ተከዜን ለመሻገር ያለመ ጦርነት በጠለምት ማይ ዳጉሽ ተቀሰቀሰ፤ የትህነግ ክ/ሰራዊት አዛዥ፣ የሎጂስቲክ ኃላፊና መሳሪያ ተማርኳል

Date:

አዲስ ሪፖተር – በሰሜን ምዕራብ ትግራይ አቅጣጫ ጦርነት መካሄዱ ተሰማ። በጦረንቱ የአርሚ አስራ አንድ ብርጌድ 113 ክፍለ ሰራዊት አዛዥና የሎጅስቲክ ኃላፊዎች መማረካቸውን ምስል አስደግፈው የአዲስ ሪፖርተር የስፍራው ተባባሪዎች አስታውቀዋል።

ወደ ተከዜ ለመሻገር ዕቅድ የነበረው ይህ ውጊያ የተጀመረው በጠለምት ማይ ዳጉሽ ሲሆን በስፍራው የነበረው የመከላከያ ኃይል በውሰደው እርምጃ ለጊዜው መቋጨቱ ታውቋል። በአካባቢው ሃራ መሬት ራሳቸውን የትግራይ የሰላም ኃይሎች ብለው የሚጠሩ ቢኖሩም በውጊያው ላይ ያላቸው ሚና አልተገለጸም።

በምስል ተደግፎ የደረሰን ዜና እንደሚያመልክተው እንደ ብሬል፣ ተቀጣጥይ ፈንጂዎች፣ የተለያዩ የነብስ ወከፍ መሳሪያዎችና የመገናኛ ሬዲዮኖች ተማርከዋል። በቁጥር ያልተገለጹ በውጊያው መሞታቸውንም በመስል ለማረጋገጥ ተችሏል።

ከሰዓት በሁዋላ ላይ የተጀመረው ውጊያ ከሰዓታት በሁዋላ የቆመ ሲሆን በተጠቀሰው አቅጣጫ ሰብሮ ተከዜን ለመሻገር የተነሳው የትህነግ ታጣቂ ገሚሱ በማፈግፈግ ወደ መጣበት አቅጣጫ መመለሱ ታውቋል። ለጊዜው ውጊያው እንደቆመ ለማረጋገጥ ተችሏል።

በተገባደደው ሳምንት “እናመሰግናለን ሽሬ፤ ሰሞኑን ምዕራብ እንሻገር” የሚሉ እናቶች፣ ወልቃይትን ያስመልሳል ለተባለለት ሚሊሻ ምርቃት ሲዘፍኑና የማበረታቻ ፌስቲቫል ሲያካሂዱ እንደነበር ከስፈአው የወጣ የቪዲዮ ምስል በማስደገፍ ይፋ ማድረጋችን የሚታወስ ነው።

ከሳምንት በፊት ጄኔራል ምግበይ “ነባሩን አስተዳደርና የጸጥታ ኃይሉን ትተው ተፈናቃዮችን ብቻ ሊወስዷቸው ነው፤ ስለዚህ በሚቀጥለው ሳምንት ወልቃይትን እናስመልሳለን” ማለታቸውን ስብሰባው ላይ የተገኙ ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም። በዚሁ ንግግራቸው ጄነራሉ ከኤርትራ አስፈላጊ መሳሪያዎች መገኘቱንና የከፋ ነገር ከተፈጠረ የኤርትራ ወታደሮች ጦርነቱ ላይ እንደሚሳተፉ አመልክተው ነበር።

ይህን ባሉ በቀናት ልዩነት ደግሞ በሱዳን የኤርትራ፣ የሱዳንና የትግራይ ሕዝብ አንድ ነው በሚል የጥምረት በዓል መከበሩን የትህነግ ደጋፊ ሚዲያዎች በሰበር ዜና አውጀው ነበር። በዚሁ ጥምረት ላይ የፋኖ መሪ መገኘታቸውም ይፋ ሆኗል።

ጦርነቱን አስመልክቶ በድልም ይሁን በሽንፈት ከትህነግ በኩል በይፋ የተባለ ነገር የለም። ከትህነግ መረጃ የሚያገኙና ሻዕቢያ የሚያንቀሳቅሳቸው የሚታወቁ ሚዲያዎች ይህ እስከተዘገበ ድረስ ያሉት ነገር የለም።

በጦነቱ ወቅት የደረሰውን ጉዳት ከማተም መታቀባችንን ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን። እማኞች ጦርነቱ ሲካሄድ መስማታቸውን ወዲያው መቆሙን ለተባባሪዎቻችን አስታውቀዋል። ዘወትር ተጨማሪ መረጃዎችን እየተከታተልን እናሳውቃለን።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኤፍሬም ማዴቦና ነዓምን በሻዕቢያ በዓል ላይ ታዳሚ በመሆናቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ለኢድ ቀን ተላለፈ፤

አዲስ ረፖርተር ዜና - አባላቶቹ በመበተናቸው መደበኛ ስብሰባውንና ሊያካሂዳቸው...

በሻዕቢያ የሚመራው የእነ ነዓምን ዘለቀ ግብረ ኃይል ተበተነ፤ ስብሰባ፣ ቅስቀሳ፣ ሰላማዊ ስለፍ በይፋ ቆመ፤

አዲስ ሪፖርተር ዜና - በኢትዮጵያ ምርጫ እንዳይካሄድ ለማደናቀፍ ተደራጅቶ...

[ሞዐ ተዋህዶ] አዲስ የድህረ ምርጫ ህዝባዊ አመጽ ዕቅድ በኤርትራ ኤምባሲ ውስጥ ቀረበ

አዲስ ሪፖርተር ዜና - ምርጫ መካሄድ እንደሌለበት በተቀመጠው አግባብ...