አዲስ ሪፖርተር | አዲስ አበባ | ህወሃትና ሻዕቢያ እስካልተወገዱ ድረስ ኢትዮጵያ ሰላም እንደማይኖራት የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ቡርሃኑ ጁላ አስታወቁ፤ ኤታማዦር ሹሙ ይህን ያሉት ዛሬ ከመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ነው፤ ጆን መዲድ ወደ ጦርነት ያስገባቸው “የደንቆሮዎች ስብስብ” ያሉት እርስ በርሱ የማይግባባ ስብስብ እንደሆነ አስታውቀዋል።
የክልሉ የሃይማኖት አባቶችና የትግራይ ክልል ባለአደራ አመራሮች በተገኙበት ፊልድ ማርሻል ቡርሃኑ እንዳሉት ኢትዮጵያ ሰላም እንድትሆን ሻዕቢያና ወያኔ መወገድ አለባቸው። ይህንን አስተያየት የሰሙ የኤርትራ ተቃዋሚዎች ንቅናቄ አመራር “ጊዜው አሁን ነው፤ ከውስጥ የሻዕቢያ አገዛዝ እየተፈረካከሰ እንደህነ መረጃው አለን” ብለዋል። በስብሰባው ህዝብ የተለያዩ ጥያቄዎችን ያነሳ ሲሆን፤ በተለይም ከጸጥታና ሰላም፣ እንዲሁም ከመለሶ መቋቋም ጋር ለተነሳው ጥያቄ ቀጥተኛ ምላሽ ተሰጥቷል።
በቅርቡ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ተማርከው በምርኮ የሚገኙት የህወሓት የቀድሞ ደቡብ ግንባር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ዮሐንስ ገብረጊዮርጊስ፣ በተለምዶ “ጆን መዲድ” በሚል ስም የሚታወቁት “ከሃዲዎቹ ምርኮኞች” በተሰኘ ዘጋቢ ፊልም ላይ ስለ መማረካቸውና ስለ ጦርነቱ ምክንያቶች ማብራሪያ ሰጥተዋል። ጀነራሉ በመከላከያ ሠራዊት ከበባ ውስጥ ገብተው እንደተማረኩ በፊልሙ ላይ ገልጸዋል።
በዘጋቢ ፊልሙ ላይ የሕወሓትን አመራር በጠንካራ ቃላት የተቹት ጀነራሉ፣ ወደ ጦርነት ያስገባቸው “የደንቆሮዎች ስብስብ” እንደሆነ ተናግረዋል። የቀድሞው የህወሓት ደቡብ ግንባር አዛዥ ይህንን አስተያየት ያቀረቡት የጦርነቱን ውሳኔዎችና የአመራሩን ስሌት በመተቸት ሲሆን፣ የሰጡት ምስክርነት በህወሓት ውስጣዊ የጦር አመራርና የጦርነቱ ሂደት ላይ ያጋጠማቸውን ኪሳራ የሚያስረዳ ነው።
ዮሐንስ ገ/ጊዮርጊስ በትግራይ ኃይሎች ውስጥ ከፍተኛ የጦር አመራር ቦታ ይዘው የነበሩ ሰው ሲሆኑ፣ በደቡብ ግንባር ዋና አዛዥነት አገልግለዋል። በተለይም በኢትዮጵያ መከላከያና በህወሓት መካከል በተካሄዱ ግጭቶች ውስጥ የተሳተፉ ከፍተኛ የጦር አመራር አባል ነበሩ። ዳዊት ከበደ “ማገዶ ቆጣቢ ጄኔራል” ሲል ያቆላመጣቸው ጄኔራ መዲድ “አንድ ትወልድ እናስጨርሳለን” በማለት የብልጽግናን መንግስት እንደሚጥሉ በፊት ለፊት የተናገሩና ሰፊ ሃብት እንዳላቸው የሚታውቁ መኮንን ናቸው። ዘርዝሩን እናቀርባለን።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






