“ይህ ትውልድ አሸናፊ ትውልድ ነው፣ እጣ ፈንታውም ማሸነፍ ብቻ ነው” ሽመልስ አብዲሳ
አዲስ ሪፖርተር ዜና — ኦሮሚያ ስድስት ዞን ሆኖ ተዋቀረ። የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ለስምንት ዓመታት ያገለገሉት ዶ/ር ረሻድ ከማል በምክትል ፕሬዚዳንትነት ማዕረግ ወደ ኦርሚያ ዞን ሲዘዋወሩ፣ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ በመሆን ተክተዋቸዋል። ሽመልስ አብዲሳ በመንበራቸው የሚቀጥሉ ሆነዋል።
የዶ/ር ረሻድ ወደ ኦሮሚያ ዞን መዛወራቸው ዛሬ በጨፌ ኦሮሚያ አዲስ መንግስት ምስረታ ላይ ይፋ ሲደረግ ነው የተኳቸው ወ/ሮ ጫልቱ መሾማቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይፋ ያደረጉት። ኦሮሚያን ስድስት ዞኖች በሚያደርገው አዲስ መዋቅር ሹመት ከተሰጣቸው ስድሰት ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑት ዶ/ር ረሻድ በሚዲያ የሚወደዱ ባለስልጣን ነበሩ። የሚተኳቸው ወ/ሮ ጫልቱ የቤቶች ልማትንና የሚዲያዎችን ግንኙነት ያስቀጥላሉ ወይም ስራቸውን ብቻ ይሰራሉ የሚለው በጉጉት የሚጠበቅ ሆኗል። አዲስ ሪፖርተር ዶክተር ረሻድ ወደ ኦሮሚያ ሄደው ቢሯቸውን በጅማ እንደሚያደርጉ አስቀድማ መዘገቡ አይዘነጋም።
አቶ ከፊያለው ተፈራ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት እና የጨፌው የመንግሥት ተጠሪ ሆነው በይፋ ተሹመዋል። ቀደም ሲል ኃላፊነቱን ይዘው የነበሩት አቶ አወሉ አብዲ ተነስተዋል። አቶ አወሉ የአቶ ሽመልስ ምክትል በመሆን ክልሉን በከፍተኛ አመራርነት ያገለገሉና በቀጥታ ከወርዳ አስተዳደርና ከንቲባዎች ሹመት ጋር ግንኙነት የነበራቸው ባለስልጣን ነበሩ። እሳቸውን የተኳቸው አቶ ከፍያለው ሰፊ ስራ የሚጠብቃቸው እንደሆነ ስለ ታች አደረጃጀት ሙስናና ብልሹ አሰራር የሚናገሩ አመልክተዋል። ኦሮሚያ ብቻ ሳይሆን በመላው አገሪቱ ሌብነት፣ ብልሹ አሰራርና መልካም አስተዳደር ዋና የመንግስት በሽታ እንደሆነ ፓርቲው ራሱ መገምገሙ ይታወሳል።
ከመስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የኦሮሚያ ክልል በዞን አደረጃጀት ላይ ባደረገው ሪፎርም 21 የነበሩትን ዞኖች ወደ 6 መቀነሱን አስታዉቋል፡፡
የተደረገውን ሪፎርም አስመልክተው መግለጫ የሰጡት የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ ጉዮ ዋሪዮ የተደረገው አደረጃጀት የመንግስት አገልግሎቶችን በቅርበት ለማድረስ ነው ብለዋል።ከዚህ ቀደም በቀበሌ አደረጃጀት ላይ የተሰሩ የሪፎርም ስራዎች ውጤታማነታቸውን ይበልጥ ለማረጋገጥ ያግዛልም ብለዋል።
በዚህ መሰረትም አዲሱ አወቃቀር ምስራቅ ኦሮሚያ፣ ማእከላዊ ኦሮሚያ፣ ምእራብ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ምእራብ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ በሚል መዋቀራቸውን አስታውቀዋል።
ዜናውን የሰሙ በኦሮሚያ ስልጣንን ወደ ታች እንዲወርድ መደረጉ የተነዛዛና አንድ ቦታ የተከማቹ አሰራሮችንና የተነዛዛ ቢሮክራሲን ለመቅረፍ እነድሚጠቅም አመልክተዋል። በየዞኑ ጸጥታ ለማስከበርና ሰላም ለማስፈንም እጅግ የጎላ አስተዋጾና ተጠያቂነትን ለማስፈን ጉልህ ሚና እነሚጫወት አመልክተዋል።
የጨፌ ኦሮሚያ 7ኛ የጨፌ ስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የመጀመሪያ ጉባኤ የክልሉ አስፈጻሚ አካላት ሹመትን ሲያጸድቅ ይፋ እንዳደረገው፣ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የተሾሙት ስድስት ተሿሚዎች ናቸው። እነሱም
1. አብዱረህማን አብደላ – በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ
2. አቶ መስፍን መላኩ – በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ
3. ዶ/ር ረሻድ ከማል – በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ
4. ዶ/ር መንግስቱ በቀለ – በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ
5. አቶ አህመድ ኢድሪስ – በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ
6. አቶ አህመድ ሃጂ- በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ
በተጨማሪም
7. ዶ/ር ቶላ በሪሶ -የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ
8. አቶ ጉዮ ዋሪዮ- የፍትህ ቢሮ ኃላፊ
9. ዶ/ር አብዱልአዚዝ ዳውድ- የገንዘብ ቢሮ ኃላፊ
10. አቶ ተስፋዬ ቱሉ- የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
11. ዶ/ር አብዲ ዩያ- የእቅድና ልማት ቢሮ ኃላፊ
12. ዶ/ር ቡልቶሳ ሂርኮ- የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
13. ፕሮፌሰር ነጻነት ወርቅነህ- የጤና ቢሮ ኃላፊ
14. አቶ ተሾመ ቦጋለ-የግብርና ቢሮ ኃላፊ
15. ዶ/ር ነመራ ገበየሁ- የማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ
16. አቶ ታረቀኝ ቡልልታ- የኢንተርፕራይዝና አንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ
17. ዶ/ር አደሬ አሰፋ- የንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ
18. ወ/ሮ መሰረት አሰፋ- የመሬት ቢሮ ኃላፊ
19. ወ/ሮ ሰዓዳ አብዱረህማን- የሴቶችና ማህበራዊ ቢሮ ኃላፊ
20. አቶ ጥላሁን ወርቁ- የከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ
21. ዶ/ር አያንቱ ጉተታ- የፈጠራና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ
22. ወ/ሮ እልዳና ሱሌማን- የቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
23. አቶ ቲጃኒ ናስር- የሰላም ቢሮ ኃላፊ
24. ወ/ሮ ሮዛ ቢያ- የባህልና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
25. ኢንጂነር ግርማ ረጋሳ- የመስኖና አርብቶ አደር ቢሮ ኃላፊ
26. ኢንጂነር ሃቢብ ቁምቢ- የመንገድና ሎጂስቲክስ ቢሮ ኃላፊ
27. ኢንጂነር ማሪያ ጉታ- የውሃ ቢሮ ኃላፊ ሆነው በጨፌ ኦሮሚያ ተሹመዋል። ሹመቱ እንደሚያመለክተው ክልሉ የአስተዳደር መዋቅሩን ከመቀየሩ ባሻገር፣ አዳዲስ ተሿሚዎችን ወደፊት ማምጣቱ የሚጠበቅ እንደሆነ በርካቶች ተናግረዋል። ከምርጫው በኋላ ፐሬዚዳንት ሽመልስ “ይህ ትውልድ አሸናፊ ትውልድ ነው፣ እጣ ፈንታውም ማሸነፍ ብቻ ነው።”
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






