ኦነግ በሻዕቢያ ተገምግሞ የራሱን መግለጫ ራሱ አስተባበለ፤ “በማብራሪያ የተስተባበለው መግለጫ ጅኒው ከጠርሙሱ ወጥቷል እንደማለት ነው” too little too late!!

Date:

አዲስ ሪፖርተር | አዲስ አበባ | የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ የተቃዋሚ ህብረትን «የገንጣዮችና የሽብርተኞች ስብስብ» በማለት መፈረጃቸውን ትከትሎ፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) በአርሲ ለተገደሉት ንጹሃን “ገዳዩ እኔ ነኝ” በማለት ኃላፊነት መውሰዱ በጥምረቱ አባላት ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞና የፖለቲካ ስጋት አሳድሯል። በዚህም ሳቢያ መግለጫው እንዲቀለበስ ዘመቻና ግፊት ሲካሄድ ከርሟል።

በድኑ በቀደመው መግለጫው በአርሲ የተገደሉትን ነጹሃን ለይቶ «እርምጃ ወስጃለሁ» ማለቱ፣ በቅርቡ መንግስት ለመገልበጥ መቋቋሙን ይፋ ላደርገው ጥምረቱ “የውድቀት አዋጅ” እንደሆነበት ተመልክቷል። በአሜሪካ “በሽብርና ጽንፈኝነት” ፍረጃ ውስጥ እንዳይገባ በአባላቱ መካከል ከፍተኛ ውጥረትና የፈጠረው የኦላ መግለጫ በቃል አቀባዩም በድምጽ “አዎ እኛ ነን መገለጫውን ያወጣነው” ማለታቸው በሽብርተኛነት እንፈረጃለን የሚለውን አደጋ ጨምሯል። በገንዘብና በተለያዩ ቁሳቁሶች ሲደግፉ ለነበሩና እየደገፉ ላሉ አካላትም በተመሳሳይ ስጋት የሆነው የኦላ መግለጫ ማስተባበያና የማብራሪያ መግለጫ እንዲዘጋጅለት በስፋት ሲወተወት የነበረው ለዚሁ ነበር።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ / ኦላ) በሻዕቢያ ማስጠንቀቂያ አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ የተገደሉትን ሰዎች በተመለከተ ቀደም ሲል ያሰራጨውን መግለጫ መልሶ ማስተባበሉ እንድተሰማ፣ ” ኦላ ማስተባበያውን የሰጠው መግለጫውን ካወጣበት ቀን ጀምሮ በውጭ አገር የሚገኙ የተቃዋሚ ኃይሎችና የሻዕቢያ ሚዲያዎች ካሰሙት ተቃውሞ በኋላ፣ በሻዕቢያ ባለሥልጣናት በተሰጠ መመሪያ ነው” ትብሏል። የመግለጫውን ማስተባበያ በርካቶች «ጅኒው ከጠርሙሱ ወጥቷል» በሚል የተቹትም ወዲያውኑ ነው።

“ጅኒው ከጠርሙሱ ወጥቷል። መልሶ ማስገባት አይቻልም። የመጀመሪያው መግለጫ በወጣበት ወቅት የነበረው አቋምና በኋላ ላይ የተሰጠው ማስተካከያ፣ በቡድኑና በአጋሮቹ መካከል ያለውን ቀድሞውንም ያልተጣጣመ ትርክት አፍርሶታል” ሲሉ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ያወጣውን የመግለጫ ማብራሪያ በርካቶች ተችተውታል። “የመጀመሪያውን መግለጫ ‘የእኛ ነው’ በማለት ማረጋገጥና፣ ቆየት ብሎ ሌላ ትርጓሜ መስጠት፣ ከጀርባ ያሉ ግፊቶችንና የፖለቲካ ፍላጎቶችን ለታዛቢዎች ይበልጥ ግልጽ እንደሆነም ያመለከቱ ጥቂት አይደሉም።

አንድ ታጣቂ ቡድን ወይም የፖለቲካ ኃይል በአንድ ጉዳይ ላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተለያዩ አቋሞችን ሲያንጸባርቅ፣ የመረጃው ተዓማኒነትና የአቋም ወጥነት ጥያቄ ውስጥ ይገባል። በአንድ በኩል «እርምጃ ወስጃለሁ» ማለት፣ በሌላ በኩል ደግሞ «የተዛባ ትርጓሜ ተሰጥቶታል» ማለቱ፣ በተመልካቾችና በተንታኞች ዘንድ ግራ መጋባትንና አለመተማመንን ፈጥሯል።

በውጭ አገር የሚገኙ የተቃዋሚ ኃይሎችና የሚዲያ አካላት የንጹሃንን ግድያ ዜና ለተለያየ የፖለቲካ ዓላማ ሲጠቀሙበት ስለነበር፣ ኦላ “በአርሲ ነጹሃንን እኔ ነኝ የገደልኩት” ሲል ኃላፊነት መውሰዱ፣ ለነዚሁ አካላት መርዶ ሆኗል። መንግስትን በጋራ ለማስወገድ ሻዕቢያን ጨምሮ ትብብር ለፈጠሩት ከፍተኛ ኪሳራ እና ህብረታቸው የይስሙላ መሆኑን እንዳመላከተ በበረካቶች ዘንድ ሰፊ ትችት ቀርቦበታል። አሁን ድረስ ይኸው ትችት እየቀጠለ ነው። በተለይም በትብብር ውስጥ ያሉ አካላት “የጋራ መስመር የላቸውም” የሚለውን ትችት ያጠናክረ ሲሆን፣ የኦሮሚያ ክልል “ጭፍጨፋውን የፈጸሙት ጽምዶ ብለው የተደራጁት የሻዕቢያ ተላላኪዎችና አሸባሪዎች ናቸው” በሚል ለተሰጠው መግለጫ ማረጋገጫ ሆኗል።

ማብራሪያው በቂ ያልሆነ (too little too late)

በአዲሱ የመግለጫው ማብራሪያ ላይ ቡድኑ «ያልታጠቁ ሲቪሎችን ዒላማ አላደረግንም» እና «እኛ ከወጣን በኋላ ሌሎች ታጣቂዎች ጥቃት ፈጽመዋል» ቢልም፣ ተቺዎች ግን ይህ ማብራሪያ ከመጀመሪያው መግለጫ ጋር የሚጋጩ ነጥቦችን በበቂ ሁኔታ አላብራራም ይላሉ። በተለይም የኦላ ታጣቂዎች ከወጡ በኋላ ጥቃት ፈጸሙ የተባሉትን አካላት ማንነት በግልጽ አለመጥቀሱና ቀደም ሲል «እርምጃ ወስጃለሁ» የተባለበትን አውድ በግልጽ አለማስታረቁ ማስተባበያውን ደካማ ያደርገዋል የሚል ትችት ይቀርቡበታል።

እንደ ተቺዎቹ አመለካከት፣ የመጀመሪያው መግለጫ ከወጣና የቡድኑ ቃል አቀባይ አቶ ጂሬኛ ጉደታም መግለጫውን ካረጋገጡ በኋላ፣ ጉዳዩ በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን፣ በዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡና በተቃዋሚ ኃይሎች ዘንድ የራሱን የፖለቲካ ትርክትና አቋም ይዞ ቆይቷል። ስለሆነም ከቀናት በኋላ የወጣው የማስተካከያ ማብራሪያ ቀደም ሲል የተፈጠረውን የፖለቲካ ጉዳትና የስም መጥፋት ለመመለስ ጊዜው ያለፈበት በመሆኑ፣ ማብራሪያው በቂ ያልሆነ “ቀሽም እና የዘገየ” (too little too late) ሲሉ አጣጥለውታል።

የመጀመሪያው መግለጫ እና የቃል አቀባዩ ምላሽ

በሽርካ ወረዳ ቢርቦፍ (ቦርቢና) ጮሌ ቀበሌ የተፈጸመውን ጥቃት አስመልክቶ ኦነሠ ቀደም ሲል ባወጣው መግለጫ፣ በአካባቢው «እርምጃ» መውሰዱን አረጋግጦ ነበር። በወቅቱ በጥቃቱ ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች ሰላማዊ ሲቪሎች ሳይሆኑ፣ በመከላከያ ሠራዊትና በፀረ-ሽምቅ ኃይሎች ተመልምለው የሚንቀሳቀሱ «የታጠቁ የአማራ ተወላጅ ሲቪሎች» ወይም «የትርፍ ጊዜ ተዋጊዎች» መሆናቸውን ገልጾ ነበር። ለእርምጃው መነሻ የሆነውም ከጥቃቱ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ እነዚሁ የታጠቁ ነዋሪዎች ከገበያ ስትመለስ የነበረች አንዲት የኦሮሞ እናትን በጥይት መትተው መግደላቸው እንደሆነ አስታውቆ ነበር። እንዲሁም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሪፖርትን በማጣጣል «የአገዛዙ ቅጥያ» ሲል ከሷል።

በካናዳ የሚኖሩት የቡድኑ ቃል አቀባይ አቶ ጂሬኛ ጉደታም «መግለጫውን ያወጣነው እኛ ነን» በማለት ኃላፊነት መውሰዳቸውን አረጋግጠው ነበር። ይህን ተከትሎ የፋኖ፣ የትህነግና የሻዕቢያ ደጋፊ ሚዲያዎች «ኦላ በዚህ አቋሙ እንዴት የህልውና ትብብር አካል ይሆናል?» በማለት አውግዘውት ነበር። በሌላ በኩል ግድያው ይፋ መሆኑን ተከትሎ በውጭ አገር ያሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች ልሳኖች መንግሥት ሆነ ብሎ ግድያውን እንደፈጸመና የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ለማጥቃት የተደረገ ዘመቻ እንደሆነ ሲያሰራጩና ለአሜሪካ መንግሥት በማሳወቅ መንግሥትን ለማሳጣት ሲጥሩ ቆይተዋል። የኦላ መግለጫ እና ግድያውን እንደፈጸመ ማመን ይህን ሁሉ ትርክት ገደል ከቶታል። ከምንም በላይ የኦሮሚያ ክልል የሰጠውን መግለጫ “ሃቀኛ” አድርጎ አሳይቷል።

የሻዕቢያ ውሳኔ እና የማስተካከያው ማብራሪያ

የሻዕቢያ ወኪል መሆናቸውን በይፋ የሚናገሩት አቶ ነዓምን ዘለቀ፣ ኦላ ማብራሪያውን ይፋ ከማድረጉ በፊት «መግለጫው እንዲታረምና ማብራሪያ እንዲሰጥበት ከውሳኔ መደረሱን በውስጥ መስመር ነግረውናል፤ ብልጽግና ያሽቃበጠውን ያህል ያፍራል ብለውናል» ሲሉ የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪ ለዋሽንግቶን ዘጋቢ ገልጸዋል።

ይህ ከተሰማ በኋላ ኦላ የጀርመን ድምፅ (DW) የአማርኛ ፕሮግራምና ሌሎች መገናኛ ብዙኃን «የተዛባ ትርጓሜ ሰጥተዋል» በማለት አዲስ ማብራሪያ ይፋ አድርጓል። በማብራሪያውም፣ የትጥቅ ግጭት መኖሩን ማረጋገጡ ባልታጠቁ ሲቪሎች ላይ ለደረሰ ጉዳት ኃላፊነት እንደወሰደ ተደርጎ መዘገቡ የመግለጫውን ዋና አውድ የሳተ መሆኑን፣ የወታደራዊ እንቅስቃሴው ዒላማ ያልታጠቁ ንጹሐን ዜጎች ሳይሆኑ፣ ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጎን በቀጥታ ይሳተፉ የነበሩ የታጠቁ አካላት መሆናቸውን፣ ከራሱ ኃይሎች በተጨማሪ የመንግሥት መከላከያ ሠራዊት፣ የፀረ-አማፂ ኃይሎች፣ ሚሊሻዎችና ሌሎች የታጠቁ ግለሰቦች እንደሚንቀሳቀሱ፣ ተዋጊዎቹ ከአካባቢው ከወጡ በኋላም ሌሎች ታጣቂዎች የተሳተፉባቸው ክስተቶች መቀጠላቸውን ጠቅሶ፣ ቡድኑ ባልነበረበት ወቅት የደረሱ ጉዳቶችን በሙሉ በእሱ ላይ ማላከክ ፍትሐዊ አለመሆኑን ገልጿል።

ሆኖም ኃይሎቹ ከወጡ በኋላ ግድያ ፈጸሙ ያላቸውን አካላት ማንነት በግልጽ አልጠቀሰም። ይህም አቶ ጂሬኛ ቀደም ባሉት ሳምንታት የፋኖ ታጣቂዎች ከአማራ ክልል በመነሳት በወለጋ፣ በሰሜን ሸዋና በአርሲ አካባቢዎች በመግባት በንጹሐን ላይ ጥቃት እንደሚፈጽሙና መንግሥት በዝምታ እንደሚያልፋቸው መክሰሳቸውን የሚያስታውስ ቢሆንም፣ በአዲሱ መግለጫ ግን «ሌሎች ግድያ ፈጽመዋል» ሲል የፋኖን ታጣቂዎች ይሁን ሌላ አካል ግልጽ አላደረገም።

ትችቶችና የፖለቲካ አንድምታዎች

ቡድኑ የራሱን መግለጫ ለማስተባበል መሞከሩ «ጅኒው ከጠርሙሱ ወጥቷል» የሚል ስላቅና «ድርጅቱ ተላላ ነው» የሚል ትችት አስነስቶበታል። ተቺዎች እንደሚሉት፣ ቀደም ሲል ግድያውን ለፖለቲካ ፍጆታ ይጠቀሙበት የነበሩት አካላት፣ ያቋቋሙት ህብረት በአሜሪካው ማርኮ ሩቢዮ «የገንጣዮችና የሽብርተኞች ስብስብ» ተብሎ መፈረጁን ተከትሎ ጫና በመፈጠሩ ኦነሠ መግለጫውን እንዲያርም ተደርጓል።

በተንታኞች ዘንድም ይህ ክስተት ቡድኑን በተመለከተ «በራሱ ያልቆመ፣ የሚታወቅ ዓላማ የሌለው እና ይበልጥ ለከፈለው ወይም ትልቁ ቢደር የሚሠራ ነው» የሚለውን ትችት የሚያረጋግጥ ተደርጎ ተወስዷል። በጉዳዩ ላይ ከጀርመን ድምፅም ሆነ ከመንግሥት አካላት የተሰጠ ይፋዊ ምላሽ እስካሁን የለም።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

Ethiopia and Eritrea Move Troops Towards Badme as Reports of Border Clashes Raise Fears of Wider War

According to the report, in response, the Ethiopian Air...

“ኢትዮጵያዊያን አገራቸውን ለሽያጭ አያቀርቡም” ሻዕቢያ ባዘጋጀው በዋሽንግተኑ ሰልፍ “ክህደት ከነከረባቱ ታየ”

አዲስ ሪፖርተር | አዲስ አበባ |ሻዕቢያ ያደራጀው የዋሽንግተኑ ሰልፍ...

የሃምሳ ዓመት ተረት ፍጻሜ!! False Narrative የተሳሳተ ትርክት አደገኛነት እና የሚያስከትለው ጥፋት – የኢትዮ ሚዲያ ፎረሙ (EMF) ምስክርነት

በተሳሳተ ትርክት ላይ የተገነባ ፖለቲካና ወታደራዊ ስሌት መጨረሻው ሁልጊዜም...

ሻዕቢያ ባደራጀው ሰልፍ አገራቸውን “ወራሪ” ብለው እንዲያወግዙ ባንዶች ያካሄዱት ዘመቻ ከሸፈ

አዲስ ሪፖርተር | አዲስ አበባ |  ሰሞኑን እንዲቀሰቀስ በተደረገው...