የአገር መከላከያና የትግራይ ሰላም ኃይሎች በጋራ ወደ መቀለ ድንበር እየተቃረቡ ነው፤ ህወሃት አስቸኳይ ሽምግልና መጠየቁ ተሰማ፤ በትግራይ ህዝብ መከላከያን እየጠበቀ ነው

Date:

በሰቆጣ አቅጣጫ ከመከላከል ወደ አጥቂነት የተዛወሩት የአገር መከላከያ ሠራዊት እና የትግራይ ሰላም ኃይሎች በጋራ ወደ መቀለ መቃረባቸው ተሰማ። አላማጣን የተቆጣጠረው ኃይል ወደ መሆኒ ለማቅናት አቅራቢያ ከተሞችን እያጸዳና እየተቆጣጠረ ነው። ህወሃት በአስቸኳይ ለሽምግልና እንደሚቀመጥ ጠቅሶ ለአፍሪካ ህብረትና አገባብ ናቸው ላላቸው ኃይሎች ደብዳቤ መላኩ ተሰማ። በጦርነት የተሰላቸው የትግራይ ህዝብ የአገር መከላከያን እይጠበቀ መሆኑም ተሰምቷል።

የቀድሞ የሕወሓት ከፍተኛ ባለሥልጣን ብስራት አማረ፦ “የሰቆጣ አስተዳደር ከተማን ማዕከል ያደረገ አራት አርሚዎች (የአንዱን ስም አላወቅኩትም)፤ አርሚ 22፣ 15፣ 11፣ ፋኖ እና የአገው ታጣቂ ያሉበት ግንባር ነው። የፌደራል መከላከያ ሠራዊትና የትግራይ ሰላም ኃይልን መደምሰስ ነበር ዓላማው። ግን ያጠቃ የነበረው ኃይል አቅሙን ጨረሰ፣ አራገፈ፤ መግፋት እና መቀጠል አልቻለም። ሙትና ምርኮኛ ሆነ፤ የቀረው ተበትኗል። በቃ ከሽፏል፣ ማጥቃት አልቻሉም። በጣም ብዙ ኪሳራ ነው የገጠማቸው፤ ከገመትነው ሞት እና እልቂት በላይ ነው ያጋጠመው” ማለቱን ተከትሎ የተሰማው ዜና እንደሚያመለክተው በሰቆጣ አቅጣጫ እየገፋ ያለው ኃይል ሳምሬ ገብቷል።

ሳምሬ ከመቀለ በሃምሳዎቹ ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ በመሆኑ፣ በሕወሓት ኃይሎች ዘንድ መረበሽና የሽሽት ዕቅድ እንዲያመቻች የታዘዘው ኮሚቴ በሥራ መወጠሩን የትግራይ ሰላም ኃይሎች የመረጃ ክፍል ለአዲስ ሪፖርተር አስታውቋል።

“ሕወሓት በቅርቡ ወደ ሙሉ ሽፍታነት ይቀየራል። መሠረተ ልማት የሚያፈርስ፣ አሸምቆ የሚያጠቃ ኃይል ይሆናል። ከዚህ ውጭ ሌላ ዕድል የለውም” በማለት ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ የሆነ የቀድሞ ከፍተኛ መኮንን ለአዲስ ሪፖርተር መናገራቸው አይዘነጋም።

ብስራት አማረ በቃለ ምልልሳቸው፦ “አንዱ ግንባር ተኩላሽ የሚባለው የአላማጣ አካባቢ ነው። በዚያ አቅጣጫ አርሚ 31፣ 24 እና 26 አሰልፏል። ይህ ግንባር ጥሶ ማለፍ ከቻለ ወልዲያ ነው የሚገባው። አምስት ቀን ተዋጋ፣ መጣስ አልቻለም… ምርኮኛና ሙት ሆነ። የተረፈውም የመበተን ዕድል አጋጥሞታል። የኋላቀሩ TPLF ማጥቃት አብቅቷል። አሁን የሚጠበቀው የፌደራል መንግሥት ፀረ-ማጥቃት ነው። አልቋል! ወደ አዲስ አበባ መሻገር፣ ወልዲያን መያዝ አልተቻለም” በማለት የአላማጣን ግንባር መረጃ አካፍለዋል።

የሕወሓት ሚዲያዎች በበኩላቸው “አላማጣን የለቀቅነው አውቀን ነው” በማለት ከትናንት ጀምሮ እያስተጋቡ ነው። እንደ እነዚሁ ሚዲያዎች ከሆነ የሕወሓት ጦር በሰቆጣም ሆነ በአላማጣ አቅጣጫ ድል እየቀናው ነው።

የዋግ ኽምራ አስተዳደር፣ አገር መከላከያ እና ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች ነዋሪዎች ይፋ ባደረጓቸው መረጃዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠራዊት መማረኩን፣ ሙትና ቁስለኛ መሆኑን፣ በርካታ የጦር መሣሪያ መማረኩንና የተረፈው ኃይል ተቆርጦ እና በየሥራቻው ተበትኖ እንደሚገኝ እየገለጹ ነው።

በአላማጣ አቅጣጫ የአገር መከላከያ እየገፋ መሆኑን ያመለከቱ የአካባቢው ተወላጆች፣ ገርጀሌ ታኦ ከተማ የገባው መከላከያ ወደ ሂጀራ ገስግሶ ጭሎታ ሚካኤልን ለመቆጣጠር ከጫፍ ላይ ነው።

ለመቀለ ቅርብ ርቀት የሆነችው የመሆኒ ከተማ ላይ የሕወሓት ኃይሎችን መልሶ ለማደራጀት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን የገለጹት የመረጃው ባለቤቶች፣ በሌላ በኩል የተበተነው ኃይል እጁን እያሰጠና የትግራይ ሰላም ኃይሎችን እየተቀላቀለ መሆኑን አመልክተዋል።

የአገር መከላከያና የትግራይ ሰላም ኃይሎች ወደ መቀለ እየተጠጉ ባለበት በዚህ ወቅት በዶክተር ደብረጽዮን የሚመራው ህወሃት “አስቸኳይ ሽምግልና እቀመጣለሁ” በማለት ለአፍሪካ ህብረትና አግባብ ላላቸው አካላት ደብዳቤ መጻፉን የአዲስ ሪፖርተር ምንጮች አስታውቀዋል። ምላሹ ምን እንደሆነ በይፋ ባይገለጽም ህወሃት የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግብሮ ወዲያው የሚያሳይ ከሆነ አሸማጋዮቹ መንግስትን ሊያነጋገሩ እንደሚችሉ ምንጮቹ አመልክተዋል። የተባበሩት መንግስታትም ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥረት ላይ መሆኑን ማመልከቱ አይዘነጋም።

በትግራይ ጦርነት የሰለቻቸው ሰላማዊ ዜጎች መከላከያ እስኪገባ በናፍቆት እየጠበቁ መሆናቸውን ጠቅሰን ባለፈው ሳምንት መዘገባችን አይዘነጋም። ያነጋገርናቸው እናቶች የመከላከያ ሰራዊት መቀለ መድረስ በናፍቆት የሚጠበቅ መሆኑን ሲናገሩ በበኩላቸው የሚደረገውን ሁሉ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን በማመልከት ነበር።

ከሁለት አቅጣጫ ወደ መቀለ የሚደረገው ማጥቃት እንዳለ ሆኖ፣ በአፋር ግንባር የሻዕቢያን ሙሉ አጀንዳ ይዘው እየተታኮሱ ያሉት የሕወሓት እና የአፋር አጉጉሞ ታጣቂዎች ላይም ተመሳሳይ ድል እየተጎናጸፉ ያሉት የአገር መከላከያ፣ የትግራይ ሰላም ኃይሎችና የአፋር ሚሊሻ በጋራ ወደፊት እየገፉ ነው።

በዚህ የተጣመረው ኃይል በመቀናጀት ባካሄደው የመልሶ ማጥቃት ውጊያ በአፋር ግንባር የአበርገሌ ወረዳ መቀመጫ የሆነችውን ኒሯቅን ተቆጣጥሮ ወደፊት እየገፋ መሆኑ ታውቋል።

የሀገርን ሉዓላዊነትና የሕዝብን ሰላም ለማስከበር በተሰማራው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እንዲሁም በትግራይ ሰላም ኃይሎችና የአፋር ሚሊሻዎች በጋራ እየተደረገ ባለው መልሶ ማጥቃት፣ ከፍተኛ የሰው ማዕበል በማሰለፍ ጥቃት ለመሰንዘር የሞከሩት የሕወሓት፣ የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አዴን) እና የፋኖ ታጣቂዎች ከባድ ኪሳራ ማስተናገዳቸው ታውቋል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊቱና የትግራይ ሰላም ኃይል ባሳዩት ከፍተኛ የውጊያ ብቃትና የተቀናጀ አመራር ታጣቂ ቡድኑ በጽኑ እንዲመታ የተደረገ ሲሆን፣ የሀገር መከላከያ በአሁኑ ወቅት የጭላ አበርገሌ እና የሳምሬ ከተሞችን ሙሉ በሙሉ ነፃ እያወጣ በመገስገስ ላይ መሆኑ ታውቋል።

በዚሁ አደገኛ ሽንፈት ሳቢያ በ“ትብብር ለህልውና” ኃይሎች መካከል ከፍተኛ እርስ በርስ ግጭትና መበታተን የተከሰተ ሲሆን፣ ታጣቂዎቹ መሣሪያቸውንና ትጥቃቸውን እየጣሉ ከውጊያው ቀጠና በመሸሽ ላይ መሆናቸውን ምስክሮች አመልክተዋል።

ይህንኑ ሽንፈት ተከትሎ ወደ አፋር ክልል ገብተው በአፋር ሕዝብ ላይ አሰቃቂ ጥቃቶችን እና ግፎችን መፈጸማቸውን በምስል አስደግፈው ያሰራጩ እንዳሉት፣ ይህንን ግፍ ሲፈጽሙ የነበሩት አርሚ 50 እና አርሚ 92 ከአፋር አጉጉሞ ታጣቂዎች ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ገልጸዋል።

በሁለቱ ቡድኖች መካከል የተፈጠረው ግጭት የወያኔ ታጣቂዎች በኤርብቲ ከተማ ሕዝብ ላይ በፈጸሙት ግፍና ባደረሱት የመሠረተ ልማት ውድመት ሳቢያ ሕዝቡ ተቃውሞ በማስነሳቱ፣ የአጉጉሞ ታጣቂዎች የወያኔ ታጣቂዎች ከክልላቸው እንዲወጡ በመጠየቃቸው አስቀድመን በማኅበራዊ ገጻችን መዘገባችን አይዘነጋም።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ህወሃት በቅርቡ ዘመኑ እንደሚያከትም አሜሪካዊ ዲፕሎማት ተናገሩ

አዲስ ሪፖርተር ዜና — ታዋቂ የአሜሪካ ዲፕሎማት በቅርቡ ህወሃት...

ስታሊን ገብረሥላሴ ባሰራጨው የሽብር ዜና በአሜሪካ ሕግ እርምጃ እንዲወሰድበት ጥሪ ቀረበ፤

በአሜሪካ የፌደራል ህግ መሰረት ኤርፖርቶችን እና የአቪዬሽን መሰረተ ልማቶችን...