አዲስ ሪፖርተር | አዲስ አበባ | ሰሞኑን እንዲቀሰቀስ በተደረገው የቦርናና ሞያሌ ግጭት የተጠበቀው ውጤት ባለመገኘቱ ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ገቢሳ መገምገማቸው ተሰማ። ሻዕቢያ የሚያደራጀው ሰላማዊ ሰልፍ የፊታችን ሰኞ በአሜሪካ ይካሄዳል፤ “ኢትዮጵያዊ ነን” የሚሉ አገራቸውን “ወራሪ” በማለት ሻዕቢያን ደግፈው መፈክር እንዲያሰሙ የመንደር ለመንደር ቅስቀሳ ይካሄዳል።
በተለያዩ ጊዜያት ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ቱርክ ወዘተ የሚመላለሱት ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል በህወሃት የአሜሪካ ክንፍ አመራሮች የተገመገሙት በቦረና እና ሞያሌ የተቀሰቀሰው ጦርነት በሚፈለገው መጠን ወደ ኦሮሚያና ሶማሊያ ክልል ዘልቆ ባለመግባቱ ነው። የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ ስለግምገማው የሚያውቁትን ጠቅሶ እንደዘገበው ፕሮፌሰሩ የሶማሌ የተለያዩ ታጣቂዎችን፣ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላትን ለማቀናጀት ወደ ተጠቀሱት አገራት ሲመላለሱ ከፍተኛ ገንዘብ ተመድቦላቸው ነበር። ግምገማውም በወጣው ገንዘብ መጠን ስራ ባለመሰራቱ ነው።
ከግምግማው በኋላ ባለፈው ረቡዕ በተካሄደ የጋራ መድረክ ስብሰባ ላይ ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል “ይህ መንግስት መውደቂያው ደርሷል። የተለያዩ ኮሚቴዎች በማቋቋም አስቀድመን ስራዎች መስራት አለበን። መዘጋጀት አለብን” ሲሉ ተደምጠዋል። ተባባሪያችን ዜና አቀባዮቹን ጠቅሶ እንዳለው፣ ለዚሁ ተግባር የተለያዩ የቤት ስራዎችን በመያዝ ወደ ኬንያ፣ ሶማሊያና ሎንዶን እንደሚያቀኑ ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል። በቅርብ ጊዜ በሎንዶን እና በናይሮቢ የሶማሌ ዜጎችን እና የኦእሮሞ ተወላጆችን ሰብሰበው እንደነበር በአዲስ ሪፖርተር መዘገቡ አይዘነጋም።
ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል በሶማሌና ኦሮሚያ መካከል ተጨማሪ ግጭት እንዲነሳ የሚዲያ ዘመቻ እንዲሰሩ በተመደቡት ሚዲያዎች ቀርበው ግጭቱ እንዲንቀሳቀስ ከጀርባ ሆነው ከሚሰሩ ጋር በሶማሌ ላንድ እና በኢትዮጵያ፣ እንዲሁም በሶማሊላንድ ተወላጆችና በኢትዮጵያ ወገኖቻቸው መካከል ግጭት ለመፍጠር የፕሮፓጋንዳ ስራ ለመስራት መርሃ ግብር መያዙን ከተባባሪያችን ለመረዳት ተችሏል። ለዚሁ ተግባር የሶማሊያ ምክር ቤት አባል የሆኑት ፈይሰል ሮበሌ እንዲሁም የሶማሊያ ተወላጅ የሆኑት የኬንያ ፓርላማ አባል ፋራህ አብረዋቸው እንደሚሰሩ ለማረጋገጥ ተችሏል።
ኬኒያና ካናዳ ሆኖ የሚሰራው አህመድ ያሲን የሚመራው DHAB ቲቪ፣ እንዲሁም SS ቲቪ የሚባሉ የዩቲዩብ ቻናሎች በአማርኛ ሳይቀር የጀመሩትን ይህንኑ ዘመቻ እንዲያጠናክሩ በጀት እንደተመደበላቸው ታውቋል።
በሌላ ዜና ዛሬ በዋሽንግቶን ዲሲ ሻዕቢያ ያደራጀው ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳል። በሰላማዊ ሰልፉ በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን አገራቸውን እንዲያወግዙ “ኢትዮጵያዊ ነን” በሚሉ የሻዕቢያ ተላላኪዎች ግብዣ እየተደረገላቸው ቢሆንም ሊሳካ እንዳልቻለ የስፍራው ተባባሪያችን አስታውቋል።
“አገሬን ወራሪ ብዬ እንዳወግዝ ጠየቁኝ” ያሉት የዲሲ ነዋሪ፣ ግብዣውን ያቀረበላቸውን ሰው አመናጭቀው እንደሸኙት አመልክተዋል። “ምንም ዓይነት የፖለቲካ ልዩነት ቢኖር ለሻዕቢያ በማገዝ አገርን በአደባባይ ማውገዝ የዘመኑ ታሪክ የማይረሳው ባንዳነት ነው። ይህንን ጉድ ህዝብ ሊሰማው እና ሊያውቀው ይገባል” ብለዋል።
በየኮሙኒቲው ኢትዮጵያዊያንን በየብሄሩ እየከፋፈሉ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ እንዲሳተፉ እቅድ መያዙን አቶ ነዓምንና አቶ ልደቱ፣ እንዲሁም ሌሎች ሶስት አባላት በተገኙበት ስብሰባ ባለፈው ረቡዕ ሲገለጽ “በሚዲያ ማውራት ብቻውን ለውጥ ሊያመጣ አላቻለም። በሰላማዊ ሰልፍ ጫና ማሳደር አለብን” ተብሏል።
የኢትዮጵያን ህጋዊ ወደብ ከህወሃት ጋር ተሻርኮ የዘረፈውን ሻዕቢያን በመደገፍ ኢትዮጵያን በመቃወም በዋሽንግቶን በሚደረገው ሰልፍ ከሲውዘርላንዱ የተለየ ምንም ዓይነት ውጤት ሊገኝ እንደማይችል የብርጌድ ነሃመዱ አመራር ገልጸዋል። “ወጣቶች ሻዕቢያን ዘወር በል በለዋል” ያሉት አመራሩ በሲውዘርላንዳ በተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ የተወሰኑ እድሜያቸው የገፋና ኤርትራ ቤት ንብረት ያላቸው ንብረታቸው እንዳይወረስባቸው ፈውርተው ከመሰለፋቸው ውጭ ወጣቶች አልተገኙም። ኢትዮጵያዊያን እንዳልወጡም አስታወቀዋል። በዲሲ ለሚካሄደው ሰልፍ ሻዕቢያ በጀት መመደቡ ታውቋል።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






