ቁስለኞች ወደ አላና ከረን “ምድሪ ኃይል” ሆስፒታል እየተጓጓዙ ነው፤ “እጅ ለመስጠት እንኳን ጊዜ የለም” – ኤርትራውያን ጥቆማ ሰጡ፤ የኤርትራ ሕዝብ ለነጻነት ተዘጋጅ!

Date:

ለአንድ ኤርትራዊ እስረኛ ሞት እድል ነው። በሞት መሰናበት ቀዳሚ ጸሎት ነው። ለአንድ ኤርትራዊ እስረኛ ሞት የሰርግ ያህል ነው። ይህ ምኞት እስረኞች ምንም ዓይነት አየር ማናፈሻ በሌላቸው የብረት የማጓጓዣ ኮንቴይነሮች (Shipping Containers) እና ከመሬት በታች በተቆፈሩ ጠባብ ክፍሎች ውስጥ ታፍኖ መኖር ከሞት የባሰ በመሆኑ ነው። በቀን እጅግ በጣም የሚግል፣ በሌሊት ደግሞ የሚቀዘቅዝ የቁም ሲኦል ነው፤ እስረኞችን ለረጅም ሰዓታት እጅና እግራቸውን ወደ ኋላ አስሮ በዛፍ ወይም በኮንቴይነር ላይ መስቀልና መደብደብ የተለመደ የቅጣት ዘዴ ነው።እስረኞች ለሳምንታት ወይም ለወራት ጨለማ ክፍል ውስጥ ብቻ በመቆለፍ የፀሐይ ብርሃን እንዳያዩ ይደረጋሉ… ይህ ዘመን ማብቂያው ተቃርቧል ነው እየተባለ ያለው፤

አዲስ ሪፖርተር | አዲስ አበባ |  የኤርትራ መንግሥት ቀደም ሲል ከያዛቸው ቦታዎች በተጨማሪ በይፋ የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቆ ባንዲራ እያውለበለበ የገባውና ወረራ የፈጸመው ፕሬዚዳንት አልሲሲ በጠሩት ስብሰባ ላይ ከመከሩ በኋላ መሆኑን በርካቶች ሲገልጹ “አልሲሲ ጦር አስገቡ” ብለዋቸው እንደሆነ በመግለጽ ነው።

የብርጌድ ነሐመዱ ሥራ አስፈጻሚ አባል አቶ ኪሮስ አሰፋዬ ይህንን አስተያየት ይጋራሉ። እሳቸው እንደሚሉት የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አገዛዝ ቀድሞም የተመሠረተው ለግብጽ ጥቅም ኢትዮጵያን ለማራቆት እንጂ የኤርትራን ሕዝብ ታሳቢ አድርጎ ባለመሆኑ ዛሬ ከግብጽ ትዕዛዝ ቢቀበሉ አይገርምም።

በርካቶች እንደሚሉት ግብጽ፣ ሱዳን፣ ኤርትራና ሶማሊያ ተሰብስበው ወሰኑት ከተባለው ውሳኔ በኋላ፣ የኤርትራ ወታደሮች በአሮጌ ረዥም ካሚዮኖች ተጭነው ወደ ትግራይ የተለያዩ አቅጣጫዎች መዝለቃቸውን ነዋሪዎች መስክረዋል። በርካታ የውጭ ሚዲያዎች “ወረራ ተፈጸመ” በሚል ጽፈዋል።

ይህ ሲሆን መቀለን የተቆጣጠሩት የአገር መከላከያ ሠራዊት እና የትግራይ ሰላም ኃይሎች ሕብረት፣ በጋራ የጀመሩትን ዘመቻ በድል አድራጊነት እየገፉበት ለመሆኑ አዲስ ሪፖርተርን ጨምሮ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ሚዲያዎች እየዘገቡ ነበር። በተመሳሳይ እንደ ጀርመን ድምፅ ዓይነት ሚዲያዎች ደግሞ የኤርትራ ሠራዊት ዓዲግራትን አልፎ ወደ መቀለ እየገሠገሠ እንደሆነ በመዘገብ ዳግም መቀለን ለመቆጣጠር እንደሚችል ዳር ዳር የሚል መረጃ እያሰራጩ ነበር።

“የብርጌድ ነሐመዱ አባል ነኝ፤ ነዋሪነቴ በስዊዘርላንድ ሲሆን፣ ትውልዴ ሰነዓፌ ነው። ይህንን መልዕክት አስተላልፉልኝ” በማለት ለዝግጅት ክፍላችን ማሳሰቢያ አዘል መልዕክት አስተላለፉ።

“አሁን ስልክ ደውያለሁ። ሰነዓፌ፣ ዓዲ ቀይሕና ከዓዲ ቀይሕ ትንሽ ራቅ ብሎ ሃጋዝ የሕክምና ጣቢያዎች በቁስለኛ ተሞልተዋል። ወታደሮች አልቀዋል” በማለት መረጃ ማግኘቱን ያስታወቀው የስዊዘርላንድ ነዋሪ፣ “ምንም እንኳን በስልክ መረጃ ማድረስ ቢቻልም፣ የዓይን እማኞች ላልሰማው ቢያዳርሱም፣ መረጃ የተዘጋበት አብዛኛው ኤርትራዊ ይህንን ኪሳራ እና የልጆቹን እልቂት ስለማያውቅ የኢትዮጵያ መንግሥት ሳተላይት ቴሌቪዥን ሊከፍት ይገባል” ብሏል።

ብርጌድ ነሐመዱ ሥራ አስፈጻሚ አባል “እያንዳንዷን መረጃ እንሰበስባለን” በማለት ለአዲስ ሪፖርተር እንዳሉት፣ የኤርትራ ሠራዊት ረግፏል። “እጅ ለመስጠት እንኳን ዕድል የለም” ያሉት አቶ ኪሮስ፣ የኤርትራ ሠራዊት አባላት የድሮን ራት የሆኑት ገና ከተሽከርካሪ ሳይወርዱ ነው።

ለመንግሥት ቅርብ የሆኑ የማህበራዊ ሚዲያዎች የኤርትራ ወታደሮች በድሮን ሲመቱ የሚያሳይ ቪዲዮ አሳይተዋል። በመረጃው እንደታየው የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ እና ያልተጠበቀ መሆኑ ቢገለጽም፣ በኢትዮጵያ በኩል ግን የአገር መከላከያ ዘመኑን የዋጀ የቴክኖሎጂ ውጊያ እንደሚያደርግ አስቀድሞ ሲገለጽ ነበር።

እንደተባለው የኤርትራ ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ተከትሎ የአገር መከላከያ ተከታታይ የድሮን ጥቃት ማድረሱ ተሰማ፤ የብርጌድ ነሐመዱ ሥራ አስፈጻሚ እንደሚሉት በድሮን ጥቃት የኤርትራ ወታደሮች ከፍተኛ ጉዳት ካስተናገዱ በኋላ ወደ ሰነዓፌ፣ ዓዲ ቀይሕ የተጓጓዙ ቁስለኞች፣ ወደ አላ፣ ከረን “ምድሪ ኃይል” ሆስፒታል፣ ቀይሕ ሆስፒታል መጓጓዛቸውን ምስክሮች ነግረዋቸዋል።

የሕወኃት ኃይሎች፣ የፋኖ እና ሌሎች ጥምረት እንደፈጠሩ የተነገረላቸው ታጣቂዎች በከፍተኛ ደረጃ እንደተጎዱ ያመለከቱት የብርጌድ ነሐመዱ ሥራ አስፈጻሚ፣ ጥቃቱ በኤርትራ አገዛዝ ዘንድ ጉዳቱ ክፉኛ ድንጋጤ መፍጠሩን አስታውቀዋል።

በዚህም ሳቢያ የአገዛዙ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ወደ ዛላንበሳ በመምጣት በጦር አመራሮች ላይ ልዩ ክትትልና የጥርጣሬ ግምገማ ማድረጋቸውን የገለጹት የብርጌድ ነሐመዱ አመራር፣ በሠራዊቱ አመራሮች እና በኢሳያስ መካከል ልዩነት መነሳቱን አመልክተዋል።

የኤርትራ ሕዝብ ጦርነት እየተደረገ መሆኑን ሙሉ በሙሉ ስለማወቁ እና በኤርትራ ውስጥ ሴል እንዳላቸው ለተጠየቁት፣ “ሴላችን ጠንካራ ነው” የሚል ድፍን መልስ ሰጥተዋል። በስልክና በተለያዩ ስልቶች ሕዝቡ፣ በተለይም ወጣቱ እንዳይታፈስ እንዲጠንቀቅ፣ ከታፈሰም ጦር ሜዳ ገብቶ እጁን እንዲሰጥ እየሠሩ መሆኑን ጠቁመዋል።

የሳተላይት ቲቪ ለመክፈት በዝግጅት ላይ እያሉ ጦርነቱ መፍጠኑን የገለጹት የብርጌድ ነሐመዱ አመራር፣ ለወደፊት የኤርትራ ሕዝብ አማራጭ ሚዲያ እንዲያገኝና ስለ አገዛዙ በደንብ እንዲረዳ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል።

ከስዊዘርላንድ በስልክ ለአዲስ ሪፖርተር ጥቆማ የሰጡት የብርጌድ ነሐመዱ አባል፣ ሻዕቢያ በመጨረሻው ሰዓት ላይ ስለሚገኝ የቀድሞውን ስልቱን ለመጠቀም መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

“ሻዕቢያ ዩኒፎርም ቀይሮ የጅምላ ጭፍጨፋ ማድረግና በሌላው ላይ ማላከክ ባህሉ ነው። አሁንም የኢትዮጵያን መከላከያ ልብስ በመልበስ በጅምላ ሰዎችን በመጨፍጨፍ በመከላከያ ላይ በማላከክ ሕዝብን ለማነሣሣት ለመጠቀም ተዘጋጅቷል። ይህንን በመረዳት ቅድመ ዝግጅት ይደረግ” ብሏል።

አቶ ኪሮስ በበኩላቸው “የኤርትራ ሕዝብ ደርሰንልሃል” በማለት ባስተላለፉት መልዕክት አሁን ሻዕቢያ እንዳለቀለት በመረዳት ለለውጥ እንዲዘጋጅ አሳስበዋል።

ጦርነት መጀመሩን የሰሙ የኤርትራ ነዋሪዎች ሥጋት ቢገባቸውም፣ “የመጣው ይምጣ፣ መሮናል” የሚል አቋም እንዳላቸው አቶ ኪሮስ አስታውቀዋል። ባላቸው የስልክና የውስጥ ለውስጥ ግንኙነት ኤርትራውያን ወጣቶች ለአገዛዙ መስዋዕት ከመሆን ራሳቸውን እንዲያቅቡ እየተሠራ መሆኑንም አመልክተዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ለህወሃት የተላለፉ የUAV M6 ድሮኖችና የስለላ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ከነግዢ ሰነዶቻቸው ተማረኩ

ህወሃት በሱዳን ወኪሉ አማካይነት የሸመታቸው ድሮኖች እና የስለላ መሳሪያዎች...

ጃዋር መሐመድ፦«የኤርትራ አምስተኛ ትውልድ ተሰዷል፤ የተረፈውም ተቆልፎበት ከቴክኖሎጂ ተፋቷል፤”

“....ቁጭ ብለው ኢትዮዺያ ስንት ቦታ እንደምትከፋፈል ሳያፍሩ እኮ ነበር ሲነግሩኝ፣ ሲያስረዱኝ...

Beyond the Immediate Horizon: Foundational Milestones for Tigray’s Post-TPLF Political Renewal

" ... Tigrayans will not only ensure a better...