አዲስ ሪፖርተር | አዲስ አበባ | በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ግጭት ከተባባሰና ወደ ኢትዮጵያ ከኤርትራ፣ ሱዳንና ሶማሊያ ጋር ወደምትጋራቸው ድንበሮች ከተስፋፋ፣ ግብጽ፣ ኤርትራ፣ ሱዳንና ሶማሊያ “coordinate military and intelligence efforts” የወታደራዊና የመረጃ ሥራዎችን በጋራ ለማስተባበር መስማማታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ዜናውን የተድበሰበሰ ነገር ግን ኢትዮጵያን ተባብረው ለመውጋት በይፋ መስማማታቸውን የሚያረጋግጥ መሆኑን አስተያየት የሰጡን አመልክተዋል።
ይህን መረጃ ለሮይተርስ የሰጡት ሁለት የግብጽ የደህንነት እና አንድ የፖለቲካ ዘርፍ ባለሥልጣን ናቸው፤ ባለስልጣናቱ አራቱ አገራት ግጭቱ ወደ ኤርትራ፣ ሱዳንና ሶማሊያ ድንበሮች ከተስፋፋ የወታደራዊና የመረጃ አቅማቸውን ለማስተባበር መስማማታቸውን ገልጸዋል።
ሮይተርስ እንደዘገበው፣ የአራቱ አገራት መሪዎች በኢትዮጵያ በተቀሰቀሰው ግጭት ዙሪያ እሁድ ዕለት መወያየታቸው ተገልጿል። ምንጮቹ ግን ስለተስማሙበት ጉዳይ ተጨማሪ ዝርዝር አልሰጡም።
ዜናውን የተመለከቱና የቀጠናውን ፖለቲካ የሚከታተሉ ለአዲስ ሪፖርተር እንዳሉት፣ ” የወታደራዊና የመረጃ አቅማቸውን ለማስተባበር መስማማታቸውን ገልጸዋል” ማለት ቢሳካላቸው ኢትዮጵያን ለመውጋት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል እንደማለት ነው።
“ሱዳን እንኳን ሌላውን ክልታጠቃ ለራሷም በእሳት እየተለበለበች ነው፤ ሶማሊያ በኢትዮጵያ አገር መከላከያ ኃይል ድጋፍ የቆመች አገር ናት፤ ኤርትራ ጦርነት ብትገባ ተተኪ ኃይል የሌላት በቁም የሞተች አገር ናት” ያሉት አስተያየት ሰጪ “ሩጫው ለግብጽ የፈጠጠ ጣልቃ ገብነት ይለፍ ለመስጠት እንጂ የተቀሩት እዚህ ግቡ የሚባሉ አይደሉም። ይሁን እንጂ ከኢትዮጵያ የተሸጡ ባንዶች ጋር አገር ለማተራመስና ለመበተን መዘጋጀታቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ነውና የኢትዮጵያ ህዝብ ንቃ” ብለዋል።
የዘወትር ተባባሪያችን የትግራይ ሰላም ኃይሎች አመራር “ያጣላን፣ ያለያየን እና ስደት የወሰደን ጉዳይ ይህ ነው፤ ዜናው ለእኛ አዲስ አይደለም።” በማለት እንደማይሳካላቸው አመልክተዋል።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






