ጃዋር መሐመድ፦«የኤርትራ አምስተኛ ትውልድ ተሰዷል፤ የተረፈውም ተቆልፎበት ከቴክኖሎጂ ተፋቷል፤”

Date:

“….ቁጭ ብለው ኢትዮዺያ ስንት ቦታ እንደምትከፋፈል ሳያፍሩ እኮ ነበር ሲነግሩኝ፣ ሲያስረዱኝ የነበረው … [የጥምረቱ አባላት] ዳዴ ሳይሉ፣ ገና እንደ ህፃን ዳዴነ ሳይሞክሩ That need to be checked ኢትዮጵያን ዝም ብሎ ማንም ወመኔ መጥቶ የሚያፈርሳት አገር አይደለችም ” 

አዲስ ሪፖርተር | አዲስ አበባ | ኤርትራ አምስተኛን ትውልድ መክሰሯን፣ በዚህም ሳቢያ ከቴክኖሎጂ ጋር የተለያየ አንጋፋ ምሽግ ቆፍሮ የሚተኩስ ኃይል ስላላት ኢትዮጵያን መቋቋም እንደማትችል ጃዋር ማነጻጸሪያ ጠቅሶ ተመለከተ። በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት የተበሳጩ መንግሥት ቢወገድ እንኳን ድርድር እንደማይፈልጉና የአገር መከላከያ ተቋም እንዲፈርስ ፍላጎት እንደነበራቸው አጋለጠ። “ኢትዮጵያን ተሸክሞ የያዛት ብቸኛውና ትልቁ ተቋም የአገር መከላከያ በመሆኑ፣ የአብይ፣ የብልጽግና ወዘተ የሚል ዘመቻ የተከፈተበት ከህዝብ ጋር በማለያያት ለማፍረስ እንዲቀላቸው ነው” በማለት ለአዲስ ሪፖርተር መረጃ ደርሶ መዘገባችን አይዘነጋም።  

ጃዋር እንዳለው ኢትዮጵያ በድሮን ጌም የሚጫወቱ የአምስተኛው ትውልድ ባለሙያዎችን በብዛትና በጥራት ማዘጋጀቷን። በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ አገር ሳይቀር በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠኑ ባለሙያዎች እንዳሏት፣ በሺህ የሚቆጠሩ አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖችን እንደምታመርት ያመለከተው ጃዋር፣ የኤርትራ ኃይሎች አንጋፋ መሆናቸውንና ከቴክኖሎጂ ጋር የተለያዩ መሆናቸውን አመልክቷል። የኤርትራ አምስተኛው ትውልድ በስደት አገሩን መልቀቁን፣ ያለውም የተዘጋበትና ከቴክኖሎጂ ጋር የማይተዋወቅ በመሆኑ ቴርክኖሎጂው ቢገኝ እንኳን ባለሙያ ፍለጋ በውደውጭ እንደሚያዩ፣ እየአደረጉ ያሉትም ይህንኑ እንደሆነ አስታውቋል።

የተለያዩ ስህተቶችና በህግ የሚያስጠይቁ ጥፋቶችን የሰራው ጃዋር መሐመድ “ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግሥት ጋር የነበረው ተቃውሞ መንግሥት ወደ ድርድር እንዲመጣ ለማስገደድ እንጂ ሀገርና የመከላከያ ተቋምን ለማፍረስ አልነበረም” ሲል በተደመጠበት ቃለ ምልልሱ ይህንን አካሄድ የሚያቀነቅኑትን “የማንም ወንበዴ ስብስብ” ብሏቸዋል።  

“…. አሁን ያሳዩን performance ብቃት ለህወሓት ምናምን አይደለም። … ከግብፅም በኩል የነበረው ግምገማ፣ ከሶማሊያ የነበረው ግምገማ ‘መከላከያ ትንሽ ነካ ካረከው ይበተናል’ የሚል ነበር። የሆነው ግን ሌላ ነው”  

ከዚህ ውጥን ጀርባ ያሉትንም ሆነ ተጣማጆቹን “እያንዳዳቸውን አነጋግሬያለሁ” በማለት ያስታወቀው ጃዋር፣ «እኔ ሙሉ ህይወቴን የሰጠሁት ህዝቤ የተሻለ መንግሥትና ልማት እንዲኖረው እንጂ፣ ያለችዋ የተዳከመች ሀገር እስከነ አካቴዋ እንድትፈርስ አይደለም» በማለት ሴራውን ከስር መሰረቱ እንደሚያውቀው ጠቅሶ ይፋ አድርጓል። ጃዋር “ህዝቤ” በሚል አሁን ላይ በተደጋጋሚ ቢናገርም “መንግስት ነኝ፣ ተከበበኩ” በማለት የሰራቸው ጥፍቶችና የተከሰተውን አደጋ በማስታወስ አሁን ድረስ ህዝብ ጀርባውን የሰጠው መሆኑ ይታወቃል። እሱም በሚወቀሳባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በገሃድ ይቅርታም ሆነ ማስተባበያ አልሰጠም።  

በደቡብ አፍሪካው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ወቅትና ከዚያ በኋላ የተወሰኑ በውጭ እና በውስጥ የሚገኙ የታጠቁ ቡድኖች አመራሮች መንግሥት ቢወገድ እንኳን ድርድር እንደማይፈልጉ ማስታወቃቸውን እያስታወሰ ተቃውሞውን ያሰማው ጃዋር፣  እነዚህ ቡድኖች ዋና ፍላጎታቸው የመከላከያ ተቋሙ እንዲፈርስ ብቻ መሆኑን አመልክተዋል።  

«…. የጥምረቱ ዜና ይፋ ከመውጣቱ በፊት በውጭና በውስጥ ያሉትን አመራሮች በአካል አናግሬያቸዋለሁ፤ አካሄዳቸው ለሀገራችን አደገኛ ነበር። ጉዳዩ የአብይን የመቆየት ወይም ያለመቆየት ሳይሆን ሀገር የማቆየት ጉዳይ ነው፤ ሀገር ለማቆየት ደግሞ እንደ ሀገር ያለን ዋናው የጋራ ተቋም መከላከያ በመሆኑ እሱን መጠበቅ ያስፈልጋል።» 

ጃዋር አክሎም፣ እነዚህ አካላት ምንም ዓይነት alternate plan (Plan B) ሳይኖራቸው የአገር መከላከያ እንዲፈርስ አደገኛ አካሄድ ይከተሉ እንደነበር ጃዋር ሲያጋልጥ፣ “በግል ባደረኳቸው ውይይቶች አረጋግጫለሁ” በማለት ነው። ጃዋር ይህንን ሲል በዚሁ ጉዳይ ያነጋገራቸውን በስም አልዘረዘረም። አዲስ ሪፖርተር ጃዋር በህወሃት እና ሻዕቢያ ጥምረት መጀመሪያ በተቋቋመው የአቶ ልደቱ አያሌውና የአቶ ነዓምን ዘለቀ የትርምስ አመቻች የጋራ መድረክ ውስጥ ከገባ በኋላ ይህን አሳብ በመቃወም መለየቱን ዘግበን ነበር።  

በቅርቡም ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት የአገር መከላከያን ቀደም ሲል “የደርግ ጦር” በማለት እንደፈረሰው ሁሉ አሁንም “የአብይ ጦር፣ የብልጽግና ጦር” በማለት ፕሮፓጋንዳ ለመስራት የጋራ መድረኩ አባላት ሻዕቢያ በሚመራቸውና በሚከፍላቸው ሚዲያዎች ሲመደቡ “ጃዋር መመደብ የለበትም” በማለት አመራሮቹ ተቃውሞ ማሰማታቸውን በአዲስ ሪፖርተር በዝርዝር መዘገቡ የሚታወስ ነው። 

 «እኔ ሙሉ ህይወቴን የሰጠሁት ህዝቤ የተሻለ መንግሥትና ልማት እንዲኖረው እንጂ፣ ያለችዋ የተዳከመች ሀገር እስከነ አካቴዋ እንድትፈርስ አይደለም» የሚለው ጃዋር አሁንም መንግስትን እንደሚቃወም ደጋግሞ አመልክቷል። እሱ እንደሚለው መንግስትን መቃወም ማለት ግን የአገሪቱን ቁልፍ ተቋም ለማፍረስ መረባረብ አይደለም። እሱ የህን ቢልም “ጃዋር መከላከያ ላይ የተለጠፈው አገሩን ወዶ ሳይሆን ለወደፊቱ ስልጣኑን ለማመቻቸት ነው” በሚል የማይቀበሉት ይተቹታል።  

“… ኤርትራ በቴክኖሎጂ የአገር መከላከያን መቋቋም አትችልም። በሺህ የሚቆጥወር አጥፍቶ ጠፊ ድሮን ነው እያመረቱ ያሉት፤ ድሮኖቹን እንደ ጌም የሚያዙና የሚጫወቱባቸው ልጆችም አምርተዋል። ኤርትራ ውስን ድሮን ብታገኝም ድሮኖችን እንደጌም የሚጫወቱባቸውና የሚያዟቸው የሰው ኃይል የላትም። የአምስተኛው ትውልድ ሃብቷ ተሰዶ አልቋል። ያላት ጦር ምሽግ ቆፍሮ የሚታኮስ እንጂ ከቴክኖሎጂ ጋር አይተዋወቅም። አገሪቱ ለቴክኖሎጂ የተቆለፈች በመሆኗ በእውቀት ጦርነት ኢትዮጵያን መፎካከር አትችልም….”  

«ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ቢወርዱ እንኳን ሀገርና መከላከያን እናፈርሳለን የሚሉ አካላትን እታገላቸዋለሁ። ይህ ሊታወቅ የገባል” ያለው ጃዋር  የአገር መከላከያ ተቋምን ጥንካሬም አወድሷል። ሲሰጠው የነበረውን የተሳሳተ ግምት ውድቅ መሆኑን አስታውቋል። ። 

የአገር መከላከያን ጥንካሬ በተመለከተ በሰጠው አስተያየት፣ ከተለያዩ አህጉራዊና ክልላዊ ኃይሎች ማለትም እንደ ግብፅና ሶማሊያ «የኢትዮጵያ መከላከያ ትንሽ ነካ ካደረጉት ይበተናል» የሚል የተሳሳተ ግምት እንደነበራቸው የሚያውቀውን ሚስጥር ጠቅሶ አመልክቷል። ጃዋር በየትኛው መድረክ ላይ ይህን የተሳሳተ ግምገማ እንደሰማ ጠያቂው አልጠየቀውም። እሱም አላብራራም።  ነገር ግን ተቋሙ አሁን ያሳየው የአቅም ግንባታና አፈፃፀም የሚደነቅ መሆኑን ጃዋር ተናግሯል።  

«ዓመቱን ሙሉ ጀነራሎችን ስወቅጥና ስነቅፍ የነበርኩ ቢሆንም፣ የመከላከያ ተቋሙን ማዕከላዊ አመራሮችና አቅሙን preserve ማድረግ (መጠበቅ) ተችሏል፤ ይሄ ደግሞ ለግለሰብ (ለዐቢይ) ሳይሆን ለሀገር ህልውና ወሳኝ ነው» ሲል የቀደመ ስህተቱን አርሟል። ጃዋር መሐመድ ሰባት አባላት ያሉበትን የታጣቂዎች ጥምረት “የአገር መከላከያን ለማፍረስ የተቀናጁ የወመኔ ስብሰብ” ብሏቸዋል።  

በጋራ መድረኩ የህወሃት ወኪል ከሆኑት መካከል አንዱ አቶ አባይ ግደይ “ኢትዮጵያ ሶስት ቦታ የምትከፋፈልበት እድል አለ” በማለት ከጦርነቱ መጀመር በፊት መናገራቸው በአዲስ ሪፖርተር መዘገቡ አይዘነጋም። እያደር በተለያዩ አውዶች ይፋ እየሆነ የመጣው ኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ህዝብ ዘንድ መድረሱ ካስከፋቸው መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ልደቱ አያሌው በተከታታይ አቶ ጃዋርን እየዘለፉ ይገኛሉ።  

በግል በከፈቱት የዩቲዩብ አውዳቸውና በተጋባዥነት በሚቀርቡበት አጋር ሚዲያዎች ጃዋርን “ከእኔ ጋር ለመሟገት ፈቃደኛ አልሆነም” በማለት የህዝብን ትግል በማጣጠል ክስ አቅርበዋል። አቶ ልደቱ በተደጋጋሚ “እንሟገት” በሚል ላቀረቡት ጥያቄ “ይህ የሰባተኛ ክፍል የክርክር ጊዜ አይደለም” በማለት ጃዋር ምላሽ ሰጥቷል።  

እሳቸው የሚመሩት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲፋፋም የሚፍለገውን ትርምስ አመቻች ግብረኃይል ባደረገው የመጨረሻ ስብሰባ ላይ ኮረም ባይሞላም መረጃ በመለዋወጥ ሌሎች እስኪገቡ በሚጠብቁበት ሰዓት ጃዋር መሀመድ፣ «የሃሳብ ገበታ» (Hasab Gebeta) የተሰኘው የዩቲዩብ ቻናል አዘጋጅና ባለቤት ሞገስ፣ እንዲሁም ቴዲ አዋሳ ህዝብ ብልጽግና ስለሆኑ ህዝብ እንዳይከተላቸው መመሪያ መሰጠቱን ለአዲስ ሪፖርተር መረጃ ደርሶ ነበር።  

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related