አዲስ ሪፖርተር ዜና — የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መሰከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ የሾማቸው ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ የቀድሞው ስራ አዳዲስ የሽግግር ጊዜ ውሳኔ ማሳለፋቸው ተገለጸ። ውሳኔውን ያሳለፉትበት ዝርዝር ምክንያት አልተገለጸም። “በሽግግር ወቅት ተመሳሳይ ውሳኔዎች የሚጠብቁና ጤነኛ ጉዳይ ነው” በማለት አንድ የተቋሙ ኃላፊ አስታውቀዋል።
አዲሷ ስራ አስፈጸሚ በደብዳቤ “አዲስ አሰራር እስኪዘረጋ …” በሚል በአንዳንድ አሰራሮች ላይ ማዕቀብ ያደረጉት በትናንትናው ዕለት በጻፉት ደብዳቤ ነው። ስራ አስፈጻሚዋ ይህን ሲወስኑ በዝርዝር በደብዳቢያቸው ላይ ያስቀመጡት ምክንያት የለም። በዛሬው ዕለት ፕሮጀክቶችን እየተዘዋወሩ መጎብኘታቸውም ተመልክቷል።
ከኪሳራ ተነስቶ ወደ ትርፋማነት መሸጋገሩ በጥንካሬ የሚነሳለት የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ የመሩት ዶክተር ረሻድ ወደ ኦሮሚያ ክልል በምክትል ፕሬዚዳንትን መዛወራቸውን ጨፌው ይፋ ባደርገው የሹመትና የአዲስ መንግስት ምስረታ ሰነ ስርዓት ላይ ማስታወቁ አይዘነጋም።
ስራ አስፈጻሚዋ የዜሮ ፋይናንስ ፕሮጀክቶች፣ የቤት ኪራይ ውል፣ የመሬት ጥያቂዎች፣ ማንኛውም የንብረት ግዢና ክፍያዎች፣ እና ተመሳሳይ ጉዳዮችን ለጊዜው እንዲታገዱ ማዘዛቸው አዲስ ነገር እንዳልሆነ ስማቸውን መጥቀስ ያልፍለጉ አንድ የተቋሙ ኃላፊ አመልክተዋል።
በሽግግር ወቅት አዳዲስ ኃላፊዎች ርክክብ እስኪጨርሱና በቂ መረጃ እስኪይዙ ጊዚያዊ ክልከላ ማድረግ የተለመደ አሰራር መሆኑን ያመለከቱት ኃላፊው “አዲሷ ተሿሚ በፕሮጀክት ጉብኝታቸው ወቅት ባዩት ስራ ተደስተው አበረታተዋል” በማለት የተጀመሩ ስራዎች እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






