“ለመንግስት ያቀረብነው ጥያቄ ምላሽ ሲያገኝ ወደ ሙሉ ጦርነት እንገባለን፤ በኢትዮጵያ ብቻ ከዘጠና ሺህ በላይ ኃይል አለን” የብርጌድ ንሓመዱ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

Date:

አዲስ ሪፖርተር ዜና — መግለጫ ከመስጠት ያለፈ አቅም እንዳላቸው የሚናገሩት የብርጌድ ነሓመዱ ስራ አስፈጻሚ አቶ ኪሮስ አስፈሃ፣ በአስራ ሰባት አገራት የሚገኙ ኤርትራዊያን ውክልና ያለው ብርጌድ ንሓምዱ፣ በበዙ መቶ ሽህ የሚቆጠር አቅም እንዳላቸው ይናገራሉ።

ብርጌድ ንሓመዱ በትግራይ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በተመለከተ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጥ፣ ስራ አስፈጻሚው አቶ ንሓምዱ በተለየ ለአዲስ ሪፖርተር በሰጡት ምላሽ፣ የኤርትራውን አምባገነን እና ጨፍጫፊ አገዛዝ ለማስወገድ ከአሜሪካ፣ ካናዳና አውሮፓ እንዲሁም ከመላው ዓለም ግንባር ገብተው ለመፋለም ዝግጁነቱ እንዳለ ጠቁመዋል።

“በኢትዮጲያ ብቻ ከዘጠና ሺህ በላይ ኃይል አለን፣ በዩጋንዳም ከፍተኛ አቅም አለን። እየጠበቅን ያለነው የኢትዮጵያን መንግስት ምላሽ ነው” በማለት ለአዲስ ሪፖርተር የተናገሩት አቶ ኪሮስ፣ ከኢትዮጵያ መንግስት ምላሽ እንዳገኙ አገራቸውን ከጨለማ ወደ ብርሃን የሚቀይርና ከሁሉም ጎረቤት አገራት ጋር በሰቶ መቀበል መርህ መኖር የሚችል መንግስት ለመመሰረት ወዲያውኑ ወደ እርምጃ እንደሚገቡ አስታውቀዋል።

“በሌሎች አገራት ላይ ታጣቂ በማደረጃትና ጦርነት በማስፋፋት አገራችንን እያደቀቀ ያለው የኢሳያስን አገዛዝ ለማስወገድ ሰፊ ርቀት ሄደው እየሰሩ እንደሆነ ያመለከቱት የስራ አስፈጻሚ አባል በቅርቡ ወደ አንድ ወጥ እንቅስቃሴ እንገባለን” ብለዋል።

በህወሓትና በሻዕቢያ መካከል የተፈጠረው እኩይ ስምምነት ለቀጣዩ ከባድ ጦርነት መንስኤ መሆኑን ግንባሩ ዛሬ በሳፋየር ሆቴል በሰጠው መግለጫ ይፋ አድርጓል። በቅርቡ በእስራኤል በቀጣዩ የኤርትራ መንግስት ምስረታ ላይ የመከረ ስብሰባ መካሄዱ የሚታወስ ነው። የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ከስር ቀርቧል።

“በአሁኑ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ከግንባር ህዝባዊ ማዕበል ብርጌድ ንሓመዱ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

ግንባር ህዝባዊ ማዕበል ብርጌድ ንሓመዱ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በትኩረትና በንቃት እየተከታተለው ይገኛል።

ይህንን አስመልክቶ ዛሬ መስከረም 30 ቀን የህዛባዊ ማዕበል ብርጌድ ንሓመዱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ተገኝቷል።

ግብዣችንን አክብራችሁ እዚህ ለተገኛችሁ የህዝብ መገናኛ የሚዲያ አካላት በሙሉ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

ግንባሩ አሁን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ላይ ያለውን አቋምና ስጋት፣ እንዲሁም በመፍትሄው ላይ ያለውን እምነት ያብራራል።

የዚህ አሁን እየተካሄደ ላለው ከባድ ጦርነት መነሻና መንስኤ ከህወሃት የተሳሳተ ምርጫ የመነጨ ነው ብለን እናምናለን።

ከዓለም አቀፉ ስምምነት (ከፕሪቶሪያው ውል) በማፈንገጥ፣ ካለ ህግ ከሚንቀሳቀሰውና ገዳይ ከሆነው የሻዕቢያ አገዛዝ ጋር የፈጠረው “ጽምዶ” (ትስስር) የተሰኘው እኩይ ኪዳን ኢትዮጵያን ለማፍረስ ያለመ ስለነበረ፣ መጪው ጊዜ ከባድ ጦርነትን እንደሚወልድ የታወቀ ነበር።

እኛም ከተመሰረትንበት ጊዜ ጀምሮ ይህንን ስንኮንን ቆይተናል።

በመሬት ላይ ምንም ዓይነት የህዝብ መሰረት የሌለውና ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት የተነፈገው ይህ ስምምነት ወደ ወታደራዊ ጥምረት በማደግ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ለነበሩ ታጣቂ ቡድኖች ስንቅና ትጥቅ በማቅረብ ሻዕቢያ የትግራይን ጦርነት ሲያባብሱት ቆይተዋል።

በዕለት 13-1-2019 ህወሃት በሻዕቢያ አዛዥነት በአፋር በኩል ጦርነት ጀምረዋል

ሻዕቢያ በሩቅ ሆኖ ያደርገው የነበረውን ድጋፍና የጦር መሣሪያ ማስተላለፍ በመቀጠል፣ ባለፈው ሳምንት በአፋር በኩል በኢትዮጵያ ጦርነት ውስጥ መሳተፉን የአልጀዚራ የዜና መረብና የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አወል አርባ ማረጋገጣቸው የሚታወስ ነው። ይህንን የሌላን አገር ለማውደም ድንበር ጥሶ የሚደረገውን የሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት አጥብቀን እንኮንናለን።

የኢትዮጵያ የውስጥ ችግር በሰላም፣ በውይይትና በምክክር እንዲፈታ እንመኛለን።

የጎረቤት አገራትን በመበጥበጥና በመበተን ስልጣኑን ለማረጋገጥና የበላይ ሆኖ ለመውጣት ህልም ያለው ሻዕቢያ፣ ኢትዮጵያ የምትፈርስበትንና የማትረጋጋበትን ሁኔታ ለመፍጠር ተኝቶ አያውቅም።

እነሆ አሁን ደግሞ የጋራ ዓላማና መጻኢ ዕድል የሌላቸውን ታጣቂ ቡድኖች በማሰባሰብ “ሕብረት ለህልውና” የሚል ጥምረት እንዲመሰርቱ አድርጓል።

ይህ በውስጡ የኢሳይያስን ተልዕኮ የሚያስፈጽም ኃይል፣ እነሆ የኢሳይያስ አፈወርቂን ቀጣይ ህልውና ለማረጋገጥ ሲባል ኢትዮጵያን በማብተን ህዝቡንና አገሩን እያደመሰ ይገኛል።

ግንባሩ ይህንን በጽኑ ይኮንናል። ሻዕቢያ በተወካዮቹና በራሱ በህዝባችንና በጎረቤት ህዝቦች ላይ ያደረሰውን ውድመትና እልቂት ስለምናውቅ፣ ይህ እንዳይደገም ከፍተኛ ስጋት አለን።

አገራዊ ተልዕኮ ያለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና የጦርነት ጥምረትን በመቃወም በነጻ መሬት ሰፍሮ የቆየው የትግራይ የሰላም ኃይል ሠራዊት በጋራ በመሆን፣ አገራቸውንና ህዝባቸውን ለማዳን እየከፈሉ ያሉትን መስዋዕትነት ዕውቅና እንሰጣለን፤ ኢትዮጵያን ለማረጋገጥና ሻዕቢያን ጨምሮ የጦርነት ኃይላትን ለማጥፋት እያደረጉት ያለውን የሞትና የሽረት ትግል እንደግፋለን።

ግንባር ህዝባዊ ማዕበል ብርጌድ ንሓመዱ የሁለቱ አገራት ግንኙነት በመስጠትና በመቀበል ላይ የተመሰረተ የጋራ እድገትና ብልጽግና መሆን እንዳለበት አቋሙንና ምኞቱን በተደጋጋሚ ገልጿል። ይሁን እንጂ እነዚህ የጥፋት ኃይላት በስልጣን ላይ እያሉ በሰላም መቀጠል ስለማይቻል፣ እነዚህን ለማሸነፍ የተጀመረው የድል መስመር እንዲቀጥል ጥሪ እናቀርባለን።

እኛ በበኩላችን አስፈላጊውን ዋጋ ለመክፈልና የኤርትራ ህዝብ ከረጅም ዘመን ጭቆና ተላቆ በአገሩ በሰላም እንዲኖር፣ በሕገ-መንግሥት የሚመራ መንግሥት እንዲተከል የጀመርነውን የትግል ጉዞ የመጨረሻ ግቡ ላይ ለማድረስ በመስመር ላይ እንገኛለን። መስመራችን እንዲያሸንፍና የጋራ ጠላታችንን ሻዕቢያን ከስልጣን ለማስወገድ ለምናደርገው ትግል የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉልን እንጠይቃለን።

ውድቀት ለፋሽስቶች! ድል ለለውጥ ፈላጊዎች!”

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የትግራይ ሰላም ኃይሎች ለትግራይ ሚሊሻና ፖሊስ ጥሪ አቀረቡ “ወደ መቀለ ቀርበናል”

አዲስ ሪፖርተር ዜና — የትግራይ ሰላም ኃይሎች ወደ መቀለ...

የአገር መከላከያና የትግራይ ሰላም ኃይሎች በጋራ ወደ መቀለ ድንበር እየተቃረቡ ነው፤

በሰቆጣ አቅጣጫ ከመከላከል ወደ አጥቂነት የተዛወሩት የአገር መከላከያ ሠራዊት...

ኦሮሚያ ስድስት ምክትል ፕሬዚዳንቶች ተሾሙላት፣ ዶ.ር ረሻድ ወደ ኦሮሚያ ዞን መሪነት ተዘዋወሩ፤

"ይህ ትውልድ አሸናፊ ትውልድ ነው፣ እጣ ፈንታውም ማሸነፍ ብቻ...

ህወሃት በቅርቡ ዘመኑ እንደሚያከትም አሜሪካዊ ዲፕሎማት ተናገሩ

አዲስ ሪፖርተር ዜና — ታዋቂ የአሜሪካ ዲፕሎማት በቅርቡ ህወሃት...