አዲስ ሪፖርተር – “ሙዓለ ጥበባት ዲያቆን ዳንዔል ክብረት እምነታቸው ቀይረው የፕሮቴስታንት ዕምነት ተከታይ ሆነዋ፣ ድንግል ማሪያምን ክደዋል” በሚል የቅብብሎሽ ዘመቻ ሊጀመርባቸው ቀጠሮ እንደተያዘላቸው ተሰማ። ዕቅዱን የተዘጋጀው በኢትዮጵያ አመጽ ለማደራጀት እየሰራ ካለው ቡድን አመራሮች መካከል አንደኛው ክንፍ ነው።
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሚኒስትር የሆኑት ዲያቆን ዳንዔል ክብረት ብልጽግናን ወክለው ለተወካዮች ምክር ቤት ለመመረጥ እንደሚወዳደሩ ሰሞኑን ይፋ መሆኑ ይታወሳል።
የአመጽ አደራጅ ግብረኃይል አባል የሆኑ ለአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ እንደገለጹት፣ ዲያቆን ዳንዔል የሚዲያ ዘመቻ እንዲደረግባቸው ዕቅድ የወጣው በኮሚቴው አባላት ሳይሆን፣ ከጀርባ ሆነው እንቅስቃሴውን በሚመሩ አካላት ነው። ይህ እስከተጻፈ ድረስ ለግብረኃይሉም ሆነ ለአመጽ አመቻች ቡድኑ የቴክኒክ ኮሚቴ አልቀረበም።
“የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ምዕመናን፣ አገልጋዮች፣ አባቶችና በዕምነቱ ዙሪያ ያሉ ባልደረቦቻቸው እንዲቆጡ ማድረግ” በሚል ዲያቆን ዳንዔል ያስተማረቻቸውንና ማዕረጓን ያለንፉግነት ያለበሰቻቸውን ቤተክርስቲያን እንደከዱ ተደርጎ “በትግሉ ሚዲያዎች” በስፋት እንዲቀርብ “እንዲራገብ” ተብሏል። ዜናው በስፋት የዲጂታል ሰራዊቱ እንዲቀባበለው ይደረጋል። ይህ ሲሆን የሚሰጣቸው ስም “መናፍቅ” የሚል እንደሆነም ተመልክቷል።
መረጃውን ያካፈሉት እንዳሉት ዲያቆን ዳንዔል የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እንደከዱ፣ ሲያስተምሩትና ሲሰብኩት የኖሩትን የድንግል ማሪያም አማላጅነት እንዳራከሱ ተደርጎ የተቀነባበረ ቃለ መጠይቅ ውጭ ባሉ የትግሉ ተባባሪ “መምህሮች” በተተታታይ ይቀርባል። እንደ አስፈላጊነቱ ትግሉን የሚደግፉና የትግሉ የዕምነት ክንፍ በሆኑ አባቶች አማካይነት እንዲወገዙ ይደረጋል። የማቆሸሹ ዘመቻ በቀኖናና በሌሎች የቤተክርስቲያኗ መጣህፍት መርሆዎች እንዲደገፍ እንደሚደረግም ለማወቅ ተችሏል።
በአገልግሎት ላይ እያሉ የተቀረጹ ቪዲዮዎችና ምስሎችን በተለያዩ የስላቅና የዕምነቱን ተከታዮችን ሊያስቆጣ በሚችል አግባብ በማዘጋጀት ለማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊቱ እንደሚከፋፈል መረጃውን ካቀበሉት ለመረዳት ተችሏል።
ዲያቆን ዳንዔል በአጫጭር መልዕክቶች አጀንዳ የሚሰጡና የሚቃወሟቸውን የሚያበግን መልዕክት በማስተላለፋቸው ቂም የያዙ በርካታ ስለሆኑ ዜናው በከፍተኛ ደረጃ ለተጀመረው የአመጽ ማነሳሻ ግብአት እንደሚሆን የዕቅዱ ባለቤቶች ዕምነት እንደሆነም ከመረጃው ባለቤቶች ገለጻ ለመረዳት ተችሏል።
“አሁን ላይ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን አየሩን በአግባቡ ስለያዘው ላለመክሰር ሲባል ዕቅዱ ቶሎ ወደ ትግበራ አይሸጋገርም” በሚል እንድተነገራቸው መረጃውን ያካፈሉት አስታውቀዋል። ራሱን የሰላማዊ ትግል አደራጅ አድርጎ የሚጠራው ቡድን ሁለት ክንፎች ነበሩት። በህወሃት ምሪት አቶ ልደቱ የሚመሩት አብሮነት እና በሻዕቢያ ምሪት አቶ ነዓምን የሚመሪት ክንፍ በቅርቡ “ተመሳሳይ ዓላማ ስላለን” በሚል እንዲዋሃዱ መደረጉን በወቅቱ ካወጡት መግለጫና ከስብሰባቸው ኦዲዮ በመረዳት መዘገባችን አይዘነጋም።
ይህ “ምርጫው ዕውቅና እንዳያገኝ እንረባረብ” በሚል ከታጣቂዎች ጋር ጭምር ህብረት ፈጥሮ የሚሰራ ጥምረት ዲያቆን ዳንኤልን ብቻ ሳይሆን፣ ሌሎችንም ባለስልጣናትና ታዋቂ ሰዎችን በመለየት ተመሳሳይ ዘመቻ የማድረግ ዕቅድ እንዳለው የድርጊት መርሃ ግብሩ ያስረዳል።
በጉዳዩ ዙሪያ ዲያቆን ዳንዔል ክብረትን አስተያየት ለማካተት ሙከራ ቢደረግም ማግኘት አልተቻለም። በቅርቡ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጋር በመሆን በጥንታዊ ገዳም በቤተክርስቲያን ስርዓት ከአባቶች በረከትን ሲረከቡና የሄዱበትን ሲተገብሩ ታይተዋል።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






