አዲስ ሪፖርተር | አዲስ አበባ | ኤርትራ የህወሓት አመራሮች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የአሰራ አምስት ቀናት ቀነ ገደብ ሰጠች በሚል የተሰራጨው ዜና ሃሰት መሆኑ ታወቀ፤ ዜናው ወደ ሌሎች ሀገራት የሸሹትን እና ለመሸሽ በዝግጅት ላይ ያሉትን አይመለከትም በማለት መረጃውን ይፋ ያደረጉት ለዲፖሎማሲ ማጭበርበሪያና ኢትዮጵያ ላሻዕቢያ ያቀረበችውን ቅድመ ሁኔታ ለማለባበስ እንደሆነም ተመልክቷል።
ይህ የተገለጸው “የኤርትራ መንግሥት ከሰሜን ኢትዮዺያ ግጭት በኃላ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ተሸንፈው ሸሽተው በሀገሪቱ የሚገኙ ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች ኤርትራን ለቀው እንዲወጡ ከአስራ አምስት ቀናት ያልበለጠ ቀነ ገደብ መስጠቱን ቢቢሲ ወታደራዊ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል” በሚል የተሰራጨውን ዜና ተከትሎ ነው።
“የኢትዮጵያ ሚዲያዎችና የማህበራዊ አውዶች የተሰፈረላቸውን ዜና የተርጨላቸውን መረጃ እንዳለ ተቀብለው ከማሰራጨታቸው በፊት የመመርመር ልምድ ያንሳቸዋል” በማለት ዜናውን ያጋሩን ዲፕሎማት እንዳሉት፤ ሻዕቢያ ይህንን ዜና ያሰራው “ኢትዮጵያ ጸረ ሰላም በማለት የመትጠራቸውን ቡድኖች መጠጊያ በመስጠት ያደራጃል፣ ያስለጥናል፣ ያስታጠቃል” በሚል የሚቀርበበትን ክስ ለማስተባበል እንዲያመቸው ነው።
ናይሮቢ ባሉ የሻዕቢያ ኤጀንቶች አማካይነት እዛው ላሉ የህወሃት ደጋፊ የቢቢሲ ቧለሟሎች እንዲደርስ የተደረገው ዜና የፈጠራና የአጀንዳ ማስቀየሻ እንደሆነ የብርጌድ ንሓመዱ የአካባቢው አስተባባሪ ለአዲስ ሪፖርተር አረጋግጠዋል።
“ወታደራዊ ምንጮቹ እንደገለጹት፣ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለህወሃት ሰዎች ትዕዛዙን ያስተላለፉት በቅርቡ ከሩሲያ አስመራ ከተመለሱ በኋላ ነው። ሆኖም አስራአምስት ቀናት ቀነ ገደቡን በተመለከተ ከኤርትራ መንግሥት ይፋዊ ማረጋገጫ አልተሰጠም” በማለት እውነት እንዲመስል ተደርጎ በቢቢሲ የተቀናበረው ሃሰተኛ ዜና “ኤርትራ የህወሃት አመራሮችን ሙሉ በሙሉ ለማባረር ወስናለች” በሚል ኢትዮጵያ የምታቀርበውን የተጨበጠ እና በመረጃ የተደገፈ ቅድመ ሁኔታ ለማለሳለስ እንደሆነ መረጃውን የሰጡት ወገኖች አመልክተዋል።
ይህ የኤርትራ መግለጫ ፀረ ኢትዮዺያ ታጣቂዎችን እና የሽምቅ ተዋጊዎችን በማስታጠቅ እና በማደራጀት እየሰራች ነው፤ በመሆኑም እነዚህን አካላት አሳልፋ ትስጥ በሚል ከኢትዮዺያ ለቀረበው ቅድመ ሁኔታ ኤርትራ የህወሓት አመራሮችን አስወጥቻለሁ ለማለት እየተጠቀመችው ዘዴ ነው የሚል አስተያየቶች እየተሰሙ ባለበት ሁኔታ ዜናው “የተቀነባበረ” እንደሆነ ገልጸው ለአዲስ ሪፖርተር ያደረሱት ወገኖች “ይህን ዜና ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች እንዲያሰራጩት ብዙ ተሰርቷል” ብለዋል።
የሻዕቢያን እና የህወሃትን እንቅስቃሴ እግር በግር እየተከታተሉ እንደሆነ የሚገልጹ የብርጌድ ነሓመዱ አመራር “ሻዕቢያና ህወሃት ተፈጥሯቸው ስለሚታወቅ ዜናው አላስገርመኝም፤ ያስገርመኝ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ዜናውን ሲቀባበሉት ማየቴ ነው” በማለት በድርጅትና በግል የተሰበሰበውን መረጃ ለአዲስ ሪፖርተር አድረሰዋል።
የህወሃት አመራሮችና ተከታዮቻቸው፣ የኤርትራና የትግራይ ድንበር በአዲ ዃላ ንኡስ ዞን የሚገኙ የድንበር መንደሮች ውስጥ እንደሚገኙ በካርታና በሌሎች አመላካች መረጃዎች አስደግፈው ልከዋል።
በዚሁ መረጃ መሰረት በኤርትራ ወገን በመረብ ወንዝ አካባቢ የሚገኙ አምስት መንደሮች በትኩረት ተጠቅሰዋል። በኤርትራ ደቡባዊ ክልል፣ በአዲ ዃላ ንኡስ ዞን ውስጥ ወደ ደቡብና ደቡብ ምዕራብ በመረብ ወንዝ እና በትግራይ ድንበር አቅጣጫ የሚገኙት እነዚህ አምስት መንደሮች የህወሃት ሰዎች ተሸሽገው እንደሚገኙ ጠቁመዋል። በዚሁ መሰረት
1. ክሳድ ዒቃ ከመረብ ወንዝ ዋና የድንበር ማቋረጫ አካባቢ በግምት አምስት ኪሎ ሜትር ርቃ የምትገኝ መንደር
2. ጉንደት ከአዲ ዃላ በደቡብ አቅጣጫ፣ ወደ መረብ ወንዝ ሸለቆ የምትገኝ ታሪካዊ መንደር
3. እንዳ ገርግስ በአዲ ዃላ ንኡስ ዞን ውስጥ፣ በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የምትገኝ መንደር ናት።
4. ዓይላ በእንዳ ገርግስ አካባቢ፣ ወደ ደቡብ ምዕራብ ድንበር አቅጣጫ የምትገኝ መንደር ናት።
5. ገዛ ዓዳባ በእንዳ ገርግስና በዓይላ አካባቢ የምትገኝ መንደር የህወሃት አመአሮች እና ተከታዮቻቸው በሻዕቢያ ፈቃድ ራሳቸውን ሸሽገው እንደሚገኙ ያመለከቱት ወገኖች፣ ሻዕቢያ “ላስወታቸው ነው” በሚል ያሰራው ዜና ይህንን ሃቅ ሊሸፍነው እንደማይችል ገልጸዋል። ሻዕቢያ ከባድ መሳሪያዎቹን ከድንበር በሃምሳና ስልሳ ኪሎሜትር በተራራና ተራራ መካከል ደብቆ በስጋት ውስጥ እንደሚገኝም እነዚሁ ወገኖች አስረድተዋል።
ኤርትራ የህወሃትን ባለስልጥናት ለማባረር አስራ አምስት ቀን መስጠቷን ቢቢሲ ወታደራዊ መኮንኖች እንደነገሩት አድርጎ ሲረጭ፣ የሻዕቢያ ደጋፊ ሚዲያዎች የኢትዮጵያን መንግስት በመክሰስ ዜናውን “ሻዕቢያ ሰላም ፈላጊ ነው” በማለት ያሰራጩት በቅጽበት ጊዜው ውስጥ ነበር።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






