በሶማሌ ክልል አዲስ የመንግሥት አወቃቀር ለመዘርጋት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ ሪፖርተር ዜና — በሶማሌ ክልል አዲስ በሚዘረጋው የመንግሥት አወቃቀር መሠረት ክልሉን በሶስት ዋና ዋና ክላስተሮች በመከፋፈል ሶስት ምክትል ፕሬዚዳንቶችን ለመሾም ዝግጅቱ መጠናቀቁ ተሰምቷል።
አዲሱ አወቃቀር የክልሉን ዞኖች እና የህዝብ ማህበራዊና የጎሳ ስብጥር መሠረት ያደረገ መሆኑ ተጠቁሟል። በዚህ መሠረት ዞኖቹ በሶስት ዋና ክላስተሮች እንዲደራጁ ዝረዝር ተዘጋጅቷል። ስለ አሰራሩ የሚያወቁ ለአዲስ ሪፖርተር እንዳሉት እቅዱ በርካታ የአሰራር ችግሮችን ይፈታል።
ለአዲስ ሪፖርተር የደረሰው ሰነድ እንደሚያስረዳው ክላስተር አንደ ዳዋ፣ ሊበን እና አፍዴር ዞኖችን ያካትታል።
ዳዋ ዞን – ጋሬ
ሊበን ዞን – ዳጎዲ፣ ጉሬ እና አብዛኛው ማሬሃን ዳጎዲ
አፍዴር ዞን – ኦጋዴን፣ ጋድሰን፣ ሀዊዬ፣ ሼካሽ እና ጋሪሬ
ክላስተር ሁለት ደግሞ ሸበሌ፣ ኖጎብ፣ ቆራሔ እና ዶሎ ዞኖችን ያካትታል።
ሸበሌ ዞን – ኦጋዴን፣ ሀዊዬ እና ጃራር
ኖጎብ ዞን – ኦጋዴን
ቆራሔ ዞን – አብዛኛው ኦጋዴን፣ እንዲሁም ሀዊዬ እና ማሬሃን
ዶሎ ዞን – ሀርቲ፣ ኦጋዴን፣ ማሬሃን እና አባዮኒስ
ክላስተር ሶስት ጃራር፣ ፋፌን፣ ሲቲ እና ፊቅ ዞኖችን ይይዛል። በዚሁ መሰረት
ጃራር ዞን – ኢሳቅ እና ኦጋዴን
ፋፌን ዞን – ኢሳቅ፣ ጅድዋቅ፣ ሰመሮን፣ ጋሪ እና ሀዊዬ
ሲቲ ዞን – ዒሳ፣ ገዳቡርሲ፣ ጉርጉሬ እና ሀዊዬ
ፊቅ ዞን – ኦጋዴን እና ሀዊዬን ያካትታል።
እንደታቀደው እያንዳንዱ ክላስተር በአንድ ምክትል ፕሬዚዳንት የሚመራ ሲሆን፣ አዲሱ አወቃቀር የክልሉን አስተዳደራዊ አመራር በክልሎቹ የህዝብ ስብጥር መሠረት ለማደራጀት የታሰበ መሆኑ ተገልጿል።
ሆኖም ይህ መዋቅር በይፋ ፀድቆ የሚተገበርበት፣ ሶስት ምክትል ፕሬዚዳንቶች የሚሾሙበትን ሂደት እና የክላስተሮቹን ሥልጣንና ኃላፊነት የሚወስነውን የሕግ ማዕቀፍ በተመለከተ ተጨማሪ ይፋዊ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።
ይህንን መረጃ በማጣመም እቅዱ የክልሉን ፕሬዚዳንት አቅም አልባ ለማድረግ የተወሰነ በማስመሰል ዜናውን አጀንዳ ለማድረግ በአሜሪካ ሜኖስታ እና ካናዳ እቅድ መያዙን የአዲስ ሪፖርትር ተባባሪ ክዋሽንግቶን ዘግቧል።
በሶማሌ ክልል ያነጋገርናቸው አንድ ባለስልጣን፣ እቅዱ ትክክል መሆኑን ጠቁመው፣ ክልሉ በሚደነቅ የልማት፣ ታላላቅ አገራዊና አህጉራዊ ፕሮጀክቶች ላይ አተኩሮ ስለሚሰራ ለአሉባልታ ጊዜ እንደሌለው አስታውቀዋል። አክለውም “መቼም ቢሆን ክልሉን የሚጠቅም ጉዳይ ተግባራዊ ይሆናል። ቋሚ ነገር የለም” ብለዋል።
አዲስ ሪፖርተር ባላት መረጃ በተመሳሳይ የሚዋቀሩ ክልሎች አሉ።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






