የፋሲል ቤተ-መንግሥት ውበቱ ዳግም ሲያበራ – ከ60 ሺሕ በላይ ጎብኚዎች ጎንደርን

Date:

አዲስ ሪፖርተር ጎንደር—ከአንድ ዓመት በላይ በፈጀውና በከፍተኛ ጥንቃቄ የተጠናቀቀው ታሪካዊው የፋሲል ቤተ-መንግሥት (ፋሲል ግቢ) እድሳት፣ ከተማዋን ወደ ትልቁ የቱሪዝም መዳረሻነት እያሸጋገራት እንደሚገኝ የጎንደር ከተማ ቅርስ ጥበቃ ቢሮ ለአዲስ ሪፖርተር አስታውቋል። እድሳቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የታየው መነቃቃት አስገራሚ ነው።

ቅርሱ ለጎብኚዎች ከተከፈተ ወዲህ ከ60 ሺሕ በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ዜጎች ቤተ መንግሥቱን መጎብኘታቸውን ለአዲስ ሪፖርተር የተናገሩት ፤በቢሮ ቱሪዝም ልማት ቡድን መሪ አቶ ዓይቼው አዲስ ናቸው አብዛኛው ጎብኚ ወደ ጎንደር ያቀናው የ16ኛው ክፍለ ዘመን ታሪካዊ ቅርስ የሆነው ፋሲል ግቢ ዕድሳቱ የታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩና በአግባቡ መከናወኑን ለማረጋገጥ መሆኑ ገልጸዋል። እድሳቱ ሲጀመር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ቅርሱን ሊያጠፉት አስበው እንደነበር በመጠቀስ በውጭ እና በአገር ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎችና ሚዲያዎቻቸው እድሳቱን ሲያወግዙ እንደነበር ይታወሳል። ከተመረቀም በሁዋላ “ቀለሙ ተቀየረ” የሚል ክስ አሰምተው ነበር።

ሁሉም ተብሎ እድሳቱ ሲጠናቀቅ 56 ሺህ የሚሆኑ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች እና 1,914 የውጭ ቱሪስቶች ቅርሱን ጎብኝተዋል ሲሉ ኃላፊው ተናግረዋል። ቅርሱ ከ1980 ጀምሮ ምንም ዓይነት ጥገናና እድሳት ሳይደረግለት መቆየቱን የጠቀሱት  ቡድን መሪው አቶ ዓይቼው ፣ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበው (1979 ዓ.ም) የቤተ መንግሥቱ እድሳት የቅርስ ጥበቃ ሂደትን ተከትሏል።

ዕድሳቱ የያዛቸው ዋና ዋና ሥራዎችን ሲያብራሩ ፤ ቅርሱ አንዳችም የይዘት ለውጥ ሳይካሄድበት ሙሉ ጥገና የተደረገለት ሲሆን ግቢውን ማስዋብ ፤ የኤሌትሪክ ሀይል መስመር ዝርጋታ ተካቶለት ከድቅድቅ ጨላማ ተላቋል።

የቡድን መሪው አክለውም፣ እድሳቱ መጠናቀቁ በተቀዛቀዘው የቱሪዝም ዘርፍ ላይ ከፍተኛ መነቃቃትን ፈጥሯል። በተለይም በጎንደር ለሚከበረው የጥምቀት በዓል ልዩ ድምቀት እንደሚሰጥ ጠቅሰዋል።

“ከተማችን ጎንደር፣ ከታላላቅ ቅርሶቿ በተጨማሪ፣ ለቱሪዝም ወሳኝ በሆነ መልኩ አስተማማኝ ሰላም የሰፈነባት ከተማ ናት” ብለዋል ኃላፊው። የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ጎብኚዎች ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ መጥተው የአፄ ፋሲለደስን ግምብ ጨምሮ በጎንደር ዙሪያ ያሉትን በርካታ ታሪካዊ መዳረሻዎች እንዲጎበኙ ጥሪያችንን እናቀርባለን ብለዋል።

ፋሲል ግቢ፡ በ1628 ዓ.ም. የተሠራውና 7 ሄክታር የሚሸፍነው ፋሲል ግቢ በውስጡ ቤተ መዛግብት፣ የአፄ ፋሲል መዋኛ፣ ቁስቋም ማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ ራስ ግምብና ደረስጌ ማርያምን ይዟል።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የአዲስ አበባ ሕዝብ የእናት ሀገር ጥሪ ተሳትፎና ኮሎኔል መንግሥቱ

የእናት አገር ጥሪ ከተደረገ በኋላ መላው የአዲስ አበባ ሕዝብ...

ቢሾፍቱ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ፤ ኢትዮጵያን ወደ መፃኤ ዘመን የሚያሻግር የሎጂስቲክስ አብዮት

ኢትዮጵያ ከቢሾፍቱ ሰማይ ስር የኢኮኖሚና የሎጂስቲክስ ካርታዋን እንደገና ለመሳል...

“ጥርስ የሌለው ውሻ” የሆነው የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የዓለም መፃኢ እጣፈንታ

አዲስ ሪፖርተር - ፕሬዛዳንት ትራምፕ አሜሪካን ከተባበሩት መንግስታት ደርጅት...

በዘመነ ትራምፕ ጫና ውስጥ የወደቀችው ሶማሊያ እና ለሶማሌ ላንድ ተስፋን ያለመለመው አዋጅ

አዲስ ሪፓርተር - ከሶማሌላንድ የሉዓላዊነት ጥያቄ እና ከእስራኤል እውቅና...