ጁቡቲ ውስጥ ባለው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ከ 8 በላይ ኢትዮጵያውያን አሽከርካሪዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸው ተገለፀ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – የረጅም ርቀት አሽከርካሪዎች ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ባሻገር፣ በጁቡቲ ወደብ የጭነት ወረፋ በመጠበቅ ላይ እያሉ በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ሕይወታቸውን ማጣታቸው የኢትዮጵያ የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ማኅበር ለአዲስ ሪፖርተር አስታውቋል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ብቻ ከስምንት በላይ አሽከርካሪዎች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን፣ ለችግሩ ዋነኛ መንስኤ የወረፋ አያያዝ ሥርዓት አለመሻሻሉ እንደሆነ ለአዲስ ሪፖርተር የተናገሩት ፤ የማኅበር ሥራ አስፈጻሚ ፕሬዚዳንት አቶ ዳንኤል ተመቸው ናቸው።

የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች፣ ከጁቡቲ ወደብ ደረቅና ፈሳሽ ጭነቶችን ወደ ኢትዮጵያ ለማጓጓዝ ለቀናት የሚወስድ ወረፋ ለመጠበቅ ይገደዳሉ ያሉት ፕሬዘዳንቱ በዚህ ሳቢያ በጁቡቲ አካባቢ ያለው ከፍተኛ የሙቀት መጠን ለበርካታ ቀናት ሲጠባበቁ የነበሩ አሽከርካሪዎችን ሕይወት እየቀጠፈ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቱ እንደተናገሩት ይህ ሁኔታ ከሚደርስባቸው አላስፈላጊ ወጪ እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተጨማሪ አሽከርካሪዎችን ለሞት እየተዳረጉ ይገኛል።

በሙቀት ምክንያት ሕይወታቸውን የሚያጡ አሽከርካሪዎች አስክሬን ለቤተሰቦቻቸው ለማድረስ የሚጠየቀው ገንዘብ እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ሌላው የችግሩ ገጽታ እንደሆነ አንስተዋል።

ማኅበሩ ይህንን የገንዘብ ችግር እና ተያያዥ ጉዳዮችን ለመቅረፍ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ የገለጹት ፕሬዘዳንቱ የሟቾች ሥርዓተ ቀብር በጁቡቲ እንዲፈፀም እንደሚደረግ አመልክተዋል።

የአሽከርካሪዎችን ሞት እና እንግልት ለማስቀረት ብቸኛው መፍትሔ አሽከርካሪዎች ባሉበት ሆነው የጭነት ወረፋ መያዝ የሚችሉበትን ዘመናዊ አሰራር መዘርጋት መሆኑን አሳስበዋል። ማኅበሩ ከነዳጅ አስመጪዎች ጋር በመሆን የወረፋ አያያዝ ስርዓቱ እንዲሻሻል እየሰራ ሲሆን፣ እስካሁን ለዚህ ለውጥ ፍቃደኛ የሆኑት እና አዲሱን ስርዓት የዘረጉት  ሁለት ኩባንያዎች ብቻ ሲሆኑ እነርሱም ኦይል ሊቢያ እና ቶታል ኢነርጂስ ናቸው።

የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ሌሎች የነዳጅ እና የደረቅ ጭነት ኩባንያዎች የተጠቀሱትን የመፍትሔ ሐሳቦች ተግባራዊ በማድረግ፣ አሽከርካሪዎችን ከዚህ አደጋ እንዲታደጉና ለበርካታ ቀናት ጭነቶችን ለመጫን የሚጠባበቁበትን አስቸጋሪ ሁኔታ እንዲያስቀሩ አሳስበዋል።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“ኦፐሬሽን ኢርቡ ሺኒጋ ፤ “የሰማዕታት ቃል ኪዳን” የጃዋር መሐመድ የህቡዕ ፕሮጀክት 

አዲስ ሪፖርተር - የስጋት ትንታኔ መስጠት እሰጣለሁ ባይ ነው።...

አሜሪካ የጄነራል አልቡርሃን  መንግስትን በሽብርተኝነት ፈረጀች፤ ውሳኔ ወዳጅ ለሆኑት ለኤርትራና፣ለትህነግ መርዶ ሆኗል

ጃዋር መሐመድና አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአልቡርሃን ደጋፊ ሆነው ኢትዮጵያን...

ኢትዮጵያ የUAE “ጉዳይ ፈጻሚ” (proxy)?!

የአፍሪካ ቀንድ የረዥም ጊዜ ቀጠናዊ ጥልፍልፎሽ (regional security complex)...

አስመራና መቀለ “ጽምዶ” የመንግስት ለመንግስት ግንኙነት ተብሎ በይፋ ሊታወጅ እየተመከረ ነው፤

አዲስ ሪፖርተር - በትህነግ የሰዓት አቆጣጠር የጦርነት ማስጀመሪያ ግብአቶች...