩ ኃይል ማቋቋሙን እነዚሁ ወገኖች አመልክተዋል። ይህ ከውጭ የተቀናጀ ኃይል በአገር ውስጥ ያሉትን ስንጥቆች በማስፋት የእርስ በርስ ግጭት እንዲቀሰቀስ የማድረግ ተልዕኮ ያለው ነው። አዲስ ሪፖርተር ከወራት በፊት አሜሪካ በሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ ከኢትዮጵያ የሄዱ የሞአ ተዋህዶ ክንፍ አባላት ኢትዮጵያን እንዴት በኃይማኖት ማተራመስ እንደሚቻል ጥናት ማቅረባቸውንና በጀት መጠየቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል። አሁን በደረሰን መረጃ ኤርትራዊያን የወር ደሞዛቸውን በአስቸኳይ በማሰባሰብ ለሻዕቢያ ሲሰጡ በዋናነት የሚውለው ለዝህም ተግባር ነው። 

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related