አዲስ ሪፖርተር ዜና — የአገር መከላከያና የትግራይ ሰላም ኃይሎች በቅንጅት እያካሄዱት ያለውን የተናበበ ኦፕሬሽን መቋቋም ያቃተው የህወሃት ሰራዊት መበተኑን፣ እጅ መስጠቱን፣ መክዳቱንና ከፍተኛ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ማስተናገዱን ተከትሎ አመራሩ ከፍተኛ ወንጀለኞች ሳይቀሩ ሙሉ በሙሉ እስረኞችን ለቆ መሸሹን ተከትሎ በመቀለ ዘረፋ እየተካሄደ ነው። በነገው እለት ለትግራይ ኮማንድ ፖስት እንደሚቋቋም ታውቋል።
የህወሃት አመራሮች በመቀለ ከተማና አካባቢው ያሉ እስር ቤቶች ውስጥ የነበሩ በነብስ ማጥፋት እና ዝርፊያን ጨምሮ በከፍተኛ ወንጀሎች ተጠርጥረው የታሰሩና ፍርደኞችን ሙሉ በሙሉ ለቆ በመኮብለሉ በአሁኑ ሰዓት ዘረፋ በከተማዋ ውስጥ እየተካሄደ እንደሆነ የትግራይ ሰላም ኃይሎች መረጃ ለአዲስ ሪፖርተር አጋርተዋል።
“በዘረፋው የተሰማሩት የሚታወቁና ወደፊት ራሳቸውን ሸሽገው ማኖር የማይችሉ በመሆናቸው ዝርፊያውን እንዲያቆሙ፣ የዘረፉትንም እንዲመልሱ ማሳሰቢያ እየተሰጠ ነው” ያሉት አመራር በትግራይ ያለው መዋቅርና ህዝብ ሁሉንም ዘራፊዎች እየተከታተለ መሆኑን አመልክተዋል፤
የመንግስት ተቋማትን፣ አገልግሎት መስጫዎችን፣ የህክምና ኬላዎችንና የትምህርት ተቋማትን እየዘረፉ ያሉት በሙሉ በስም የሚታወቁ መሆናቸውን፣ ስማቸውን ጭምር በመጥራት የትግራይ ሰላም ኃይሎች የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በቀጥታ ስርጭት ደጋጋመው ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ እየሰጡ ነው።
“እኔ ከሌለሁ ትግራይ ትፍረስ፣ ስርዓተ አልበኛነት ይሰፍን” በሚል ህወሃት እስር ቤት ከፍቶ ወንጀለኞችን ሜዳ ላይ ሲበትን ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ያስታወሱ፣ ወንጀለኞቹ የሽግግር ጊዜውን ሁለከት በመንሳትና ህዝቡን ሰላም በመንሳት፣ እንዲሁም በመዝረፍ ሰላም እንዲነሱ ታስቦ የተደረገ ቢሆንም፣ ዛሬ ማታ ላይ በቅንጅት ሙሉ በሙሉ ትግራይን በመቆጣጠር ዜናው ይፋ ሲሆን ወነጀለኞችን የማጽዳት ስራ ወዲያው ይጀመራል።
“ትግራይ ለእኛ አዲስ አይደለችም። ጓዳውን ጎድጓዳውን እናውቀዋለን። መዋቅራችን ስራውን እየሰራ ነው። የሚያስቸግር ነገር የለም። ዋናው ስራ አልቋል” ሲሉ ቀጣይ ስራቸ ሰላምና መረጋጋት፣ ጸጥታና የትግራይን የተስተጓጎሉ አገልግሎቶች ማስጀመር ነው” በማለት የትግራይ ሰላም ኃይሎች አመራር ለአዲስ ሪፖርተር አስታውቀዋል። ሙሉ በሙሉ እስኪገቡ ድረስ እንዝረፍ በሚል በሌብነት የተሰማሩ አካላት ራሳቸውን እንዲያቅቡ ድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።
ዛሬ ማታ ላይ ሙሉ በሙሉ መቀለ በቁጥጥር ስር መዋልዋ ይፋ እንደሚሆን ያመለከቱ፣ የአገር መከላከያ፣ የትግራይ ሰላም ኃይሎች፣ የፌደራል ፖሊስና የአገር ሽማግሌዎች የሚካተቱበት ኮማንድ ፖስት እንደሚቋቋም አዲስ ሪፖርተር ሰምታለች።
የትግራይ ሰላምና ለውጥ ፈላጊዎች በሚል የዶክተር አረጋዊ በርሄ ቲዴፓ ሲቀር ሁሉም የትግራይ ተቀናቃኝ ድርጅቶች የመሰረቱት ምክር ቤት በቀጣይ ከብልጽግና ፓርቲ፣ የተለያዩ ሲቪክ ማህበራት እና ሚመለከታቸው የሚካተቱበት ጊዜያዊ የሽግግር አስተዳደር በአስቸኳይ እንደሚመሰርቱ ለመረዳት ተችሏል።
ብልጽግና እንደቀድሞው ሽግግሩን ጥሎ በመውጣት ታዛቢ እንዳይሆን ከምክር ቤቱ ማሳሰቢያ የሰጡ እንዳሉት “ብልጽግና በአዲሱ የሽግግር አወቃቀር ውስጥ ድርሻውን ወስዶ ምን እንደሚሰራ መቆጣጠር፣ ማወቅ፣ መሳተፍና መወሰን አለበት” በማለት ያለፈው ስህተት እንዳይደገም ከወዲሁ አሳስበዋል።
የህወሃት አመራሮችና የአርሚ አዛዦች ወደ ኤርትራ መሸሻቸው በስፋት እየተገለጸ ሲሆን፣ አስቀድመው በሰነአፌ መመሽሸጊያ ማዘጋጀታቸው ሲገለጽ እንደነበር የሚታወስ ነው። ዶክተር ደብረጽዮን ወደ ጎሬላ ተዋጊነት መቀየራቸውን ከትናንት በስቲያ መናገራቸው አይዘነጋም።
ፎቶ በኤአይ የበለጸገ
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






