አዲስ ሪፖርተር | አዲስ አበባ | የኤርትራ መንግስት ከሱዳን የጄኔራል አልቡርሃን ኃይሎች ጋር በመሆን በመቀለ እና በአሶሳ ከተሞች፣ መሰረተ ልማት እና ሰላማዊ ዜጎችን ዒላማ ያደረገ የድሮን ጥቃት ለመሰንዘር መዘጋጀታቸው ተደረሰበት። ሁለቱ መንግስታት ባቀዱት መንገድ ማናቸውም የጥቃት ሙከራ ቢፈጸሙ መንግስት ራሱን ለመከላከል የሚገደድ መሆኑን አመልክቷል። በጥቃቱ ዕቅዱን ለመተግበር አስልጥነው ያስታጠቋቸውን እና የሚላላኳቸውን አካላት እንደሚጠቀሙ መረጃው አጋልጧል።
ሁለቱ አገራት በኢትዮጵያ መሳሪያ ያነሱ ኃይሎችን በማሰባሰብ ጽምዶ የሚባል ጥምረት በማቋቋም በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ሲገቡ ቆይተዋል። ቀደም ሲል ጀምሮ ኢትዮጵያ ላይ መሳሪያ የሚያነሱ ቡድኖችን በማደራጀት፣ በማስታጠቅ፣ እንዲሁም በማስለጠን ኢትዮጵያን ሰላም የመንሳት ስራ ሲሰሩ የነበሩት ሁለቱ አገራት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በገሃድ ኢትዮጵያ ላይ ዘርፈ ብዙ አፍራሽ ተገባራትን ሲያካሂዱ እንደነበር ከተለያዩ ወገኖች በመረጃ የተደገፈ ዜና በአዲስ ሪፖርተርና በተለያዩ ሚዲያዎች ሲገለጽ መቆየቱ አይዘነጋም።
ህወሃት በቅርቡ የጀመረውና በሳምንት ጊዜ ውስጥ ሽንፈት የደረሰበት ህወሃት በየከተሞቹ ጥሏቸው የሄደው፣ የተማረኩበትና ከደበቃቸው ጉድጓዶች፣ መጋዘኖች፣ የዕምነት ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶችና መኖሪያ አካባቢዎች የተገኘው መሳሪያ ለዲፕሎማቶች ይፋ ሲሆን እንደታየው፣ በኤርትራና በሱዳን ወደ ትግራይ የገባው መሳሪያ ብዛት አንድ አገር ለሚኖራት በላይ እንደሆነ መመለከቱ አይዘነጋም። ድሮንና ሮኬቶች፣ ዘመናዊ መድፎችና ታንኮች የተማረኩበት ህወሃት አመራሮቹ የፋኖን ጨምሮ አሁን ላይ ኤርትራ መመሸጋቸው መረጃዎች እየወጡ ነው።
ህወሃት የጀመረው የውክልና ጦርነት አለመሳካቱ ሲታወቅ የኤርትራ መንግስት የሚመራቸው ሚዲያዎች፣ በኢትዮጵያ ስም የሚጠሩ ተቃዋሚዎች፣ እንዲሁም በተለያዩ ስሞች የሚጠሩ ማህበራት የኃይማኖት፣ የብሄር እና ዘር ተኮር የርስ በርስ ግጭት እንዲፈጠር ቅስቀሳ እንዲያደርጉ መመሪያ መሰጠቱን ጠቅሰን በዘገብን ቀናት ውስጥ በሞያሌ የሶማሌና የኦሮሞ ወንድማማች ህዝብ፣ ብዙም ሳይቆይ የአርሲ እልቂት፣ ሰሞኑን ደግሞ የአፋርና የሶማሌ ወገኖችን እርስ በርስ ደም የሚያፋስስ ጦርነት እንዲቀሰቀስ ሁሉንም ዓየነት ተግባራት እንደፈተሙ ተመልክቷል።
“ጥብቅ ሚስጥር” ተብሎ ይፋ የሆነው እና አዲስ ሪፖርተር የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው የኤርትራው አገዛዝ በውክልና ጦርነት ኢትዮጵያን በማተራመስ አካባቢውን ሰላም ለማድረግ ያቀደው ዕቅድ ባለመሳካቱ ንጹሃንን ዒላማ ያደረግ ጥፋት ለመፈጸም ተዘጋጅተዋል።
እንደ መረጃው ኤርትራ መንግስትና የሱዳን የአልቡርሃን ቡድን ፀብ አጫሪነታቸውን አጠናክረው በመቀጠል፣ ሁለቱም ኃይሎች በጋራ አሰልጥነው ያስታጠቋቸውን እና መንግስት “የኢትዮጵያ ፀረ ሰላም ታጣቂዎች” በሚላቸው ሽፋን መቀሌ ከተማንና አሶሳን በድሮን ለመምታት በጋራ ዝግጅት እያደረጉ ነው።
“ይህንን ሰላማዊ ዜጎች ላይ ትኩረት ያደረገ የጥፋት እቅድ የኢትዮጵያ መንግስት ደርሶበታል” በማለት ለአዲስ ሪፖርተር መረጃውን ያካፈሉ እንዳሉት፣ የኤርትራና ሱዳን ዓላማ ሲቪል ህዝብን እና የሲቪል ተቋማትን ማውደም እንደሆነ ያስረዳል።
እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ሲከታተል የነበረው የኢትዮጵያ መንግስት “ሻቢያ እና የአልቡርሀን ቡድን ይህን ጠባ ጫሪነት ባቀዱት መንገድ በትኛውም ዓይነትና ደረጃ ሙከራ ቢያደርጉ ውርድ ከራስ ብሏል” መረጃውን ያካፈሉን እንዳሉት ጥቃት ከተፈጸመ የኢትዮጵያ መንግስት እራሱን ለመከላከል የሚገደድ መሆኑን ብቻ ሳይሆን ተጨማሪ ማስጠንቀቂያም እንዳለው አስታውቀዋል።
የመረጃው ባለቤቶች እንዳሉት ሁለቱ አምባገነን አገዛዞች በተላላኪነት ኢትዮጵያ ላይ በየትኛውም አካባቢ ያሰቡትን ጥቃት ከሞከሩ የሚሰጠው ምላሽ ሁለቱም አገራት ሊገምቱት የማይችሉት እርምጃ ነው። “የከፋና ኢትዮጵያን ነከቶ መትረፍ እንደማይቻል የሚያሳይ ርምጃ እንደሚወሰድባቸው ይወቁት” ያሉት ታማኝ ምንጮች ቀደም ሲል ሜጄር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ የተናገሩትን አስታውሰዋል።
ሜጀር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ በግንቦት 2018 ዓ.ም ከኢቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚዳፈሩ ኃይሎችን «ስንዝር ቢንቀሳቀሱ እንደ ሰም ይቀልጣሉ» ሲሉ አስጠንቅቀው ነበር።
ጄኔራሉ በንግግራቸው ላይ የውስጥ ባንዳዎችና የውጭ ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች በጋራ በመሆን «ጽምዶ» በሚል ስያሜ የጠነሰሱት ሴራ ሀገርን ለማፍረስ የታለመ «ተራ ቅዠት» እና «ክብረ ነክ» ድርጊት መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ጥምረት ለኢትዮጵያ ሰላም አስጊና ሚዛን የሚደፋ አቅም የሌለው መሆኑን አስረድተው፣ የመከላከያ ሠራዊቱ የሀገሪቱን ዳር ድንበርና ሉዓላዊነት ለማስከበር በማንኛውም ሰዓት ሙሉ ዝግጁነት እንዳለውና ማንኛውንም ትንኮሳ በአጭር ጊዜ ውስጥ የመደምሰስ ብቃት እንዳለው በአጽንኦት መናገራቸው አይዘነጋም።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






