የአገር መከላከያ ሰራዊት በሱዳን በኩል ተገዝተው ለህወሃት የተላለፉ የUAV M6 ድሮኖችና የስለላና የወታደራዊ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ከነግዢ ሰነዶቻቸው ማረከ – ልዩ ሪፖርት

Date:

ህወሃት በሱዳን ወኪሉ አማካይነት የሸመታቸው ድሮኖች እና የስለላ መሳሪያዎች አሁን ላይ ባለው ገበያ እስከ 10 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም እስከ 2 ቢሊዮን ብር የሚገመት ወጪ ያስወጣሉ፤ የትግራይ ህዝብ በመጠለያ እየተሰቃየ ባለበትና በምግብ እጥረት ከፍተኛ ስቃይ ላይ ያሉ ዜጎች በጀት ላይ እና በኮንትሮባንድ ወርቅ ከሚያገኘው ሃብት ይህንን ጨምሮ ከሸመታቸው መሳሪያዎች ውስጥ በአገር መከላከያ የተማረኩት ዋጋቸው አጠቃላይ ተሰልቶ ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን ምንጮች አስታውቀዋል። ከወደሙት ውጪ ድሮንን ጨምሮ በርካታ መሳሪያዎችን እጁ እያስገባ ያለው መከላከያ ወደፊት ዝርዝር መግለጫ የሚሰጥ ቢሆንም በሱዳን በኩል የተገዙት የM6 UAV ድሮኖች፣ የስለላና የወታደራዊ ሰው አልባ አውሮፕላኖች መማረክ ትልቅ ዜና ሆኗል

አዲስ ሪፖርተር | አዲስ አበባ |  በሱዳን ተገዝተው ለህወሃት የተላለፉ የM6 UAV ድሮኖች፣ የስለላና የወታደራዊ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ተማረኩ፤ የአገር መከላከያ ሰራዊት በሱዳን በኩል ተገዝተው ለህወሃት የተላለፉ የUAV M6 ድሮኖችና የስለላና የወታደራዊ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ከግዢ ሰነዶቻቸው ጋር መማረኩን ይፋ ሆኗል።

ጥር 26 ቀን 2017 ዓም ወይም እኤአ አቆጣጠር ፌብሩዋሪ 3 ቀን 2025 በአቅራቢው አገር የPFI ቁጥር 071749749-02 እና ሰኔ 3 ቀን 2017 ዓም ወይም እኤአ በ11 ጁን 2025 የተመዘገበው መሣሪያ በገዢው ሕጋዊ ተወካይ በአካል ተመርምሮ፣ የቴክኒክ ምርመራ ተደርጎለት በመጨረሻ ቴክኒካዊ ይዞታው ጸድቆ ተቀባይነት እንዳገኘው ከመሳሪያዎቹ ጋር የተገኘው የቴክኒክ ርክክብ ሰነድ እና የግዢ ውል ያስረዳል።

ከUAV M6 ሶስት ድሮኖች መካከል አንዱ ለበረራ ሙከራ ተመርጦ ሲሞከር፣ ሌሎቹ የUAV M6 ክፍሎች በመሬት ላይ ተመርምረዋል። ሁሉም የUAV M6 ክፍሎች የቴክኒክ ምርመራ ያለ ምንም ችግር መሥራታቸው ከተረጋገጠ በኋላ ግዢውን ጸድቆ ተቀባይነት አግኝቷል።

ከsurveillance payload መሣሪያዎች ውስጥ አንዱ ለምርመራ/ሙከራ ተመርጦ ሲፈተሽ፣ ሌሎቹ በመሬት ላይ ተመርምረዋል። ሁሉም የsurveillance payload ክፍሎች በአካል ተመርምረው የቴክኒክ ምርመራቸው ከተረጋገጠ በኋላ የመጨረሻ ቴክኒካዊ ተቀባይነት ተሰጥቷቸዋል።

በPFI ውስጥ የተዘረዘሩት ሁሉም UAV M6 መሣሪያዎች፣ FCU እና BRU ተመርምረው የቴክኒክ ምርመራቸው ተረጋግጦ፣ የመጨረሻ ተቀባይነት ማግኘታቸው በሰነዱ በግልጽ ተቀምጧል። በዚሁ አግባብ የተጠቀሱት መሳሪያዎች ሙሉ በሙሉ ህወሃት እጅ መድረሳቸው ተረጋግጧል።

በይፋዊው ደብዳቤ ላይ “ምሥጢር” በሚል የተላለፈው መመሪያ፣ በሱዳን ጦር ሠራዊት የተንቀሳቃሽ ዕዝ አዛዥ በሜጀር ኢንጂነር አህመድ አደም አህመድ የተፈረመ ሲሆን፤ ለተጓዳኝ ኦፕሬሽኖችና ለሎጂስቲክስ አገልግሎት የተመደበውን መኪና ዝርዝር መረጃ፣ የሻንሲ ቁጥር እና ልዩ የይለፍ ፈቃድ ይዟል። የተሽከርካሪው አስፈላጊውን የደህንነት መስፈርት አሟልቶ በየፍተሻ ኬላዎች ላይ ያለ ምንም ተጨማሪ ጥያቄና እንግልት በነጻነት እንዲያልፍ የይለፍ ፈቃድ እንደተሰጠ የሚያስታውቅ ነው።

ግዢውን በፈጸመው ሱዳናዊው ኤላሚን አህመድ አማካይነት ማረጋገጫ ቀረቦና ውል ተፈርሞ ህወሃት እጅ የገቡት ሰው አልባ ድሮኖችና የስለላ ካሜራዎች ሙሉ በሙሉ መከላከያ እጅ መግባታቸውን የሚያሳዩት ቪዲዮዎች ህወሃት ከፕሪቶሪያው ስምምነት ጀርባ ለጦርነት ሲዘጋጅ መኖሩን የሚያረጋግጡ እንደሆኑ ተመልክቷል።

ሻጩ ስሙ ሳይገለጽ በወኪል አማካይነት ለህወሃት የተገዙት ኤም 6 ሶስት ወታደራዊ ድሮኖች፤ በመከላከያ እጅ ሲወድቁ የተያዘው የግዢ ሰነድ በዝርዝር እንደሚያስረዳውና የተቀረጹት የተለያዩ ቪዲዮዎችና ምስሎች እንደሚያስረዱት አንዱ ድሮን አራት ቦንብ የመሸከም አቅም አለው።

አስራሁለት የቦንብ ማቀፊያ ዩኒቶች፣ የተለያዩ ካሜራዎች፣ ከመሬት በመሆን ድሮኖቹ የሚታዘዙበት ኮምፒታራይዝድ የመተኮሻ እና ማዘዣ መሳሪያዎች (የመሬት መቆጣጠሪያ ጣቢያ [GCS]፣ ፋየር ኮንትሮል ዩኒት [FCU] እና የሬዲዮ/መገናኛ መሳሪያዎች)፣ ለድሮኖቹና ለሁሉም መሳሪያዎች የሚያገለግሉ ሙሉ መለዋወጫዎች፣ የመጠገኛ ኪቶች ወዘተ ግዢ ተፈጽሞ ህወሃት እጅ መግባቱን ከሰነዱና ከቪዲዮዎች ለማረጋገጥ ተችሏል።

የUAV M6 (Mohajer-6) ድሮኖች መካከለኛ ከፍታ ላይ ለረጅም ሰዓታት መብረር የሚችሉ፣ ለስለላና ለታለሙ ወታደራዊ ጥቃቶች የሚያገለግሉ ዘመናዊ የታክቲካል ደረጃ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ናቸው። እነዚህ ድሮኖች ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የቀንና የሌሊት ኦፕቲካል ካሜራዎች (Payloads) የታጠቁ በመሆናቸው የቀጥታ ምስልና የመረጃ ስርጭትን ወደ ምድር መቆጣጠሪያ ጣቢያ የሚያስተላልፉ ሲሆን፤ በተጨማሪም የውጊያ መቆጣጠሪያ (FCU) እና የቦምብ መልቀቂያ (BRU) ሲስተሞች ስላሏቸው የታለሙ ኢላማዎችን በጥራትና በትክክለኝነት የመታት ከፍተኛ አቅም አላቸው።

የእነዚህ ድሮኖች ጥራትና አስተማማኝነት የሚገለጸው በላቀ የመገናኛና የሲግናል ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂያቸው እንዲሁም የጂፒኤስ ማወክንና መጨናነቅን በሚከላከሉ (GPS Anti-Jamming) የመከላከል ክፍሎቻቸው ነው። ከዚህም በተጨማሪ በድንገተኛ የቴክኒክ ችግር ወቅት አውሮፕላኑን ከጉዳት የሚያድን የፓራሹት ደህንነት ሲስተም የተገጠመላቸው ከመሆኑም በላይ፤ በሜዳ ላይ በቀላሉ ሊጠገኑና ሊጠበቁ የሚችሉ አጠቃላይ የመለዋወጫና የጥገና ቁሳቁሶች ስብስብ (Integrated Logistic Support) ያላቸው በመሆናቸው ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ብቁ ሆነው እንዲቆዩ ያስችላቸዋል።

በዓለም አቀፍ የጦር መሣሪያዎች ገበያ ዋጋ መሠረት፣ የተጠቀሱትን 3 የM-6 ድሮኖች፣ 4 የስለላና የምስል ካሜራዎች (payloads)፣ 12 የቦምብ ማቀፊያ ዩኒቶች (BRU)፣ የመተኮሻና የመቆጣጠሪያ ኮምፒውተሮች፣ የመገናኛ መሠረተ ልማቶች እንዲሁም በርካታ የመለዋወጫና የጥገና ዕቃዎችን ያካተተው ይህ ሙሉ ፓኬጅ አጠቃላይ ዋጋው ከ5 ሚሊዮን እስከ 10 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም እስከ 2 ቢሊዮን ብር ይገመታል።

ምንም እንኳን ትክክለኛው የገንዘብ መጠን በእነዚህ የቴክኒክ ምርመራ ሰነዶች ላይ ባይጠቀስም፣ አንድ ሙሉ የM-6 ድሮን ሲስተም ከነመቆጣጠሪያውና ቦምብ ማቀፊያው ከ1.5 እስከ 2.5 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ሲሆን፣ ቀሪው ወጪ ለረጅም ጊዜ የሚያገለግሉ መለዋወጫዎች፣ የጥገና ዕቃዎችና የመሬት መቆጣጠሪያ ጣቢያ መሣሪያዎች የሚውል ነው።

እነዚህን መሳሪያዎች ሙሉ በሙሉ የማረከው የአገር መከላከያ ሠራዊት ባለሙያዎች ይህ እስከተጻፈ ድረስ ሙያዊም ሆነ ማናቸውም ዓይነት መረጃ አልሰጠም። የተማረኩት ዝርዝር መሳሪያዎች ግን ህወሃት ባለው አቅሙ ሁሉ ለጦርነት ሲዘጋጅ እንደነበር የሚያሳይና የሚያረጋግጥ መሆኑን መረጃውን የላኩልን አስታውቀዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ጃዋር መሐመድ፦«የኤርትራ አምስተኛ ትውልድ ተሰዷል፤ የተረፈውም ተቆልፎበት ከቴክኖሎጂ ተፋቷል፤”

“....ቁጭ ብለው ኢትዮዺያ ስንት ቦታ እንደምትከፋፈል ሳያፍሩ እኮ ነበር ሲነግሩኝ፣ ሲያስረዱኝ...

Beyond the Immediate Horizon: Foundational Milestones for Tigray’s Post-TPLF Political Renewal

" ... Tigrayans will not only ensure a better...