“አለቅሳለሁ፤ የማለቅሰው ለሞቱብኝ ሁለት ልጆቼ አይደለም፤ እነሱ ሞተዋል፤ አርፈዋል፤ የማለቅሰው በቁም ለሞትነው ነው” የትግራይ እናት፤ ሻዕቢያ ሽሬን ወስዷታል

Date:

“አለቅሳለሁ፤ የማለቅሰው ለሞቱብኝ ሁለት ልጆቼ አይደለም። እነሱ ሞተዋል። አርፈዋል። የማለቅሰው በቁም ለሞትነው ነው። በቁም ሞተናል። ተሎታችንም ሊደርስ አልቻለም። ከስቃይ ወደ ስቃይ፣ ከመከራ ወደ መከራ …. መቼ ነው የሚያበቃው? የትግራይ ሕዝብ መከራ ማቆሚያ አጣ፤ የትግራይ ህዝብ ስደትና ስቃይ እድሉ ሆነ፤ እድሜ ለህወሃት ወልደን እንዳንድር፣ ሸምተን እንዳንበላ፣ በሰላም ወጥተን እንዳንገባ አደረገን፤ ከዚህ በላይ ምን እንደንሆን ነው የሚጠበቀው?”

አዲስ ሪፖርተር ዜና — “ሸቀጥ የለም። ክብሪት እንኳን በአቅሙ ጠፍቷል። ትናንት በየመደብሩ የነበረው ሩጫ የጭንቀታችን ማሳያ ነበር” ሲሉ ጦርነቱን ተከትሎ በመቀለ ከተማ የነበረውን የሸመታ ሩጫ የገለጹ እናት “ግን ይህ መንግስት እስከመቼ ነው ዝም የሚለው? መቼ ነው መከላከያ ወደ መቀለ የሚገባው? ሲሉ ጠይቀዋል። 

የአዲስ ሪፖርተር የመቀለ ተባባሪ ያነጋገራቸው እናቶች “እስከመቼ ቆመን የሞትን ሆነን እንቀጥላለን?” በማለት ህዝብ እጅግ መሰላቸውቱን አመልክተዋል። “ለልጆቼ አላለቅስም” ያሉት እናት ሁለት ልጆቻቸውን አጥተው ባዶ ቤት የቀሩ እናት ናቸው።

“ሁለት ልጆቼን አጣሁ። አንዱን አሸሸሁ፤ ጎረቤቶቼ ሁሉ ፎቶ ታቅፈው ቀርተዋል። አይበቃንም ወይ? እስከመቼ ነው ይህ መንግስት ዝም የሚለን? አሁን እኮ መከላከያ ቢመጣ ዋጋ ለመክፈል የተዘጋጁ እናቶች አሉ፤ ይህን ነገሩልን” ያሉት እናት “ክብሪት እንኳን ብርቅ ሆነ፤ ሸቀጥ የለም። ችግሩ ከቀን ወደ ቀን እየባሰ የማንቋቋምበት ደረጃ ደርሷል” ሲሉ ከዚህ በላይ መታገስ ህዝብን እንደመዘነጋት ያህል እንደሚቆጠር አስታውቀዋል። 

“ልጆች ትምህርት ቤት መስደድ ሰቀቀን ሆኖብናል። ፈርተናል። በኑሮ ችግር፣ በሞት ፍርሃት፣ በሰላም እጦት ተሰቃየን። የእኛ ኑሮ ኑሮ አይደለም” ያለቸው ሌላ የሁለት ታዳጊዎች እናት፣ “ጠላት ካለ እንዴት ትኖራላችላችኹ” በሚል ታዳጊ ሴቶችን ለማፈስ ዝግጅት እንዳለ የመንደር ካድሬዎች እንደነገሯቸው አስታውቃለች።

ከስድሰት ቀን በፊት አፈሳ ፈርታ አዲስ አበባ የመጣች የ14 ዓመት ታዳጊ ለአዲስ ሪፖርተር “አሁን ትምህርት ቤት ገብቻለሁ፤ ጓደኞቼ እዛ ናቸው። ስለ እነሱ ሳስብ እጨነቃለሁ። ምን አለበት ቢስማሙና ጦርነቱን ቢያቆሙት? ምን ይጠቀማሉ?” በማለት እምባዋን እያቀረረች ተናግራለች። እሷ ወደ ተሻለ ስፍራ መምጣቷ ቢያስደሳታትም፣ ኝ መፍትሄ እንዳልሆነ ትናገራለች። 

የሽሬ ነዋሪ እናት በበኩላቸው በርካታ የሻዕቢያ ወታደሮች በመስፈራቸው በድሮን ድንገተኛ ጥቃት ከተሰነዘረ ለነሱም እንደሚተርፍ በመናገር ስጋታቸውን ይናገራሉ። “ለሻዕቢያዎች የሚተኮስ የድሮን ጥቃት ያሰጋናል፤ እንቅልፍ የለም። የሚሰፍሩት ትምህርት ቤቶችና የሰላማዊ ሰዎች መኖሪያ አካባቢ በመሆኑ ሁሌም በስጋት ውስጥ ነውን” በማለት የጭንቀታቸውን መጠን ያስረዳሉ። በሽሬ ያለውን የሻዕቢያን እንቅስቃሴ የሚታዘቡ “ሽሬን ሻዕቢያ ወስዷታል” በማለት ነው የሚገልጹት።

ሻዕቢያ ጦርነቱ ትግራይ ምድር ላይ እንዲቀር የያዘውን ዕቅድ እያስፈጸመ ያለው የዶክተር ደብረጽዮን ህወሃት “እንዴት ስለ ትግራይ ህዝብ አያስብም” በማለት የሚጠይቁ ሌላ እናት አንድ ቀን ይህ ሁሉ ያልፋል። ያኔ ምን ምላሻቸው ምን ይሆን?” በማለት ስሜታቸው መጎዳቱን ይናገራሉ። 

እቅድ አንድ ሳይሳካ ህወሃት አፈግፍጎ ከባድ መሳሪያ መወርወር ጀመረ። ሰላማዊ ሰዎች ሞቱ 

በትናንትናው ዕለት በይፋ አስታውቆ ህወሃት የጀመረው ውጊያ ሁለት ነበረው። በፋርና በአላማጣ ራያ አቅጣጫ የጀመረው ውጊያ አስመልክቶ የሚከተሉት መረጃዎች ደርሰውናል። 

በሰሜን ወሎ ጀመዶ፣ አመያ፣ ተኩልሽ አቅጣጫ የተጀመረውና የቆቦን አቅጣጫ አውራጎዳና በመያዝ መከላከያን ቆርጦ ለማጥቃት ዕቅድ የነበረው ውጊያ አልተሳካም። ለጊዜው ለህትመት የማይምች ምስል በማስደገፍ የደረሰን መረጃ እንደሚያሳየው ህወሃት ከፍተኛ ስብአዊ ኪሳራ ደርሶበት እቅዱን ሳያሳካ አፈግፍጓል። 

ይህንኑ ዕቅድ ለማሳካት ዋና ማዘዣውን አላማጣን አድርጎ በተጠቅሱት ቦታዎች ደቡብ ወሎ ደጋ ደጋውን የእግረኛ ውጊያ የከፈተው ህወሃት፣ አሁን ላይ የእግረኛ ውጊያውን አቁሞ፣ ከአላማጣ አልፎ አልፎ መድፍ በመወርወ ላይ እንደሚገኙ በስልክ መረጃ ካደረሱን ወገኖች ለማረጋገጥ ችለናል። በሚጣለው መድፍ ቆቦ ስድስት ነጹሃን፣ ዋጃ አራት ሞተዋል። አላማጣ ሁለት ሰዎች በተመሳሳይ ህይወታቸው ማለፉ ተመልክቷል። 

ሮቢትን ተቆጣጥሮ መከላከያን የመቁረጥ ዕቅድ ከሸፈ፤ ዕቅዱ ቢሳካ ዳውንት ፋኖን መቀላቀል ነበር

ህወሃት በደቡብ ግንባር ያደረገውን ዝግጅትና ማሳካት የፈለገውን የሚያውቁ በዝርዝር እንደሚያስረዱት ከሆነ፣ ህወሃት ተኩለሽን ከያዘ በኋላ፣ ራያ ቆቦ ወረዳ ሮቢት ቀበሌን መቆጣጠር አላማቸው ነበር። 

ሮቢት ትንሽ ከተማ ስትሆን የአገር መከላከያ እንዳለበት ይታወቃል። ጋራ ጋራውን በመሄድ ሮቢትን በመያዝ መከላከያን ቆርጦ፣ ወደ ዳውንት በማምራት ከአርሚ 32 እና የፋኖ ኃይል ጋር በመቀላቀል ወደ ፊት ለመገስገስ ያቀደው ህወሃት፣ በተመሳሳይ የከፈተውን ጦርነት በኪሳራ አጠናቆ ወደኋላ ማፈግፈጉ ታውቋል። ኃይሉን አጠናክሮ ዳግም ሊመጣ እንደሚችል ቢገመትም፣ ወቅታዊ ቁመናው እንደማይፈቅድለት ዝግጅቱን በቅርብ የሚያውቁ ገልጸዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

አሜሪካ ህወሃትን ይህንን ጦርነት አታሸንፉም ስትል አስጠነቀቀች፤ ከባድ ማዕቀብ እጥላለሁ ብላለች

አሜሪካ ህወሃትን እንጂ ሌሎችን ግምት ያስገባች አትመስልም። "የማታሸንፉት ጦርነት...

ህወሓት በተለያዩ ግንባሮች በይፋ ጦርነት ጀመረ፤ የትግራይ ሰላም ኃይሎችን ለመቁረጥ ታስቦ ነበር፤

አዲስ ሪፖርተር ዜና —  ህወሓት በአፋር ክልል ቶንሳ እና...

በአላማጣ እና አካባቢው በተካሄደ ከባድ የድሮን ጥቃት ምን ተፈጠረ? የፋጫ ትምህርት ቤት ጥቃት

አዲስ ሪፖርተር አዲስ ዜና —  ከሰሞኑ ከተካሄዱት የድሮን ጥቃቶች...