“ኢትዮጵያ ወራሪ አይደለችም” የአፋር ተወላጆች ያስተባበሩት ሰልፍ አውሮፓ ፓርላማ ፊት ለፊት ይካሄዳል፤ “በጦርነት ሲሸነፉ በየአደባባዩ ጩኸት የጀመሩት የጸረ ኢትዮጵያ ስብሰብ ናቸው”

Date:

አዲስ ሪፖርተር | አዲስ አበባ | “ኢትዮጵያን እንደ ጦረኛና ወራሪ አድርገው መጮህና ማስጮህ የጀመሩት በወል ስም ‘ጽምዶ’ የሚባለው ስብስብ የአሚሪካን፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታትን እና የአፍሪካ ሕብረትን የሰላም ጥሪ ወደ ጎን በማለት ጦርነት ከፍተው ሲሸነፉ ነው” በማለት የሰላማዊ ሰልፉን አስፈላጊነት የሚናገሩት በቤልጂየም የአፋር ማህበረሰብ አስተባባሪ አቶ ሃገር ሃመድ ሩአ ናቸው። 

አቶ ሃገር ከብራስልስ በተለይ ለአዲስ ሪፖርተር እንዳሉት “በሳምንት ውስጥ መንግስት እንገለብጣለን” ብለው ጥምረት የፈጠሩት ቡድኖች ዓላማቸው አገር ማፍረስ በመሆኑ በአደባባይ መቃወም አስፈልጓል። 

የፊታችን ታህሳስ 5 ቀን 2026 በብራስልስ የአውሮፓ ፓርላማ ፊት ለፊት በሶስት ዋና ምክንያቶች የሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳል። እንደ አቶ ሃገር ገለጻ “ሱዳን፣ ኤርትራና ግብጽ አለችልን” በማለት የሰላም ጥያቄና ሽምግልናን ወደ ጎን የገፉት ክፍሎች፣ ኢትዮጵያን ወራሪ አድረገው ለመሳል የሚሞክሩት ሙከራ መጋለጥ አለበት።

ተሰባስበው አገር ለማፍረስ የሚችሉትን ሁሉ ያደረጉት ቡድኖች ተመልሰው ኢትዮጵያን ወራሪ አድርገው ለማሳየት በየአገሩ መጮህና ማስጮህ መጀመራቸውን ያመለከቱት አቶ ሃገር፣ አንዳንድ “ኢትዮጵያዊ ነን” የሚሉ አካላት ከሻዕቢያ ጎን ቆመው መታየታቸው አሳዛኝ እንደሆነና ታሪካዊ ጥፋት ሆኖ እንደሚመዘገብ አመልክልተዋል። 

“የአፋር ህዝብና የአፋር ምድር አይከፋፈልም” በማለት ሱልጣን ሀንፍሬ አሊሚራህ መናገራቸውን ያስታወሱት አቶ ሃገር፣ “ሁሉም ጉዳይ እዚህ ውስጥ ነው” በማለት በሰጡት አስተያየት ሰጥተዋል። አሁን ያለው ትውልድም የአሊሚራህን ቃል መርህ አድርርጎ ይኖራል ብለዋል። 

ሱልጣን ሀንፍሬ የአፋር ሕዝብ በቅኝ ግዛትና በፖለቲካዊ ድንበሮች በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ እና በጅቡቲ መካከል ቢከፋፈልም፣ አንድ ሕዝብ፣ አንድ ባሕል እና አንድ ቤተሰብ መሆኑን አጉልተው ሲያስቡ ኖረው ያለፉ ባለታሪክ ናቸው። «በመካከላችን ያለው ድንበር በወረቀት ላይ የተሰመረ እንጂ የአፋርን ሕዝብ ሥጋና ደም የሚለያይ አይደለም፤ የአፋር ሕዝብ በየትኛውም ቦታ ቢኖር አንድነቱንና ወንድማማችነቱን ጠብቆ ለሰላም መቆም አለበት። የአፋር ወጣቶችና የጎሳ መሪዎች በውስጥ ልዩነት ከመከፋፈል ይልቅ ለጋራ ልማት፣ ለትምህርትና ለአካባቢያቸው ጸጥታ በአንድነት ቁሙ” የሚል አደራም አላቸው። 

ይህንኑ በማስታወስ ስለ ሚደረገው ሰልፍ መረጃ የሰጡት አቶ ሃገር፣ “አፋር እንደ ቀድሞው በኢትዮጲያ ጉዳይ አይደራደርም፤ በኢትዮጵያ ጉዳይ ከሚያፈርሷትና ሊያፈርሷት ለዓመታት ከሚሰሩ ኃይሎች ጋር የሚያብሩትን ያወግዛል፤ ሰልፉም መነሻው ይህ ነው” ብለዋል። 

“ኢትዮጵያ ራሷን የምትከላከል አገር እንጂ ወራሪ አይደለችም” በማለት ለአውሮፓ ህዝብ ለማሳወቅ ቀጠሮ የያዙት የአፋር ተወላጆች፣ አገራቸውን የሚወዱ ሁሉ በሰልፉ ላይ እንዲገኙ አመልክተዋል። 

አገር ለማፍረስ የተነሱትን ከማውገዝ ጎን ለጎን በሰልፉ ላይ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ እጃቸውን ከኢትዮጵያ ላይ እንዲያነሱ የሚያሳስብ ጥሪና ጥያቄም ይቀርባል። በሌላ በኩል በአፋር ህዝብ ላይ የሚፈጽሙትን ጭፍጨፋና ወርራ እንዲያቆሙ የአውሮፓ ህብረት አቋም እንዲወስድ ድምጻቸውን ያሰማሉ። 

በቅርቡ የአፋር ሽማግሌዎችን እና የኃይማኖት መሪዎችን በማፈን ወደ ማይታወቅ ስፍራ ይጓጓዘው የኢሳያስ አገዛዝ የአፋር ህዝብን በመከፋፈል እያደረጉ ያሉትን አረመኔያዊ ተግባር ዓለም እንዲረዳ በጋራ ድምጻቸውን እንደሚያሰሙ አምለክተዋል። 

ኢህአዴግ ስልጣን ሲይዝ በሽግግር መንግስት ምስረታ ወቅት የአፋርን ህዝብ ሲበጣጥስ ሱልጣኑ “የአፋርን ህዝብና መሬት መከፋፈል አይቻልም” በማለት የተናገሩትን በድጋሚ ያስታወሱት አቶ ሃገር፣ የቤልጂየም የአፋረ ኮሙኒቲ በዓለም ዙሪያ ካሉ ተመሳሳይ የኮሙኒቲ አባላት ጋር በጋራ እንደሚሰሩ አመልክተዋል። 

«አሰብ የአፋር ነው፤ አፋር ደግሞ የኢትዮጵያ ነው!» የሚለው የሱልጣን ሀንፍሬ አሊሚራህ የማይረሳ መልዕክት፣ ከታሪካዊ እውነታና ከሀገራዊ ፍቅር የመነጨ የዘላለም አሻራቸው ነው። ሱልጣን ሀንፍሬ አሰብ የአፋር ሕዝብ ጥንታዊ መኖሪያና ርስት መሆኑን፣ ይህ ለዘመናት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና አንድነት ደሙን ያፈሰሰ ሕዝብ ደግሞ ከእናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ጋር የማይነጣጠል ሥጋና ደም መሆኑን አስገንዝበዋል። ታላቁ አባት ሱልጣን አሊሚራህ ሀንፍሬ የአፋር ሕዝብና ምድር በድንበር መከፋፈል እንደሌለበት የያዙትን ጽኑ ታሪካዊ አቋም በማስቀጠል፣ አሰብ በሰላማዊና በወንድማማችነት መንፈስ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ለቀጠናው ሕዝቦች የጋራ ብልጽግና መዋል እንዳለበት በመምከር፣ ለትውልድ የሚተላለፍ የአንድነትና የሀገር ወዳድነት ቃል ኪዳናቸውን አኑረው ማረፋቸውን አቶ አገር ተናግረዋል። አቶ አገር ችግሮች በሙሉ በውይይት እንዲፈቱ ምኞታቸውን ገልጸዋል።  

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related