ስታሊን ገብረሥላሴ ባሰራጨው የሽብር ዜና በአሜሪካ ሕግ እርምጃ እንዲወሰድበት ጥሪ ቀረበ፤

Date:

በአሜሪካ የፌደራል ህግ መሰረት ኤርፖርቶችን እና የአቪዬሽን መሰረተ ልማቶችን ማጥቃት ወይም ከዚሁ ጋር የተያያዙ የሀሰት የሽብር ዛቻዎችን እና የጥቃት ጥቆማዎችን ማሰራጨት ብሄራዊ ደህንነትን የሚያናጉ ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ናቸው። በሀገሪቱ ለሲቪል አቪዬሽን ሰላም እና ደህንነት ከሚሰጠው ከፍተኛ ትኩረት አንጻር፣ እንደዚህ ባሉ ድርጊቶች ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ከባድ የገንዘብ መቀጮ እና ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮች የካሳ ክፍያን ጨምሮ ከበርካታ ዓመታት እስራት እስከ እድሜ ልክ ወይም የሞት ቅጣት የሚያደርሱ የፌደራል ፍርድ ውሳኔዎች ይተላለፍባቸዋል።

አዲስ ሪፖርተር ዜና —በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖረው ማህበራዊ ሚዲያ ተዋናይ ስታሊን ገብረሥላሴ በሰጠው አወዛጋቢ አስተያየት ሳቢያ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ የተቀሰቀሰ ሲሆን፤ ያሰራጨው መረጃ በዓለም አቀፍ አቪዬሽን ደህንነት ላይ የደቀነውን ስጋት ተከትሎ የዩኤስ የፌደራል የህግ አስከባሪ አካላት ጣልቃ እንዲገቡ አስቸኳይ ጥሪዎች እየቀረበ ነው። ያሰራጨው መረጃ ሽብርን የሚያበረታታ እንደሆነም ተመልክቷል።

ስታሊን ገብረሥላሴ በፌስቡክ ገጹ ባሰፈረው መልዕክት የኮምቦልቻ እና የባህር ዳር አውሮፕላን ማረፊያዎች መመታታቸውን እንዲሁም በደብረዘይት በኩል ከባድ ኢላማ መገኘቱን ጠቅሷል። በመቀጠልም ቦሌ በረራ ሊቋረጥ የትብብር ኃይሎች ማስጠንቀቂያ ሊሰጡ ይችላሉ የሚል እጅግ አሳሳቢ መልዕክት አስፍሯል።

በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሲቪል መንገደኞችን የሚያስተናግደው የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የበረራ መቋረጥ ስጋት ሊደቀንበት እንደሚችል መገለጹ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ፈጣን ውግዘትን አስከትሏል። በርካታ ጉዳዩ ያሳሰባቸው ዜጎች ንግግሩ አደገኛ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ አስተያየት ሰጪዎች ድርጊቱን “እብደት” ሲሉ ኮንነውታል። ሲቪል የአቪዬሽን መሰረተ ልማቶች በማንኛውም የፖለቲካ ግጭት ውስጥ ለፖለቲካዊ ዓላማዎች መጠቀሚያ ወይም የጥቃት ኢላማ መሆን እንደሌለባቸውም ህግ እንደሚያስገድድ ጠቅሰው አውግዘዋል።

ታዛቢዎችና የማኅበረሰብ ተሟጋቾች እንደሚያመለክቱት ስታሊን ገብረሥላሴ የትህነግ ቀንደኛ ደጋፊ እና ትህነግ በተዘዋዋሪ ህዝብን ለማስደንገጥ፣ ሃሰተኛ መረጃ ለማሰራጨትና ለማሸበር ከሚጠቀምባቸው የማህበራዊ ሚዲያ ጭፍራዎቹ መካከል አንዱ ነው፤ ስታሊን ቡድኑን ወደ ስልጣን ለመመለስ በቻለው ሁሉ የተጣመመና የስጋት መረጃ እያሰራጭ ነው። ቀደም ሲል “በኔ ትውልድ ኢትዮጵያ ስትፈርስ በማየቴ በጣም ደስተኛ ነኝ” በማለት የተናገረውን ጨምሮ ያለፉት አፍራሽ ንግግሮቹ በብዙዎች ዘንድ በድጋሚ እየተመዘዙለት ነው።

ራሱን የ”ጽምዶ” አስተባበሪና መሪ አድርጎ የሚያቀርበው ስታሊን፣ ስማቸውን ዘርዝሮ እንደሚመቱ ይፋ ያደረጋቸውና የመቱ ያላቸው አውሮፕላን ማረፊያዎች፣ ስራቸውን በአግባቡ እየሰሩ እንደሆነ ያመለከቱ እንዳሉት እንዲህ ያለው መረጃ ማሰራጨት የሽብር ተግባር ነው።

ይህንኑ ተከትሎ ቁጣቸውን ያሰሙ አሁን ላይ ጉዳዩ ወደ ህጋዊ ተጠያቂነት እየወሰዱት እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል። ስታሊን ገብረሥላሴ የሚኖረው በአሜሪካ በመሆኑ፤ ንግግሮቹ የዓለም አቀፍ የመጓጓዣ ደህንነትን እና የሀገር ደህንነትን በሚመለከቱ የዩኤስ አሜሪካ የፌደራል ህጎች ስር የሚወድቁ መሆኑን የህግ ተሟጋቾች አስረድተዋል። በዩናይትድ ስቴጽ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳዩን በቸልታ እንዳያልፈውና ብዜኘት ጉዳዩን ወደ ህግ ለመውሰድ ከሚሰሩ ጋር ሊተባበር እነደሚገባም አመልክተዋል።

በአሜሪካ የፌደራል ህግ መሰረት በዓለም አቀፍ የትራንስፖርት ማዕከላት ላይ ስጋት መፍጠር፣ ጥቃት እንዲሰነዘር መቀስቀስ ወይም አገልግሎትን ማስተጓጎል ከባድ የወንጀል ጥፋት መሆኑን የህግ ባለሙያዎች አንቀጽ ጠቅሰው አመልክተዋል።

የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ ያነጋገራቸው የህግ ባለሙያ በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ጥቃት መሰንዘርን ወይም አገልግሎትን ማስተጓጎልን በፌደራል ወንጀልነት የሚቀጣውን ህግ 18 U.S. Code § 37 ይጠቅሳሉ። በተጨማሪም 49 U.S. Code § 46507 የአውሮፕላን ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥሉ ዛቻዎችን ወይም የሀሰት መረጃዎችን ሆን ብሎ ማሰራጨት ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት እና እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ እስራት እንደሚያስቀጣ አስረድተዋል።

መስከረም 16 ቀን 2019 ዓም (ሴፕቴምበር 23 ቀን 2026) በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጄ. ማሲንጋ በአዲስ አበባ ከሚገኘው የዩኤስ ኤምባሲ ባወጡት ይፋዊ መግለጫ ትህነግ የከፈተውን አዲስ ወታደራዊ ጥቃት አጥብቀው አውግዘዋል። አምባሳደር ማሲንጋ በቅርቡ በትግራይ እና በአፋር ክልሎች የተቀሰቀሰውን ግጭት “ልታሸንፉት የማትችሉት ውጊያ” ሲሉ ገልጸውታል።

በኤምባሲው ይፋዊ መግለጫ ላይ አሜሪካ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ማዕቀብ የጣለችበት የትህነግ አመራር ሰፊ ጥቃት ለመሰንዘር የወሰደውን መጥፎ ውሳኔ ህገወጥነት በመግለጽ ኮንነዋል። አምባሳደሩ በፕሬዝዳንት ኦባሳንጆ መሪነት በአፍሪካ ህብረት የተደገፈውን ውይይት ውድቅ ማድረግ ለህዝቡ የሚጠቅመው ነገር የለም ካሉ በኋላ፤ አሜሪካ ኢትዮጵያን ወደ ተሳሳተ መንገድ ለመግፋት በሚሞክሩ ተጨማሪ መሪዎች ላይ ማዕቀብ ለመጣል የሚያስችሉ መሳሪያዎች ያሏት መሆኑን አስታውቀዋል።

በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዲሁም ጉዳዩ የሚያሳስባቸው ዜጎች ይህንን ሁኔታ ለአሜሪካ ባለስልጣናት በይፋ ማሳወቅ እንዳለባቸው በስፋት ጥሪ እየቀረበ ነው። ከህግ ተጠያቂነት ጎን ለጎን የስታሊን ገብረሥላሴ የግል የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች በአስቸኳይ ታግደው ለገጾቹ አስተዳዳሪዎች ሪፖርት መደረግ እንዳለባቸው ያሳሰቡ አሉ። በተጨማሪም የስታሊን የቅስቀሳ ማዕከል የሆነው ዛራ (Zara) የተባለው የሚዲያ ገጽ በህዝብ መሰረተ ልማቶች ላይ ስጋት ለሚፈጥሩ የሽብር አጀንዳዎች ድምጽ በመሆኑ፤ ሙሉ በሙሉ እንዲታገድ እና ሪፖርት እንዲደረግ ይህ ጎልጉልን ተከትለው የተለያዩ ሚዲያዎች ጥሪ አቅርበዋል።

መልዕክቱ በቀጥታ ለኢሚግሬሽን እና ጉምሩክ አስከባሪ (ICE) እና ለፌደራል ምርመራ ቢሮ (FBI) ሪፖርት እንዲደረግና ከአለም አቀፍ የህዝብ ደህንነት አንጻር አስፈላጊው ምርመራ እንዲካሄድበት የተቀናጀ ጥረት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሊሰጠው እንደሚገባው ተመልክቷል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related