ህወሃት በቅርቡ ዘመኑ እንደሚያከትም አሜሪካዊ ዲፕሎማት ተናገሩ

Date:

አዲስ ሪፖርተር ዜና — ታዋቂ የአሜሪካ ዲፕሎማት በቅርቡ ህወሃት ዘመኑን እንደሚጨርስ አመልከቱ። በምስራቅ አፈሪቃ ብዙ ልምዳ ያላቸውና ሞቃዲሾ ተቀምጠው የአገራቸውን ተልዕኮ ሲፈጸሙ የነበሩት ዲፕሎማት ይህን ያሉት ዋሽንግቶን በተካሄደ ስብሰባ ላይ በጎንዮሽ ውይይት ላይ ነው። የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ ስብሰባው ላይ የነበሩና ዲፕሎማቱን ያነጋገሩትን ጠቅሶ እንዳለው በአሜሪካን እሳቤ ህወሃት አብቅቶለታል።

የሶማሊላንድ መሪ በተገኙበት የዕውቅና ድጋፍ ማሰባሰቢያ ስብሰባ ላይ የተገኙት ዲፕሎማቱ እንዳሉት፣ ህወሃት በተደጋጋሚ ጊዜ ቢመከርም አልሰማም። በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደርን ገፍተው፣ የአፍሪካ ህዝብረት አደራዳሪን ሰድበው ወደ ጦርነት የገባው ህወሃት፤ የዘመኑን መጠናቀቅ ስለተረዳ ኤርትራ ውስጥ ቤዝ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

“ተመክሯል አልሰማም፤ ተዋግቶ ማሸነፍ አይችልም፤ ቀደም ሲል የነበረው ድጋፍ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የለውም፤ የገንዘብ አቅሙም ተመናምኗል” ያሉት ዲፕሎማቱ፣ ቀደም ሲል የነበረውን የዲፕሎማሲ መስመሮች ቆራርጦ ከጥቅም ውጭ እንዳደረጋቸው አመልክተዋል።

“አሁን ላይ በየትኛውም የአሜሪካ መዋቅር የሚሰማቸው የለም። እንደ ቀድሞም የሚያስተናግዳቸው የለም” በማለት ህወሃት ቀደም ሲል መንግስት እያለ የገነባው የዲፕሎማሲ መስመር መበጣጠሱን ያመለከቱት ዲፖሎማቱ፣ ሰሞኑን ህወሃት የከፈተውን ውጊያ ተከትሎ ከየአቅጣጫው የደረሰበት ውግዘት የዚሁ ማሳያ እንደሆነ አስረድተዋል።

ከምንም በላይ ከኤርትራ አምባገነን መሪ ጋር የፈጸሙት ውለታ የዲፕሎማሲው ውድቀታቸውን እንዳፋጠነው ዲፕሎማቱ ተናግረዋል። ህወሃት ሰነአፌ ኤርትራ ማፈግፈጊያ መገንባቱን እንደ አንድ ሌላ የውድቀቱ አመላካች አድርገው ወስደዋል። አክለውም “ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ በተጨማሪ አሸባሪ ከሱዳኑ አልቡርሃን ጋር ሲያብሩ ያኔ አብቅቶላቸዋል” ብለዋል።

ስለጦርነቱ ተጠይቀው “በዛ ቢባል እስከ መጪው ጃንዋሪ ህወሃት ህይወቱ አይኖርም” ሲሉ ግምገማቸውን አኑረዋል። ዲፕሎማቱ አዲስ ትፈጠረ በተባለው ጥምረት ውስጥ ስላሉት ድርጅቶች ያነሱት ነገር የለም።

ህወሃት ከትግራይ ድንበር ወደ ሰነአፌ የሚያስገባ ጥርጊያ መንገድ ሰርቶ ከሻዕቢያ ባለስልጣናት ጋር ማስመረቁ አይዘነጋም። በአሁኑ ሰዓት የህወሃት የሎጂስቲክ ዋና ማዕከል ሆኖ እንምዲያገለግል ተደረጎ ማሰራቱም በተለያዩ ሚዲያዎች እየተገለጸ ነው። በቅርቡ ወደዚያው ያመሩ ከፍተኛ አመራሮች መኖራቸው መዘገቡ አይዘነጋም።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related