ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ በኋላ የኤርትራና የመላው ቀይ ባህር ስጋት እንደሚሆኑ ተደርገው የተደራጁ በርካታ የሱዳን ታጣቂዎችና ኢሳያስ አፈወርቂ መምከራቸው ተሰማ፤ አሜሪካ መረጃው ደርሷታል

Date:

አዲስ ሪፖርተር | አዲስ አበባ | የብርጌድ ንሓመዱ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ “ኢሳያስ በሚፈልጉት አግባብ ከስልጣን የማይወገዱ ከሆነ ከሚረዷቸው አገራት ጋር ሆነው ያደራጇቸው በርካታ ከሽብር ጋር የተያያዙ ታጣቂዎች አሉ። ስጋታችንም ይሄው ነው። ኢትዮጵያ ብዙ ኃላፊነት ይጠብቃታል” በማለት ለአዲስ ሪፖርተር መናገራቸውን በማስታወስ ስብሰባ መደረጉን በሱዳን የሚገኙ የድርጅቱ አባል ጥቆማ ሰጥተዋል። በጥቆማው መሰረት ኢሳያስ አፉወርቂ አስራ ሶስት ከሚጠጉ የሽብር ቡድን አባላት መሪዎች ጋር መክረዋል። ንግግሩ ያስፈለገው በኢትዮጵያ በኩል በይፋ ባልተገለጹ ቦታዎች የድሮን ጥቃት በማየሉ እየተሰማ ባለበት ወቅት ነው።

በሱዳን ውስጥ በኅቡዕ እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ የገለጹ የብርጌድ ንሐመዱ አባል ለአዲስ ሪፖርተር ይፋ ባደረጉት መረጃ መሠረት፣ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በምሥራቅ ሱዳን እና በኤርትራ ድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ አስራ ሶስት የሚጠጉ ቡድኖች አመራሮችን መሰብሰባቸው ሲያስታውቁ ለጊዜው ይፋ ባልሆነ ምክንያት ቦታውን እና ቀኑን ለይተው ግልጽ ለማድረግ አልወደዱም። ይህን ያላደረጉት ምን አልባትም ኢሳያስ አድራሻቸው መታወቁን እንዳያውቁ አስበው ይሁን በሌላ ለማብራራት ፈቃደኞች አለሆኑም።

ምንጮቹ ለአዲስ ሪፖርተር እንደገለጹት፣ የስብሰባው ዋና ዓላማ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሆነ አግባብ ከሥልጣን ከተወገዱ፣ ከእሳቸው በኋላ ኤርትራን፣ ሱዳንን እንዲሁም የቀይ ባሕር ቀጣናን የሚያውክ እንቅስቃሴ እንዲፈጥሩ ታስበው የተደራጁትን የሽብር ኃይሎች የተለየ የስራ ስምሪት መስጠት ሊሆን እንደሚችል አስታውቀዋል። እንደ ብርጌድ ንሐመዱ ምንጮች ከሆነ፣ እነዚህ ቡድኖች የሙስሊም ወንድማማቾች ህብረት አካላት ናቸው።

ሻዕቢያ በግልጽ ስማቸው ከላተገለጸና በገለልተኛ አካላት ካልተረጋገጡ የገንዘብ ምንጮቹ በሚያገኘው ሃብት አደራጅቷቸዋል ከተባሉት ከአስራ ስድስት በላይ “የአሸባሪነት ይዘት ያላቸው” ታጣቂዎች መካከል ዘጠኝ የሚሆኑት የሱዳን ታዋቂ የመንግስት ጋዜጦችን ጨምሮ በተለያዩ ሚዲያዎች ስማቸው ከሙስሊም ወንድማማቾች እና ሌሎች በሽብር ከሚታውቁ አደረጃጀቶች ጋር ስማቸውን ይነሷቸዋል። ድርጅቶቹም

በምሥራቅ ሱዳን ከሱዳን ጦር (SAF) ጎን የተሰለፉና በኤርትራ ስልጠና፣ ትጥቅ ወይም ሌላ ድጋፍ እንዳገኙ በተለያዩ የዜናና የቀጣናዊ ደኅንነት ምንጮች የተጠቀሱ ዘጠኝ ዋና ዋና ታጣቂ ቡድኖች አሉ። ከእነዚህ መካከል በአል-አሚን ዳውድ (El-Amin Daoud) የሚመራው የምሥራቅ ኮርፕስ (Eastern Corps/Eastern Battalion) የተባበረው የነጻነትና የፍትህ ሕዝባዊ ግንባር (UPFLJ) ወታደራዊ ክንፍ ሲሆን፣ በዋናነት ከቤኒ አመር ማኅበረሰብ የተውጣጡ ተዋጊዎችን ይዟል። 

በኢብራሂም ዱንያ (Ibrahim Dunya) የሚመራው የምሥራቅ ሱዳን ነጻነት ኃይሎች (Eastern Sudan Liberation Forces) ደግሞ በኤርትራ ድጋፍ የተመሠረተ ሲሆን፣ ወደ 2,000 የሚጠጉ ከቤኒ አመርና ከሃባብ ማኅበረሰቦች የተውጣጡ ተዋጊዎች እንዳሉት ተዘግቧል።

በተጨማሪም በመሐመድ ታሂር ሱለይማን ቤታይ (Mohamed Tahir Suleiman Betay) የሚመራው የፍትህና ልማት ብሔራዊ ንቅናቄ (National Movement for Justice and Development – NMJD) ከቤጃ ጁሜላብ ማኅበረሰብ የተውጣጣ ታጣቂ ኃይል ነው። 

በሙሳ መሐመድ አህመድ (Mousa Mohamed Ahmed) የሚመራው የቤጃ ብሔራዊ ኮንግረስ (Beja National Congress) እና በኦማር ታሄር (Omar Taher) የሚመራው የቤጃ ታጣቂ ኮንግረስ (Beja Armed Congress) ሌሎች የተጠቀሱ ቡድኖች ሲሆኑ፣ የኋለኛው በጋሽ-ባርካ የስልጠና ካምፕ እንዳለው ተዘግቧል። 

በዘይነብ ካባሺ (Zeinab Kabashi) አስተባባሪነት የሚንቀሳቀለው የቤጃ ኮንግረስ የጋራ አመራር (Beja Congress – Collective Leadership) ከዋናው ድርጅት ተገንጥሎ በኤርትራ ስልጠና የወሰደ አንጃ መሆኑ ተጠቅሷል።

በሼባ ዲራር (Sheiba Dirar) የሚመራው የምሥራቅ ሱዳን ፓርቲዎችና ኃይሎች ጥምረት (East Sudan Parties and Forces Alliance) በፖርት ሱዳንና በቀይ ባሕር ግዛት የሚንቀሳቀስ ታጣቂ ኃይል ሲሆን፣ በሙባረክ ሃሚድ በርኪ (Mubarak Hamid Berki) እ.ኤ.አ. በ2025 የተመሠረተው የምሥራቅ ሱዳን ጋሻ ኃይሎች (East Sudan Shield Forces) ከራሻይዳ ማኅበረሰብ የተውጣጡ ተዋጊዎችን የያዘ ሚሊሻ እንደሆነ ተገልጿል። 

ዘጠነኛው ደግሞ በማብሩክ ሙባረክ ሳሊም (Mabrouk Mubarak Salim) የሚመራው ነጻ አንበሶች ንቅናቄ (Free Lions Movement) ሲሆን፣ ከራሻይዳ ማኅበረሰብ ጋር የተያያዘና በታሪክ ከኤርትራ ጋር ጠበቅ ያለ ግንኙነት የነበረው ቡድን ነው።

በሱዳን በኅቡዕ የሚንቀሳቀሱት የብርጌድ ንሐመዱ አባላት ይፋ ያደረጉት መረጃ በምሥራቅ ሱዳንና በኤርትራ አዋሳኝ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን እንቅስቃሴ እና ቀጣናዊ የደኅንነት አንድምታ የሚመለከት ሲሆን፣ ስብሰባ ስለመደረጉ ከኤርትራ መንግሥት ወይም ስማቸው ከተጠቀሱት አካላት በኩል የተሰጠ ይፋዊ መረጃ የለም። ይሁን እንጂ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በኤርትራና ሱዳን ድንበር የመሸጉ አሸባሪ ኃይሎችን ስጋት እንደሆኑ በተደጋጋሚ ሲያስታውቅ መስማት የተለመደ ነው። የዜናው ባለቤቶች እንዳሉት የቀይ ባህርን ለማተራመስና አፍሪቃ ቀንድን ለማወክ የተደራጁትን ኃይላት እንቅስቃሴ አስመልክቶ ለአሜሪካና በቀጣናው ለሚገኙ እና አግባብ አላቸው ለተባሉ አገራት ሙሉ መረጃ አድርሰዋል። በተለያዩ መድረኮች ትንተና ተስጥቶበታል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related